Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ ዘገባዎች

የካቲት 9 – 2014

CGTN

ኢትዮጵያ በዋና ከተማዋ አዲስ አእበባ እምብርት ላይ የሚገኘውን 209.15 ሜትር ከፍታ ያለው የሀገሪቱ ትልቁን የንግድ ባንክን ዋና መስርያ ቤት ቢሮ የያዘውን 209.15 ሜትር ከፍታ ያለው በቻይና የተገነባውን ታሪካዊ ህንጻ አስመረቀች።

https://africa.cgtn.com/2022/02/14/ethiopia-inaugurates-chinese-built-landmark-building-in-capital/

https://www.aljazeera.com/news/2022/2/15/ethiopia-parliament-votes-to-lift-state-of-emergenc

Aljazeera

የኢትዮጵያ ፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ድምጽ ምስጠቱን የሚያብራራ ዘገባ ነው። ይህም የሚያሳየው የሀገሪትቱ ሠላም ወደ ተሻለ ደረጃ እንደተመጣ የሚያሳይ እንደሆነ ነው የጻፈው። ለስድስት ወራት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መንግስትን በተለየ መልኩ የመንገድ መዝጋት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ማስቆም፣ የሰዓት እላፊ ገደብ እንዲጣል እና ወታደሮች በተወሰኑ አካባቢዎች እንዲቆጣጠሩ የሚያስችለው እንድነበርም በማንሳት መንግስት የዜጎቹን መብቶች የተጋፋበት እንደሆነ በግርድፉም ቢሆን ለመግለጽ ሞክሯል።

በዘገባው የህወሓትን የኤርትራን ጦር ከኢትይዮጵያ መከላከያ ጋር ውግተውኛል የሚልን ክስም በማካተት ሁኔታውን ለማረጋገጥ ሞክሯል። መንግስት ድል አድርጊያለሁ እያለ ነገር ኝ ጦርነቱ ወ ትግራይ አጎራባች ክልሎች በመዛመት ከፈተኛ ጉዳትና ውድመትን እንዳስከተለም ጠቅሷል።

ምንጭ – https://www.aljazeera.com/news/2022/2/15/ethiopia-parliament-votes-to-lift-state-of-emergency

AP News

ኢትዮጵያ ጦርነትን በማቃለል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዳነሳች ነው የጻፈው። አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት የተቻለው በግጭቱ ውስጥ ያሉ ሁኔታዎች በመሻሻላቸው እንደሆነና ይህ በጠ/ሚኒስትሩ በሚመራ ምክር ቤት መነሳቱን አንስቶ የጠ/ ሚኢስትሩ ጫና እንዳለበት ለማሳየት የሞከር እዘገባ ነው። ይህም መንግስት የሚንቀሳቀሰው በጠ/ ሚኒስትሩ ፍላጎት ላይ እንደሚመሠረት ለማስመሠል ያለመ ዘገባ ነው። በሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታሰራቸውንና ብዙዎቹ ከታህሳስ ወር ለውጥ በኋላ መለቀቃቸውን በማከል መንግስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በዙ የትግራይ ተወላጆች ለማሠርና መብቶቻቸውን ለመጋፋት እንደተጠቀመበትም የሚያሳይ ዘገባ ነው የጻፈው።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም  ከተነሳ በኋላ በዚያ ውስጥ ተጀምረው ያልተቋጩ ሥራዎች የሚኖሩ ከሆነም በመደበኛ የህግ ማስከበር ሂደት እንደሚሠሩ መገለጹን በማብራራት መንግስት በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀበትን ዓለማ ያሳካ እንደሆነም እንደሚያሳይ ለማስገንዘግብ ያለመ ዘገባ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት “በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት በእስር ላይ የሚገኙ ቀሪ ሰዎች እንዲፈቱ ወይም በእስር ላይ የሚገኙትን ሰዎች እንዲፈቱ ለማድረግ ተጨማሪ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ያበረታታ መሆኑንና አሁን ባለው ሁኔታ ከመንግስት ጎን በመቆም ለሠላም መስፈን እንደሚሠራ መሆኑን የሚነግረን ዘገባ ነው።

ምንጭ – https://apnews.com/article/africa-kenya-ethiopia-addis-ababa-abiy-ahmed-114c113bf52114157abcb0b165ef3a50

France 24

በኢትዮጵያ ግጭት የትግራይ ታጣቂዎች ሴቶችን እና ልጃገረዶችን በቡድን አስገድደው ደፍረዋል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዘገባ ማውጣቱን ነው የሚዘገብው። የአምኔስቲን ዝገባ ዋቤ በማድረግ ባለፈው አመት በአማራ ክልል በሚገኙ ሁለት ከተሞች ሆን ተብሎ ሰላማዊ ዜጎችን መግደል እና በቡድን በደርዘን የሚቆጠሩ ሴቶችን እና ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጃገረዶች መገደላቸውን ዘግቦ ቡድኑ ጸረ ህዝብ፣ ጸረ ሀገር እንደሆነ የሚያሳይ ዘገባ ነው የጻፈው። ዘገባው በአስገድዶ መድፈሩ ወንጀል  አዛውንቶችና እስከ 14 ዓመት እድሜ ያላቸው ህጻናትም ተጠቂ እንደነበሩ ግልጾ የህወሓት ቡድን የኢትዮጵያን መንግስትና የተጠቂ ኢትዮጵያውያንን ክስ በመካድ ምንም አለመፈጸሙንና ይልቁኑ መንግስት የትግራይ ወጣቶች ላይ ጭፍጨፋ እየፈጸመ እንደሆነ ሲጮህ የነበረውንና እነዚሁ ሚድያዎችም አብረዋቸው ሲያስተጋቡላቸ የነበረውን የሀሰት ጩኸት ያጋለጠ ዝገባ ነው።

በተጨማሪም በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የህወሓት ቡድን ያታጠቁ  ሠዎችን በጥይቅ በመግደል ጭምር የሚፈጽማቸው ወንጀሎች የበቀል ግድያ መሆናቸውን የሚያሳይ እንደሆነ ገልጾ ነገር ግን የመከላከያ ሠራዊት ከዚህ በፊት መሠል የጦር ወንጀል መሥራቱ ለማሳየት የተጠቀመ ቃል ነው።  ይሁን እንጂ አሁን በዚህ ተቋም ጥናት የተገኘው መረጃ የህወሓት ሀይል የጦር ወንጀል የሚያሳይ እንደሆነ ነው የጻፈው። በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደው ጦርነት በጅምላ ጭፍጨፋ እና በጅምላ አስገድዶ መደፈር የሚበዛበት እንደሆነ በመግለጽ የአሸባሪው ቡድን በነዚህ ወንጀሎች ከፈተኛ ተዋናይ እንደሆነ ግልጿል። ይህ ደግሞ ከማይካድራ ጀምሮ ከፈተኛ የጅምላ ግድያዎችን መፈጸሙንና አሁንም ያን የሚያሳዩ ያልተገኙ መረጃዎች ከተለያዩ አካባቢዎች እንደሚጠበቁም ገልጿል።

ምንጭ – https://www.france24.com/en/africa/20220216-tigray-rebels-gang-raped-women-and-girls-in-ethiopia-conflict-says-amnesty

Xinhua

ኢትዮጵያና ኬንያ አልሸባብንና የኦነግ ሸኔን ታጣቂ ቡድኖችን  በጋራ ለመዋጋት ስምምነት ላይ መግረሳቸውን ነው የጻፈው። ሽብርተኞቹን የመዋጋት ሥራም በኬንያ ፖሊስና በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በጋራ ጥመረት እንደሆነም በመግለጽ የአሽባሪ ቡድኖቹ ኢትዮጵያና በኬያ ድምበር አካባቢ እንደሚንቀሳቀሱን ይህንንም ለመቀልበስ የሁለቱ የጋራ ጥምረት የግድ ስለሆነ ሁለቱ ሀገራት እነዚህ ቡድኖች ካካባቢው ለማጥፋት ወደ ሥራ ሊገቡ እንደሆነ የሚያሳይ ዘገባ ነው። ይህንንም የጋራ የጸጥታ ማስከበር ሥራ ለማፋጠን ኢትዮጵያና ኬንያ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ የመግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም ማቀዳቸውን ማቀዳቸውን ጠቅሶ ስኬቱም በድምበሩ አዋሳኝ አካባቢ ለሚነረው ህበረተሰብ ከፈተኛ እፎይታና የሠላም ተስፋ ሲሆን አልፎ ሀገራዊና አሀጉራዊ ፋይዳ ያለው ሥራ እንደሆነ የሚያመለክት ዘገባ ነው።

ምንጭ – http://www.xinhuanet.com/english/africa/20220216/2a745ee973794cf38d77ec8b3ddfc880/c.html

All Africa 

አሜሪካ በኢትዮጵያን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳትን በደስታ መቀበሏን ነው የሚዘግበው። አሜሪካ በኢትዮጵያን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳትን በደስታ እንደተቀበለችና ይህም በኢትዮጵያ መንግስት የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚወስዳቸው እርምጃዎች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን የሚአያሳይ መሆኑን እንደገለጸች በማንሳት ነገር ግን አሁንም በአዋጁ ጊዜ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ባስቸኳይ እንዲፈቱ ማሳሰቧን ጽፏል። ይህ የሚያሳየ አሜሪካ ግጭቱን ለማረጋጋት የምታደርገው ጠረት የኢትዮጵያን መንግስት የእርምጃ አቅጣጫዎችን በማስቀየር ለህወሓት ያላትን ወገንተኝነት በስውር ለማራመድ እንጂ ለኢትዮያ ሠላምና መረጋጋት እንድሁም ፍትህና ዲሞክራሲ ምንም የሚገዳት እንዳልሆነ የሚገልጽ ጽሁፍ ነው።

በተጨማሪም የህወሓታ ደጋፊዎች የጅምላ እስራት ጯክትን በቀጥታ በመቀበል የኢትዮጵያ መንግስት የተሳካ የብሔራዊ መጋባባት ውይይትን ለማካሄድ የጅምላ እስራቱን ማቆም እንዳለበት በተለመደው ትዕዛዝ መሠል ማሳሰብያዋን መጥቀሷን ነው የጻፈው።

ምንጭ – https://allafrica.com/stories/202202160109.html

Al Monitor

ኢትዮጵያ በግብፅና በሱዳን ላይ የሰነዘረችው ክስ የህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ ያለውን ውዝዝግብ ለመፍታት  ያለውን ተስፋ እንዳዳከመ ነው የጻፈው። በጥር ወር በድርድሩ ዝርያ በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል የነበሩት አወንታዊ ምልክቶች የሁለቱን ሀገራት ልዩነት ለማስወገድ ይቅርና የተቋረጠውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ድርድር እንደገና ለማስቀጠል አለመጥቀሙን ጠቅሶ ይህም ኢትዮጵያ ገብጽንና ሱዳንን የህወሓትን አሸባሪ ቡድን እንደሚደግፉ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሬድዋን ሁሴን የገለጹበት መግለጫ ለዚህ ግንኙነት መሻከር ዋነኛ ምክንያት እንደሆነም ለመግልስጽ ሞክሯል።

አቶ ሬድዋን ሁሴንም ለዚህ ክሳቸው ምንም ማስረጃ እንዳላቀረቡ በመጠቀስ ግብጽን የወነጀሉበት ምክንያት ተገቢ የሚመስል እንዳልሆነ ለማሳየት ሞክሯል። በዚህ ወር በአዲስ አበባ የተካሄደውን የአፍሪካ ህብረትም የአፍሪካን መሪዎች ትኩረት የሳበ እንዳልሆነ በመግለጽ ለዚህ ማሳያው የግብጽ ፕሬዚዳንድት አል ሲሲ በጉባዔው ላይ አለመገኘታቸውን በማንሳት የህብረቱ ጉባኤም የህዳሴ ግድብን ጉዳይ ለማንሳይ አለመቻሉንም ገልጿል። በህዳሴ ግድቡ ድርድር ዙርያም ኢትዮጵያ ሱዳንን ከግብጽ የሚደረግባት ጫና እንዳለም እንዳነሳችና ይህም በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል ጤናማ የንግግር እሳቤ እንዳይኖር እንዳድረገም ለመግለጽ ሞክሯል።

ምንጭ – https://www.al-monitor.com/originals/2022/02/ethiopias-accusations-against-egypt-sudan-dispel-hopes-renaissance-dam-crisis

ማጠቃለያ

   የዛሬ የዓለማቀ ሚድያዎች የዘገባ ውሎ በሀገራችን አራት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ዘገባዎችን ጽፈዋል።  ኢትዮጵያ ጦርነትን በማረጋጋት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዳነሳችና በአዋጁም በመጠቀም ከፈተኛ እስራት በትግራይ ተወላጆች ላይ እንደተፈጸመ የሚገልጽ፣ ቡድኑ ጽረ ህዝብ፣ ጸረ ሀገር እንደሆነ የሚያሳየዉን በኢትዮጵያ ግጭት የትግራይ ታጣቂዎች ሴቶችን እና ልጃገረዶችን በቡድን አስገድደው ደፍረዋል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዘገባ ማውጣቱን ፣ ኢትዮጵያና ኬንያ አልሸባብንና የኦነግ ሸኔን ታጣቂ ቡድኖችን  በጋራ ለመዋጋት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንና ኢትዮጵያ በግብፅና በሱዳን ላይ የሰነዘረችው ክስ ከህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ ያለውን ውዝግብ ለመፍታት  ያለውን ተስፋ እንዳዳከመ የሚገልጹ ዘገባዎች ናቸው።

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *