Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

በኢትዮጵያ 37 ሺ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ

INSA

በኢትዮጵያ 37 ሺ በሚሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ

በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ 37‚000 ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ይፋ አድርጓል፡፡

ተቋሙ እንዳለው “ሳይበር ሆርስ ግሩፕ” የተሰኘ የመረጃ ሰርሳሪ ቡድን አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ኮምፒውተሮች ላይ ለመልቀቅ ዝግጅት ማድረጉ ተደርሶበታል፡፡

ይህ ቫይረስ “ብላክ ፒራሚድ ዋር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን 37‚000 በሚደርሱ የሀገራችን ኮምፒውተሮች ላይ ማነጣጠሩ ተገልጿል፡፡

ይህ ቡድን ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሀገራችን ድረ-ገጾች ላይ የመበርበር ሙከራ ሲያደርግ መቆየቱም ታውቋል፡፡

በመሆኑም ሁሉም የሳይበር ምህዳሩ ተጠቃሚዎች ተገቢውን የሳይበር ደህንነት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አሳስቧል፡፡

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *