Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውጭ ሚዲያዎች ዘገባ

ጥቅምት 29 2017 ዓ.ም Nov 8 2024

World bank

ኢትዮጵያ ለስደተኞች በህጋዊ መንገድ የመስራት መብትን መስጠትዋን ይህም በስራ ሃይል ውስጥ በግልፅ እንዲሳተፉ፣ ንግድ እንዲጀምሩ እና ለአካባቢው ኢኮኖሚ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ እንደሚያስችል አንስተዋል። 

ዋና ዋና ነጥቦች:
  • የኢኮኖሚ ዕድሎች ፕሮግራም (ኢኦፒ) በአለም ባንክ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የተደረገ የትብብር ጥረት መሆኑን በማንሳት ኢኦፒ ለሁለቱም ኢትዮጵያውያን ዜጎች እና ስደተኞች ኢኮኖሚያዊ ዕድሎችን በዘላቂነት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን
  • ፕሮግራሙ የተነደፈው ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ፣ ስደተኛ እና አስተናጋጅ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን በማንሳት
  • በርካታ ኤርትራዊያን ስደተኞች ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ እና መደበኛ የስራ ልምድ ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ለስራ ገበያ ውድ ሀብት መሆናቸውን  
  • የኢትዮጵያ የስደተኞችን ኢኮኖሚ ማካተት አካሄድ ለሌሎች የስደተኞች ጉዳይ ረዘም ላለ ጊዜ ለሚታገሉ አገሮች ጠቃሚ ትምህርት ኣንደሚሰጥ በቀጣይ ትብብር እና ጥረት ሁሉንም የሚጠቅም የስደተኞች ማካተት ሞዴል መፍጠር እንደሚቻል የአለም ባንክ እንደሚያምን

ሊንክ https://www.worldbank.org/en/news/feature/2024/11/07/ethiopia-grants-refugees-the-right-to-work.print

 
Carnegieendowment  

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል በአፍሪካ ቀንድ እየጨመረ ያለውን ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ይዳስሳል። ፅሁፉ ሶማሊያ እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ተጽእኖ ለመመከት አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ ትብብርን በስትራቴጂ እየገነባች መሆኑን በማንሳት በስፋት ይዳስሳል። 

ዋና ዋና ነጥቦች:
  • ሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ውጥረት መፈጠሩን በማንሳት  ኢትዮጵያ በሰሜናዊ ሶማሌ ክልል ራሱን ገንጥሎ ከሚጠራው ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙን ይህም  ስምምነቱ ኢትዮጵያ ለ50 ዓመታት ስትራቴጅካዊ የባህር መስመር እንድትጠቀም እንደሚያስችላት ነገር ግን ሶማሊያ ይህንን በሉዓላዊነቷ ላይ እንደ ስጋት መመልከትዋን
  • ሶማሊያ ቀጠናዊ እና አለም አቀፋዊ ጥምረቶችን በማጠናከር የኢትዮጵያን ተፅእኖ ለመመከት ስትሰራ ቆይታለች። ይህም ከቱርክ ጋር ለመከላከያ እና ኢኮኖሚ ትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን እንደሚያካትት በማንሳት  የቱርክ ፓርላማ የቱርክ ወታደሮች በሶማሊያ ግዛት ውስጥ ለሁለት አመታት እንዲሰፍር ማጽደቋን
  • ሶማሊያም ከግብፅ ጋር የመከላከያ ትብብር ፕሮቶኮልን መፈራረምዋን በማንሳት ግብፅ የአፍሪካ ቀንድ ደኅንነትን እንደ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እንደምታይ ገልጽዋል።ሶማሊያን በተመለከተ በካይሮ እና አንካራ መካከል እያደገ ያለው ስምምነት በአፍሪካ ቀንድ የሁለቱ ሀገራት የወደፊት ትብብር ላይ ጠቃሚ ጥያቄዎች እንደሚያስነሳ
  •   ሶማሊያ መንግስቷ በሶማሊላንድ ውስጥ ከሚገኙ ተገንጣይ ባለስልጣናት ጋር የገባውን ቅድመ ውል እንዲያፈርስ በአዲስ አበባ ላይ ከፍተኛውን የፖለቲካ ጫና እያሳደረች መሆንዋን

ሊንክ  https://carnegieendowment.org/sada/2024/11/somalia-ethiopia-relations?la

Tvbrics

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ስላሴ በአዲስ አበባ በተካሄደው "የአለም የረሃብ ኮንፈረንስ" ላይ መንግስት ያከናወናቸውን ስኬታማ የስንዴ ልማት ስራዎች ማድነቃቸውን በማንሳት  ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ላደረጉት መሪነት አመስግነው የአፍሪካ መንግስታትና የግሉ ሴክተር የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ ዘላቂ ልማትን በማስፋት አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጠይቀዋል። ጉባኤው ከ1,500 በላይ ከፍተኛ ተሳታፊዎችን መሰብሰቡን አንስትዋል። 

ዋና ዋና ነጥቦች:
  • ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን በመቻል እና በምግብ ዋስትና ላይ እያስመዘገበች ያለችበትን ሂደት አጽንኦት መስጠታቸው
  • በመንግስት የተሳካ የስንዴ ልማት ውጥኖች ራስን መቻል እና ትርፍ ሰብሎችን ወደ ውጭ መላክ ማስቻላቸው
  • ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ግብርና ልማት ላደረጉት አመራር እና ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸው
  • የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ እና ዘላቂ ልማትን ለማስፋፋት በአፍሪካ መንግስታት እና በግሉ ሴክተር መካከል ትብብር እንዲደረግ ጠየቀ።
  • በUNIDO፣ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት የተዘጋጀው ኮንፈረንስ ከ1,500 በላይ ከፍተኛ ተሳታፊዎችን ማሳተፉን
ሊንክ  https://tvbrics.com/en/news/ethiopian-president-taye-atske-selassie-emphasises-country-s-progress-in-food-security/

About Post Author

1 thought on “በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውጭ ሚዲያዎች ዘገባ

  1. “Such a refreshing read! 💯 Your thorough approach and expert insights have made this topic so much clearer. Thank you for putting together such a comprehensive guide.”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *