በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውጭ ሚዲያዎች ዘገባ
ጥቅምት 20 2017 ዓ.ም October 2024
AercAfrica
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ጥናትና ምርምር ኮንሰርቲየም (ኤአርሲ) እና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (PSI) በኢትዮጵያ የሰብአዊ ካፒታል ልማት የፖሊሲ ውይይት አውደ ጥናት በአዲስ አበባ ማካሄዱን በማንሳት በቢል ኤንድ ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ የተደረገው ትልቅ ፕሮጀክት አካል የሆነው ይህ ዝግጅት በኢትዮጵያ የኤች.ሲ.ዲ. ፕሮጀክት ጉዳይ ጥናት ላይ ያተኮረ እንደነበር በማንሳት አውደ ጥናቱ ትምህርትን ከኢንዱስትሪ መስፈርቶች ጋር ለማጣጣም እና በትምህርት ላይ ያለውን የሥርዓተ-ፆታ ክፍተት ለማስተካከል ፖሊሲዎች አስፈላጊ መሆናቸውን ማስመልከቱን በተመለከተ የተጻፈ ማብራሪያ ነው።
ዋና ዋና ነጥቦች
- የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ጥናትና ምርምር ኮንሰርትየም (ኤአርሲ) እና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (PSI) የሰብአዊ ካፒታል ልማት ፖሊሲ ውይይት የቅርስ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ማካሄዱንና አውደ ጥናቱ በቢል ኤንድ ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን (ቢኤምጂኤፍ) የገንዘብ ድጋፍ የተደረገው የኤችሲዲ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ ጉዳይ ጥናት ላይ ያተኮረ እንደነበር በማንሳት አውደ ጥናቱ በጥቅምት 2024 በቡርኪናፋሶ፣ኬንያ፣ማዳጋስካር፣ናይጄሪያ እና ሴኔጋል የተደረጉ ተመሳሳይ ውይይቶች አካል እንደነበር ለማሳየት ሞክርዋል።
- በአውደ ጥናቱ የኢትዮጵያን የሰው ካፒታል ልማት ተግዳሮቶች እና የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብሮችን ለመቅረፍ የትብብር ዉይይት ያለውን ጠቀሜታ በማመልከት የኢትዮጵያ መንግስት በትምህርትና ስልጠና መርሃ ግብሮች ላይ የሚያደርገውን ኢንቨስትመንት አጠናክሮ እንዲቀጥልም አውደ ጥናቱ ማሳሰቡን ለመግለጽ ሞክርዋል።
Allafrica
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ውይይት ኮሚሽን ተወካዮች የሀገሪቱን አንገብጋቢ ችግሮች ለመፍታትና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ብሔራዊ ውይይቱ ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ የተሰጡትን አስተያየቶች በማንሳት በሌላ መንገድ መፍትሄ የሚሹ አካላትም እንኳን ይህን ሰላማዊ ሂደት እንዲቀበሉ ማሳሰባቸውን በማንሳት በወላይታ ሶዶ ከተማ የተካሄደው የምክክር መድረክ ከሰባት ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ተሳታፊዎችን በመለየት ግብአት በማሰባሰብና በመለየት መካሄዱን የሚተነትን ነው።
ዋና ዋና ነጥቦች
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ውይይት ኮሚሽን ተወካዮች ብሄራዊ ውይይቱ አንገብጋቢ የሆኑ ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ያለውን ጠቀሜታ መግለጻቸውን በማንሳት የሀይማኖት አባቶች ቀሲስ በድሉ ፈቀደ የውይይት ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና የህብረተሰቡን እሴቶች ለማጠናከር ያለውን ሚና አጽንኦት በመስጠት የዜጎችን ስቃይ ለማስቆምና ድህነትን ለማሸነፍ የተሻለው መንገድ መሆኑን በመግለጽ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በንቃት እንዲሳተፉ አቶ በድሉ ማሳሰባቸው
- በወላይታ ሶዶ ከተማ የተካሄደው የምክክር መድረክ ከሰባት ክልሎችና ከሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ተሳታፊዎችን በመለየት ግብአት ማሰባሰብን እንደሚያካትትና የምክክሩ ሂደት በ12 ዞኖች ከሚገኙ 96 ወረዳዎች የተውጣጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የህዝብ ተወካዮች፣ የማህበረሰብ ተወካዮች እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችና ተወካዮችን እንደሚያካትት
ሊንክ https://allafrica.com/stories/202410300163.html
Agra NEWS
የ AGRA VALUE4HER ተነሳሽነት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሴቶችን የግብርና ባለሙያዎችን ለማብቃት አቅሙን የሚያጎለብት እና የተሻሻለ የፋይናንስ አቅርቦትን በማቅረብ እድገታቸውን የሚያደናቅፉ መዋቅራዊ እንቅፋቶችን በመፍታት እንደሆነ አንስትዋል።
ዋና ዋና ነጥቦች
- ሴቶች 75% የእርሻ ስራ የሚሰሩ እና እስከ 80% የሚሆነውን የወጪ ንግድ ገቢ በኢትዮጵያ ያዋጣሉ ነገርግን የንግድ ስራቸውን ለማስፋት ትልቅ እንቅፋት እንደሚገጥማቸው
- የVALUE4HER ተነሳሽነት ግልጽ የሆነ አላማ በመያዝ እንቅፋቶችን በማፍረስ እና ሴቶችን የግብርና ባለሙያዎችን በአቅም ግንባታ እና በተሻሻለ የፋይናንስ አቅርቦት ማብቃት እንደሆነ
- የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የማዕዘን ድንጋይ የሆነው ግብርና 80 በመቶውን የወጪ ንግድ ገቢ እንደሚያበረክት
Tvbrics
ዋና ዋና ነጥቦች
- የኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ድንበር ተሻጋሪ የከርሰ ምድር ውሃን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ አያያዝ ላይ ጥናቶችን እንደተጀመረ በማንሳት በከተሞች መስፋፋት፣ በሕዝብ ቁጥር መጨመር እና በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎች የተነሳ እየጨመረ የመጣውን የውሃ ፍላጎት የሚፈታ እንደሆነ
- የኢትዮጵያን የበለፀገ የውሃ ሀብት በመምራት ረገድ ውጤታማ አመራር እንደሚያስፈልግ ሚኒስትር ዴኤታው አብርሃ አዱኛ ማስታወቃቸውን በማንሳት የከርሰ ምድር ውሃ እንደ ተከላካይ አማራጭ በተለይም የውሃ እጥረት ላለባቸው ክልሎች ቅድሚያ መሰጠቱ