Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች 

ሰኔ 11 | 2014 ዓ.ምJune 18 |2022

VOA

  • በኢትዮጵያ  በነበረው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ የታሰሩ የትግራይ ተወላጆች በችግር እና በበሽታ  መጎዳታቸውን የሚተርክ ነው።
  • የታሠሩትም በእስር ቤት ብዙ መንገላታት እየገጠማቸው እንደሆነም ለማሳየት የሞከረና ይህም አሁን ይደረጋል ለባለው ድርድር የህወሓት ሀይል ካሁኑ ካሣ እጠይቃለሁ የሚለውን የሚደግፍ የአሜሪካ ሚዲያ ሀሳብ መሆኑ ነው።
  • ዘገባው በቀጥታ ለማስተላለፍ የፈለገው ብዙ የትግራይ ተወልጆች በመንግስት አካላት ያለም ፍትፍህ እንደታሠሩ ነው።
  • ይህም መንግስት የተለያዩ ሥዉር ቦታዎች የትግራይን ተወላጆች ለማሠር ማቆያዎች ሠርቶ በዚያ እንዳሠራቸውም አንዳንድ የቦታ ስሞችን በመጥራት ላማስረዳት ሞክሯል።
  • ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ

ሊንክ  – https://www.voanews.com/a/in-ethiopia-s-civil-war-thousands-of-jailed-tigrayans-endured-squalor-and-disease/6621910.html

The New Arab

  • በኦሮሞ አማፂያን በከፈቱት ጥቃት በፀጥታ ሃይሎች ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን የኢትዮጵያ መብት ኮሚሽን መግለጹን የሚያስተጋባ ነው።
  • ዘገባው አስቀድመው ተኩስ የከፈቱት የኦሮሞ አማጽያን ቡድን እንደሆኑና በከፈቱት ተኩስም ባካባቢው የሚኖሩ ሠላማዊ ዜጎች መጎዳታቸውንም ያሳየበት ዘገባ ነው።
  • ይሁም የደርሰው ያለፈው ማክሰኞ በጋምቤላ ክተማ  ላይ የተፈጸመው ጥቃት በጸጥታ ሃይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በሚል ራሱን በሚጠራው ቡድን  መካከል በኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪ ተብሎ በተፈረጀው አማፂ ቡድን መካከል ለሰአታት የፈጀ የተኩስ ልውውጥ  እንደሆነና በዚህም የንጹሀን ሕይወት ያላግባብ እንዲጠፋ የመንግስት ታጣቂ ሀይሎች አስተዋጻኦ እንዳለበትም አመላክቷል።
  • ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ

ሊንክ   https://english.alaraby.co.uk/news/ethiopia-rights-body-says-security-forces-killed-civilians-after-rebel-attack

      Egypt  Independent

  • መንግስት እና የህወሐት ሃይሎች ወደ ድርድር  ሊገቡ እንደሆነ ነው የጽፈው።
  • ከሠሞኑ እንደተለመደው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ለድርድሩ የሚሆን ኮሚቴ ማዋቀራቸውን  እንደተናገሩ በማስተጋባት መንግስት ተገዶ ወደ ድርድር እደመጣ ለማሳየት ያለመ ዘመቻ ይመስላል።
  • ይህንንም ለማሳያት ጠ/ሚኒስትርሩ ኮሚቴ ከ 10 እስከ 15 ቀናት ውስጥ  ከድርድሩ ጋር በተያያዘ ማጥናት ያለበትን አጥንቶ ከህወሓት ጋር የመደራደርያ ሁኔታ ያሳውቃል የተባለውን በማንሳት መንግስት ድርድሩን ባስቸኳይ ለማድረግ እንደሚፈልግም ለማሳየት የሚችል ሀሳብ  አካቷል።
  •   ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ

ሊንክ –  https://egyptindependent.com/ethiopian-government-and-tigrayan-forces-move-towards-negotiations/

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *