በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውጭ ሚዲያዎች ዘገባ
ጥቅምት 19 2017 ዓ.ም Oct 29 2024
Garoweonline
የሶማሌ ላንድ ተቃዋሚ ፓርቲ በቅርቡ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ግልፅነት የጎደለው መሆኑን ቢነቅፉም ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደሚደግፍ መግለጹን አንስትዋል።
ዋና ዋና ነጥቦች
- ዋናው ግኝቱ ዋዳኒ ፓርቲ የሶማሌላንድ እና የኢትዮጵያን ግንኙነት የሚደግፍ ቢሆንም በቅርቡ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ግልፅነት የጎደለው መሆኑን
- የመግባቢያ ሰነዱ ዝርዝር ይፋዊ ባይሆንም ተቃዋሚዎች በሶማሌላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ቀጣይነት ያለው እና ጠንካራ ሆኖ እንደሚቀጥል እምነት እንዳላቸው የገለጹት የዋዳኒ ፓርቲ ባለስልጣን ምንም ችግር እንደሌለው
- “ፓርቲያችን ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ባለው ግንኙነት እውነተኛ መሆኗን በመተማመን፣ ንግድን፣ ደህንነትን እና ኢነርጂንን ጨምሮ በብዙ መስኮች የበለጠ ትብብር ለማድረግ እንጠባበቃለን” ማለታቸውን
- “የኢትዮጵያ የወደብ ተጠቃሚነት ፍላጎት ህጋዊ ፍላጎት ነው እና የበርበራ ወደባችን በትክክል የተገነባው ለዚሁ ዓላማ እንደሆነ ቢያነሳም ሞቃዲሾ ምንም አይነት ድርድር ከመደረጉ በፊት አዲስ አበባ ስምምነቱን ማቋረጥ አለባት የሚል አቋሟን መቀጠልዋን
ሊንክ https://www.garoweonline.com/en/news/somalia/ethiopia-is-genuine-partner-to-somaliland-opposition-party-says
The Africa report
በሶማሊላንድ የሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እና ለአካባቢው መረጋጋት ያለው ጠቀሜታ፣ እውቅና ፍለጋ እና አለመረጋጋት ሊያስከትሉ የሚችሉ ስጋቶች የሚያነሳ ነው።
ዋና ዋና ነጥቦች
- በሶማሌላንድ ስለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እና ለአካባቢው መረጋጋት ያለውን ጠቀሜታ፣ እውቅና ፍለጋ እና አለመረጋጋት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ችግሮች
- ጽሑፉ የፖለቲካ ምኅዳሩን፣ ክልላዊ አንድምታውን፣ እና የነጻነት ግፊትን እና የስልጣን ተለዋዋጭነትን እንደሚያሳይ
- ምርጫው ለሶማሌላንድ ዲሞክራሲያዊ ጤና እና በድንበሯ እና በአካባቢው ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ያለውን ጠቀሜታ አጽንኦት መስጠቱ ሊንክ https://www.theafricareport.com/366314/somaliland-elections-whats-at-stake/
Berlin
የኢትዮጵያን፣ ሶማሊያን እና ሶማሌላንድን የሚያሳትፈው ጂኦፖለቲካል ሁኔታ መቀያየር ኢኮኖሚያዊ እና ስትራቴጂካዊ ጥቅሞችን አጽንኦት ይሰጣል። በተጨማሪም ስለ ወታደራዊ የኃይል ሚዛን፣ አልሸባብን በመዋጋት ላይ ስላለው የጋራ ጥቅም እና ሊባባሱ ስለሚችሉ ስጋቶችም የሚያብራራ ነው።
ዋና ዋና ነጥቦች
- ኢትዮጵያን፣ ሶማሊያን እና ሶማሌላንድን የሚያካትተው ውስብስብ ጂኦፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አጠቃላይ እይታ
- የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በሶማሌላንድ ወደብ ላይ የምታደርገውን ኢንቨስትመንት እና የኢትዮጵያን የባህር መዳረሻን የመሳሰሉ የቀጣናው ሀገራት ኢኮኖሚያዊ እና ስትራቴጂካዊ ጥቅሞችን በማጉላት
- የአልሸባብን ስጋት ለመዋጋት ያላቸውን የጋራ ፍላጎት በማጉላት በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ስላለው ወታደራዊ የኃይል ሚዛን ውይይት
- የውጪ ተዋናዮችን ተሳትፎ እና የትጥቅ ግጭትን ጨምሮ የመስፋፋት ሊያስከትሉ የሚችሉትን አደጋዎች ዝርዝር።
- በቀጠናው የውስጥ ግጭቶች መባባስ ላይ አጽንዖት መሰጠቱ