Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

መስቀል አደባባይ ፕሮጀክት ተመረቀ

የመስቀል አደባባይ ብዙ ያየ ብዙ ያሳለፈ የማንነታችን ክፋይ የመሰብሰቢያችን ሲሳይ ነው። የብዙ ሀገር መሪዎችን ተቀብሎ አስተናግዷል፣ በህልፈተ ህይወት የተሰናበቱ ታላላቅ መሪዎችን ሸኝቷል።

በመስቀል ደመራ በአል ደምቋል፣ ታላላቅ የህዝብ በአላትን አስተናግዷል፣ የድጋፍና የተቃውሞ ሰልፎችን በትዝብት አይቷል፣ በየማለዳው የአካል ብቃት ሯጮችንና ስፖርተኞችን አደግድጎ ተቀብሏል። ስሙ ተለዋውጣል፣ የአብዮት አደባባይ ሆኖ የመሪዎችን ቁጣና የህዝብን እምባ በአርምሞ ታዝቧል።

የምርጫ 97 እና የሰኔ 16ን የህዝብ የገነፈለ ስሜት በሰፊ ሆዱ ተሸክሞ አሳልፏል። የሀገሪቱ ብቸኛ ታላቅ አደባባይ እንደመሆኑ የመጣውን ታላቅ ሁነት ሁሉ ለብቻው እንደአመጣጡ ተቀብሎ ሸኝቷል። በአዘቦት ቀን ደግሞ ወናውን ተሰጥቷል፣ አላፊ አግዳሚውን በትዝብት ተመልክቷል።

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *