Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውጭ ሚዲያዎች ዘገባ

biometricupdate
የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና የዲጂታል መታወቂያ እድገት የተመለከተ ነው።
ዋና ነጥቦች
• የኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጥረቶች በስትራቴጂካዊ አጋርነት የተጠናከሩ መሆናቸውን በማንሳት
የሀገሪቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አቶ በለጠ ሞላ የዲጂታል ፐብሊክ መሠረተ ልማትን ለማስፈን፣ ፈጠራን ለማነሳሳት እና የስራ እድል ለመፍጠር የመንግስት ስትራቴጂ አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል።
• ኢትዮጵያ 14.6 ሚሊዮን ሰዎችን ለፋይዳ መታወቂያ የተመዘገበች ሲሆን በ2030 ወደ 90 ሚሊዮን ተመዝጋቢዎች ለመድረስ መታቀዱን ።
• የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማሊ እና ጋምቢያን ጨምሮ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አድናቆትን አግኝቷል።
• የኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ አሰራር ሂደት በመጪው ID4Africa ዝግጅት ላይ ይገለፃል።

ሊንክ https://www.biometricupdate.com/202505/ethiopia-digital-transformation-efforts-progress-as-country-readies-for-id4africa-2025

Energynews
የኢትዮጵያ ኢነርጂ ስትራቴጂ በምስራቅ አፍሪካ የተመለከተ ነው።

ዋና ነጥቦች
• ኢትዮጵያ በአምስት ዓመታት ውስጥ የብሔራዊ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አቅርቦትን ከ54 በመቶ ወደ 78 በመቶ ለማሳደግ አቅዳለች ይህንም የአባይ ግድብ ዋና ፕሮጄክቷ በማድረግ እንደሆነ ተነስትዋል።
• የአባይ ግድብ ሀገራዊ ኢኮኖሚ ልማትን ለመደገፍ ለውጭ ንግድ የሚውል ትርፍ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት የሰፊው የኢንዱስትሪ ልማት እቅድ አካል ነው።
• ኢትዮጵያ ትርፍ የኤሌክትሪክ ኃይልን ወደ ሱዳን፣ኬንያ፣ጅቡቲ እና ታንዛኒያ ለመላክ ተዘጋጅታለች፣ይህም ቀጠናዊ ትስስርን በማጠናከር የጋራ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን እያስመዘገበች ነው።
• የኢትዮጵያ ኢኒሼቲቩ ከረጅም ጊዜ ክልላዊ ጥረት ጋር የተቆራኘ የኃይል ፍርግርግ ጋር ይጣጣማል።
• ድንበር ተሻጋሪ የኢነርጂ አውታሮች ከአፍሪካ ልማት ባንኮች የገንዘብ ድጋፍ እያገኙ ሲሆን ይህም የተለያየ የሃይል ድብልቅ እንዲኖር ያስችላል።
• ክልላዊ ውህደት ያለውን አቅም በጋራ መጠቀምን በማስተዋወቅ የሃይል ብክነትን እና የመሠረተ ልማት ወጪዎችን ይቀንሳል።
ሊንክ https://energynews.pro/en/ethiopia-accelerates-regional-energy-integration-with-abbay-dam/

Thepeninsulaqatar.com
የኢትዮ ጅቡቲ ደረጃ መለኪያ የባቡር አክሲዮን ማህበር ሚናን ለማስፋት ማቀዱን የተመለከተ ነው።

ዋና ነጥቦች
• 752 ኪሎ ሜትር በኤሌክትሪፊኬድ የሚሸፍነውን የባቡር መስመር አመታዊ የጭነት አቅም ከሁለት ሚሊዮን ቶን ወደ 6.2 ሚሊዮን ቶን በ2027 ለማሳደግ ማሰቡን በማንሳት የባቡር መስመሩ ቢያንስ 25 በመቶውን የኢትዮጵያ ገቢና ወጪ ንግድ ለማስተናገድ አቅዷል።
• የባቡር ሐዲዱ ተግባራት እንደ መልቲ ሞዳል ትራንስፖርት፣ ጭነት ማስተላለፊያ፣ መጋዘን፣ የጉምሩክ ክላንስ እና የመንገደኞች አገልግሎቶች ባሉ እሴት-ተጨመሩ አገልግሎቶች ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው።
• የባቡር መስመሩ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የትራንስፖርት ኮሪደርን ወደ ጅቡቲ ወደብ በማድረስ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ በከፍተኛ ደረጃ አሻሽሏል።
• የባቡር ሀዲድ ኤሌክትሪክ አሰራር ወጪ ቆጣቢ እና ለአካባቢ ጥበቃ ዘላቂነት ያለው የመንገድ ትራንስፖርት አማራጭ ይሰጣል።
• የኢዲአር አመታዊ የካርጎን አቅም ከ2.09 ሚሊዮን ቶን ወደ 10.1 ሚሊዮን ቶን እና የመንገደኞች ቁጥር ከ180,000 አካባቢ ወደ 560,000 ለማሳደግ ያለመ ነው።
• የባቡር መንገዱ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ፣ ሮሊንግ ስቶክ ማሻሻያ፣ የሎጂስቲክስ ስራዎችን ዲጂታላይዜሽን እና የአገልግሎት ብዝሃነትን የሚያካትት ዘርፈ ብዙ ስትራቴጂን በመተግበር ላይ ነው።

ሊንክ https://thepeninsulaqatar.com/article/06/05/2025/ethiopia-djibouti-railway-pledges-to-reshape-trade-dynamics-foster-regional-development

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *