የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ታኅሳሥ 4፣ | 2015 ዓ.ም – Dec 13 | 2022
Aljazeera
- መሀሪ ታደለ በተባለ ግለሠብ የቀረበ በኢትዮጵያ በሰላም ስምምነት ሽፋን ፍትህ መጥፋት የለበትም የሚል ሀሳብ የሚያንጸባርቅ ሪፖርት ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- በኢትዮጵያ ውስጥ የጦር ወንጀለኞችን ተጠያቂ ማድረግ የሀገሪቱን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ እንዳሆነ
- የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሀት) መካከል በፕሪቶሪያ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በአንድ ድምፅ እንደተቀበለው
- ነገር ግን ስምምነቱ አወንታዊ እርምጃ ቢሆንም፣ ተኩስን ለማስቆም ያለመ ቢሆንም ስምምነቱ አንዳንድ ከባድ ጥያቄዎች እንደሚቀሩ
- በተለይም በትግራይ ለተፈፀሙት የጦር ወንጀሎች እና በሰው ልጆች ላይ ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ጉዳይ ትኩረት እንዳላገኘ
- ሆኖም የሰላም ስምምነቱ ፍትሕ ለሚሹ በጥቃቱ ሰለባ ለሆኑት ብዙም እንዳልጠቀመ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://www.aljazeera.com/opinions/2022/12/13/justice-in-ethiopia-must-not-be-
Ahram Online
- በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት እየተባባሰ እንደሆነ ነገር ግን የሠራተኞች ደሞዝ እንዳልጨምረና ሀገሪቷን እንዳስጨነቃት የሚተነትን ነው።
የተነሱነጥቦች
- “ከደመወዛችን በስተቀር ሁሉም ነገር እየጨመረ ነው” በሚል የአንድ ሪፖርተር ግለሠብ ሀሳብ ለAFP በሰጠው ሀሳብ እደቀረበ
- የአፍሪካ ቀንድ አገር እያሽቆለቆለ ካለው የዋጋ ንረት እና የኢኮኖሚ ውድቀትን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከፈተኛ ውጥረት ውስጥ መግባቷ
- ከሸቀጦች በተለይ ምግብ ላይ እየታየ ያለው የዋጋ ንረት ከፍተኛ እንደሆነ
- ለዚህ አነድኛ ምክንያት በኢትዮጵያ የነበረው ጥርነት ጫና እንደሆነ የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው
ሊንክ – https://english.ahram.org.eg/News/482493.aspx