የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ጥር 15 ፣ | 2015 ዓ.ም – Jan 23 | 2023
Reuters
- በኢትዮጵያ የተሠራው ከምንም ወደ ተምሳሌታዊ ምልክት የመጣው የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና መሥሪያ ቤት የቻይና-አፍሪካ ወዳጅነት ማረጋገጫ ነው ይላል።
የተነሱ ነጥቦች
- በኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ደቡባዊ ዳርቻ በአንድ ወቅት በቆሻሻ የተሞላ መሬት ላይ አሁን እዚያ ቦመንትያ ግንብ ሲመለከቱ የአካባቢው ነዋሪ ዋቅጅራ ቶቶፋ “በእርግጥ እንደ ህልም የሚመስል የማይታመን ውጤት እንደሆነ
- በአጭር ጊዜ የተሠራ ድንቅ ሀንጻ መሆኑ እጅ የሚደነቅ እንደሆነ
- በአፍሪካ ተላላፊ በሽታ በተከሰተ ቁጥር ልክ እንደሌላው አለም ህክምና ማግኘት እንዳልተቻለና ወረርሽኙ ኮቪድ በተከሰተ ጊዜም በመጀመሪያ ክትባት መውሰድ እንዳልተቻለም ተጠቅሶ አሁን ግን ትልቅ ተስፋ እንዳለ መነገሩ
- በኢህ ህንጻ ግንባታና የአፍሪካውያን መዲና አዲስ አበባ መገንባቱንም ኢትዮጵያውያን ድስታቸውን መግለጻቸውን የሚገልጹ ዋና ዋና ሀሳቦች ተነስተዋል።
All Africa
- የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ትግራይ ከተሞችን ለቀው ሲወጡ እንደታዩ ነው የሚገልጸው።
የተነሱ ነጥቦች
- የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ጋር በመሆን ሲዋጉ ከነበሩበት በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ከተሞችን ለቀው ሲወጡ መታየታቸው
- የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ለሁለት ዓመታት ያህል ከቆየ ጦርነት በኋላ በተረጋጋው አካባቢ መረጋጋትን መፍጠሩ
- ስምምነቱ ህወሓትትጥቅ መፍታትን ያጠቃልላል። የሕወሃት ጦር ቅድሚያ የኤርትራ ሠራዊት ከግትራይ እንዲወጣ ቢጠይቁም አንዳንድ የኤርትራ ተዋጊዎች ግን በየአካባቢው ተሠማርተው መቆየታቸው
- አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ኤርትራ የተቀሩ ወታደሮቿን እንድትመልስ እንዳሳሰቡ የሚገልጹ ዋና ዋና ነጥቦች ተነስተዋል።
ሊንክ https://allafrica.com/stories/202301220025.html
Garowe Online
- አሚሪካ የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ መውጣቱ እንደምትገፍና ጥሩ እርምጃ እንደሆነም አደርጋ መቀበሏን እንደገለጸች የሚገልጽ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- አሜሪካ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ መውጣቸው ጥሩ እርምጃ እንደሆነ መግለጿ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የትግራይን ሠላም ለመመለስ ቁርጠኛ እንደሆነ የሚገልጽ እርምጃ እንደሆነም መገለጹን የሚያሳዩ ሀሳቦች ተነስተዋል።
ሊንክ – https://www.garoweonline.com/en