Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

1 min read

ታኅሳሥ 11፣ | 2015 ዓ.ም – Dec 20 | 2022

Bbc

 • በመንግስት እና በህወሓት መካከል በነበረው ግጭት ህፃናት ላይ ጥቁር ጠባሰ ጥሎ ማለፉን የሚናገር የጸሁፍ ዘገባ ነው ።

የተነሱ ነጥቦች

 • ዘገባው እንደሚለው ሃፍቶም የሚባል ህፃን አምስት ዓመት ሲሆነው እሱም እንደስሙ ሀብታም የሚለው ቃል አሁን ላይ ያለው ሁኔታ እንደማይገልፅው መሆኑን ።
 • በትግራይ ክልል ለሁለት አመታት የዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት የእለት ከእለት የረሃብ እና የምግብ እጦት  እየጨመረ መሆኑን ።
 • በመንግስት እና በህወሓት መካከል የነበረው ግጭት አሁን ላይ የሰላም ስምምነት ቢያገኝም የግጭቱ አሻራ አሁንም እንዳለ ነው ።
 • የመንግስታቱ ድርጅት በትግራይ ውስጥ ከአምስት አመት በታች ከሆኑ ህጻናት መካከል አንዱ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንዳለበት  መገመቱን ።
 • በመንግስት እና በህወሓት መካካል በነበረው ግጭት የመንግስት ባለስልጣናት ወደ ትግራይ ክልል የሚደረገውን እርዳታ በመገደብ እርዳታው ውጤታማ እንዳይሆን አርጎታል ማለቱን ።

       ሊንክ    https://www.bbc.com/news/world-africa-63994851

Voa

 • የኢትዮጵያውያን የሰላማዊ ሰልፍ ተስፋ እና ስጋት በሚል መወያየታቸውን  የሚዘግብ ጹሁፍ ነው ።

የተነሱ ነጥቦች

 • በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደካማ የሰላም ስምምነት ይፈጠር እንደሆነ ለማየት በጉጉት መመልከታቸውን ።
 • በተጨማሪ የዲያስፖራ ቡድን በዋሽንግተን ቪኦኤ ዋና መሥሪያ ቤት የከተማ አዳራሽ ውይይት ለማድረግ መሰብሰቡን ።
 • ኢትዮጵያ የሰላም ጎዳናዎች በቴሌቭዥን የተላለፈው ዝግጅት ከበርካታ ብሔረሰቦች የተውጣጡ አክቲቪስቶችን፣ ምሁራንን እና ሌሎችንም በማሰባሰብ ሀገሪቱን ስላፈራረሰው ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን ግጭት ለመናገገር  ያደረጉት ያልተለመደ አጋጣሚ መሆኑን ።
 •  አሁን ላይ የተደረገው ስብሰባ ተሳታፊዎቹ እንደዚህ አይነት ግልጽ ውይይት በጣም አስፈላጊ ነው ማለታቸውን ።
 • በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ልዩ ባለሙያተኛ የሆኑት ተወያዮቹ  መገሸታቸውን ።
 • ከተወያዮቸሁ አካል አቶ ኤታና ሀብቴ  እንደተናገሩት ከብሔር ክፍፍል አልፈው ለመቀጠል ክርክር እና ግልጽነት ለማግኘት መደራደር አስፈላጊ ነው ማለታቸውን ።
 • አቶ ኤታና እንደሚሉት በአገሪቱ ያለው ችግር በአንድ ወይም በሁለት ቀን ውስጥ የተጀመረ ነገር አለመሆኑን ።
 • በተጨማሪም እንዲ ሲሉ መናገራቸውን በአንድ ቀን ውስጥ የተከሰተው ችግር በአንድ ቀን ውስጥ ሊፈታ  እንደሚችል።
 • ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ችግሮች ከ150 ዓመታት በፊት የተፈጠሩ  መሆናቸውን መናገራቸውን ።
 • መአዛ ገብረመድህን ትግራዋይ አክቲቪስት ተመራማሪ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ከተወያዮቹ አንዷ መሆናቸውን ።
 • በትግራይ ክልል ግጭት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን በማዘጋጀት በሃገሯ ስለተፈጸመው ግፍ መናገሯን ።
 • መአዛ እንደተናገረችው በሎሳንጀለስ በተካሄደው ሰልፍ ላይ አንድ ሰው ሽጉጥ  እንደደቀነባት እና የግድያ ዛቻ  ሊደርስባት እንደነበረ ስብሰባው ላይ ከ ተጠቀሰው አንዱ ነው ።
 •  በተጨማሪም ትላለች በትግራይ ከደረሰው አሰቃቂ ድርጊት ጋር ሲወዳደር ምንም እንዳልሆነ ገርሞኛል ማለቷን ።
 • “ጦርነቱ ምን ያህል መጥፎ እንደሆነ የሰማነው ሳይሆን የኖርነው ነው ስትል  እንደተናገረች ።

  ሊንክ   https://www.voanews.com/a/ethiopians-voice-hopes-and-fears-about-peace-pr

Aljazeera

 • የኢትዮጵያ ትልቁ ባንክ በትግራይ ውስጥ አገልግሎት መጀመሩን የሚናገር  የቪዲዮ ዘገባ ነው ።

የተነሱ ነጥቦች

 • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዓመት በላይ ከተቋረጠ በኋላ በሽሬ አላማጣ እና ኮረም ቅርንጫፎችን መክፈቱን ማስታወቁን  ።
 • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል ግጭት በተከሰተባቸው አንዳንድ ከተሞች የፋይናንስ አገልግሎት መጀመሩን  መገለጹን ።
 • በነበረው ግጭት ምክንያት ከአንድ አመት በላይ በዘለቀው አገልግሎት ነዋሪዎቹ ገንዘባቸውን እንዲያገኙ  ማስቻሉን ።
 • በመንግስት እና በህወሓት መካከል በነበረው ግጭት ምክንያት የትግራይ ክልል ወደ ሰላም ቀጠና ለመመለስ በተደረገው ስምምነት መፈራረም ተከትሎ መሆኑን ነው ።
 • በቅርብ ጊዜ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሽሬ አላማጣ እና ኮረም ከተሞች ያሉን ቅርንጫፎች ከውጭ እና ከሀገር ውስጥ የተላከ ገንዘብ መቀበል እንዲሁም ገንዘብ ማስገባት ጀምረዋል ማለቱን የሀገሪቱ ትልቁ ባንክ በመግለጫው መግለጹን ።
 • ባንካችን በሰሜናዊው የሀገሪቱ ክፍል በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት የባንክ አገልግሎቱን ለማቆም  መገደዱን መግለጫው መግለጹን ።

ሊንክ     https://www.aljazeera.com/news/2022/12/20/ethiopias-biggest-bank-resumes-se

Atalayar

 • ኢትዮጵያ እና ሱዳን በአልፋሻጋ የድንበር ውዝግብ በቁጥጥር ስር የዋሉ 62 እስረኞችን  መለዋወጣቸውን የሚዘግብ ዘገባ ነው

የተነሱ ነጥቦች

 • በ2020 የተቀሰቀሰውን የድንበር ግጭት ለመፍታት 53 የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሃይሎች በሰባት ሱዳናውያን እና በሁለት ሱዳናውያን ወታደሮች ምትክ የተደረገው ልውውጥ በቀይ መስቀል የተደገፈ እንደነበረ ነው።
 • ካርቱም እና አዲስ አበባ በአል-ፋሻጋ የድንበር ውዝግብ ለመታረቅ አንድ እርምጃ ቅርብ መሆናቸውን ።
 • በሰሜን ምስራቅ ሱዳን ውስጥ በነዳጅ ክምችት የበለፀገ እና በህጋዊ መንገድ በካርቱም ቁጥጥር ስር መሆኑን ።
 • ነገር ግን ምንም እንኳን በተግባር የኢትዮጵያ ብሄር ተወላጅ የሆኑ አማሮች የሚኖሩበት በጣም ለም መሬት ያለው ክልል እንደሆነ ።
 • የሱዳን ታጣቂ ሃይሎች እና የኢትዮጵያ አቻቸው አባላት ሁለቱን ሀገራት የ62 እስረኞች ልውውጥ የተደረገ መሆነን ግልፅ መደረጉን ።
 • ሱዳን ከሰኞ ኦፕሬሽን በኋላ የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ስለ ልውውጡ ዝርዝር መግለጫ የሰጠ ሲሆን ፓርቲዎቹ በመገናኘት በአለም አቀፍ ቀይ መስቀል አስተባባሪነት 62ቱን  እንዳስረከበ መናገሩን ገልፆል ።

ሊንክ    https://atalayar.com/en/content/ethiopia-and-sudan-exchange-62-prisoners-captured-

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *