Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ታኅሳሥ 10፣ | 2015 ዓ.ም – Dec 19 | 2022

Foreign Policy

  • አዲሱ ለሺተው በተባለ ግለሠብ የተዘጋጀ የኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት ይጸናል  ወይ የሚል ህሳብ ለማብራራታ የሞከረ ጽሁፍ ነው።

የተነሱ ነጥቦች

  • ያለ ፖለቲካ ማሻሻያ፣ የኢኮኖሚ መረጋጋት እና ተጠያቂነት ስምምነቱ ተግባራዊ ቢሆንም ግጭት እንደገና ሊቀጥል እንደሚችል
  • የተፈረመው የሠላም ስምምነት የተሟላ እንዳልሆነና ኤርትራ መጉዳትን ጨምሮ ኢትዮያንም የክልሉንም ሠላም ለማስጠበቅ የማይችል ስምምነት እድነሆነ
  • አሁን ስምምነቱ የተፈረመ ቢሆንም ብዙ ጥያቄዎች እንደሚቀሩ
  • የኢትዮጵያ የሠላም ስምምነት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ያላለቀ የሪፎርም አጀን መኖሩን እንዳጋለጠ
  • ስምምነቱ ለህወሓት ሁለተኛ ጊዜ  ህይወት እንዲዘራና በወታደራዊ ሃይል ያላገኘውን ድል በፖለቲካዊ መልኩ እንዲያሸንፍ እድል እንደሚሰጥ
  • የሰላም ስምምነቱን ውጤት ለማረጋገጥ የሚቻለው ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ሲኖር ብቻ እደሆነ
  • ስምምነቱ ሲፈረም ብዙሀን ፈጣን መፍትሔ እንደሚያመጣ ጥብቀው እንደነበርነና ይም ሊሆን እንዳልቻለ  የሚገልጹ ዋና ዋና ነጥቦችን የያዘ ነው።

ሊንክ   – https://foreignpolicy.com/2022/12/19/tplf-abiy-ethiopia-peace-deal-last/

 Plenglish

  • የኢትዮጵያ አባይ ግድብ እንዴት አይድሮፓወር ክልላዊ ውህደትን ያጠናክራል የሚል ሀሳብን የተነተነ ነው።

የተነሱ ነጥቦች

  • በህዳሴ ግድብ ዙርያ የኢትዮጵያ የግብጽና የሱዳን ውጥረት እንደቀጠ እንደሆነ
  • የተለያዩ ክልላዊ ተቋማትና ሀገራትም ለመፍትሔው የማወያየት ጥረቶች ቢኖሩም እስካሁን እንዳልተፈታ
  • ግብጽና ሱዳን በውሃ ድርሻዎቻቸውና በግድቡ አስተዳደር ላይ አስገዳጅ ስምምነት እንዲደረግ በሚጠይቁትን አንገብጋቢ ጥያቄ ኢትዮጵያ ዓይኗን በመጨፈን የራሷን መንገድ ብቻ እየተከተለች እንደሆነች
  • ነገር ኢትዮጵያ ማንንም የመጉዳት ዓላማ እንዳላት በተደጋጋሚ ስትገልጽ እንደነበር
  • በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ከሀገራቸው ልማት በተጨማሪ የጥቁር አባይ ወንዝ የአፍሪካ ቀንድን አጠቃላይ ፍላጎት የሚሸፍን ግዙፍ ሃይል የተፈጥሮ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል እና በዚህም በቀጠናው ያለውን የባለብዙ ወገን ትብብር እንደሚያጎለብት ደጋግሞ መግለጹ
  • ኢትዮጵያ በክርክር ላይ ባለው ግድብ የግንባታ ሂደቱን በማቀላጠፍ የሀይል ኤክስፖርት ንግድ መጀመሯን የሚገልጹ ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው።

ሊንክ    – https://www.plenglish.com/news/2022/12/16/ethiopia-and-saudi-arabia-to-expand-coope

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *