በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውጭ ሚዲያዎች ዘገባ
ጥቅምት 25 2017 Nov 4 2024
usembassy
የፕሪቶሪያው ስምምነት አላማዎች ለሁለት አመታት የዘለቀውን አስከፊ ጦርነት ማስቆም፣ የተፈናቀሉ ዜጎች በገዛ ፈቃዳቸው የሚመለሱበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ ማድረግ እና ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር ፍትሃዊነት እና ተአማኒነት ያለው ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት እንዲደረግ መጠየቁን የሚያብራራ ነው።
ዋና ዋና ነጥቦች
- ይህ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የተሰጠ መግለጫ እንጂ የጥናት ጥናት ስላልሆነ ተፈጻሚነት
- ዩናይትድ ስቴትስ ለሰላም መሰረት ለመጣል ከአፍሪካ ህብረት፣ ከመንግስታቱ ድርጅት እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር መተባበርዋን
- ዩናይትድ ስቴትስ በ COHA ትግበራ ላይ የተደረገውን ጠቃሚ መሻሻል በደስታ እንደምትቀበል እና በግጭቱ የተፈናቀሉ ዜጎች በሙሉ በፈቃደኝነት የሚመለሱበትን ሁኔታ የማመቻቸት፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ከትግራይ የሚወጣበትን ሁኔታ እንዲያመቻች እና ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር ፍትህ ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት እንዲታይ የኢትዮጵያ መንግስት ርምጃውን እንዲያፋጥን እንጠይቃለን በማለት መጠየቃቸው
- አማራ እና ኦሮሚያ፣ አለመግባባቶችን በድርድር እንዲፈቱ የአሜሪካ ኢምባስስይ መጠየቅዋን
ሊንክ https://et.usembassy.gov/second-coha-anniversary/
AllAfrica
6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄዱን ተከትሎ በጉባዬው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፓርላማ አባላት ለተነሱት እጅግ በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎችን ምላሽ መስጠታቸውን ተከትሎ መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ማሻሻያዎችን በማጠናቀቅ አገራዊ መነቃቃትን በማጎልበት በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት እየሰራ መሆኑን የሚተነትን ነው
ዋና ዋና ነጥቦች
- በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ ማሻሻያዎች መጠናቀቁን እና አገራዊ መነቃቃትን መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ማስታወቃቸውን በማንሳት በበጀት አመቱ 8.4% እድገት የተጠበቀ ሲሆን ግብርናው በ6 ነጥብ 1 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ “የለማት ጥሩፋት” ዘርፍ ተስፋ ሰጪ እድገት የታየበት እንደሆነ በማንሳት በበጀት አመቱ የ5.4 በመቶ እድገት ማስመስገብዋን በማንሳት ኢትዮጵያ ራሷን በአለም አቀፍ ደረጃ በቡና አምራችነት ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንድትገኝ እየሰራች እንደሚገኝ መግለጻቸው
- የኢንዱስትሪ ዘርፍ ዕድገት በተመለከተ የኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ መስፋፋት የኢንዱስትሪውን ዘርፍ አበረታቶ በማምረት አቅም 67 በመቶ እድገት ማስገቡን በማንሳት በበጀት አመቱ የኢንዱስትሪው ዘርፍ በ12 ነጥብ 8 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ መገለጹ
- የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የኢኮኖሚ እድገት በተመለከተ የዶላር ምንዛሪ ከብር ጋር መጀመሩ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፈወስ ያለመ እንደሆነ በማንሳት ያመጣውን አስተዋጾ በመዘርዘር ምን ያህል የመንግስትን ገቢ በከፍተኛ ደረጃ ያሳደገ እንደሆነና ባለፉት ሶስት ወራት 180 ቢሊዮን ብር እንዲሰሰብ ማድረጉን በተጨማሪም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ6.4 በመቶ በማደግ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን መፍጠር መቻሉን መነሳቱ
- የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አገሪቱ ያለባትን የብድር ጫና ለመቋቋም የሚያስችል አቅም እንድትፈጥር ማስቻሉን
ሊንክ https://allafrica.com/stories/202411040021.html