የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ሕዳር 12፣ | 2015 ዓ.ም – Nov 21 | 2022
Sudan Tribune
- የሱዳንና የኢትዮጵያ የስለላ ኤጀንሲዎች ትብብርን ለማጠናከር ተስማሙ በሚል ርዕስ የሁለቱን ሀገራት የደህንነት ተቋማት ለጋራ ሥራ ማጠናከርያ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ዙርያ የተጻፈ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የሁለቱ ሀገራት የድህንነት ተቋማት የተፈራረሙት በጋራ በሚደረገው የሽብርተኝነትን መዋጋት ሥራን በተጠናከረ መልኩ ለመሥራት እንደሆነ
- ሁለቱ ወገኖች በጋራ ስልጠናና ልምድ ልውውጥ ዙሪያ በትብብር ለመስራት፣ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት፣ የተደራጁ ወንጀሎችን እና ጊዜያዊ ኢኮኖሚያዊ ወንጀሎችን በጋራ ለመስራት እና የሁለቱን ሀገራት ዜጎች ጉዳይ ለመፍታት እንደተስማሙ
- ኢትዮጵያ ካርቱምን ወያኔን እንደምትደግፍና በምስራቅ ሱዳን በሚገኙ የስደተኛ ካምፖች ውስጥ እንዲጠለሉ ፈቅዳለች በማለት ስትከስ እንደነበር።
ሊንክ – https://sudantribune.com/article267068/
Xinhua
- በቻይና የተደገፈ የሳይንስ ሙዚየም በኢትዮጵያ የሳይንስ ወዳጆችን ልብ አሸንፏል ይላል።
የተነሱ ነጥቦች
- ሙዝየሙ በዓይነቱ ከአፍሪካ የመጀመርያው እንደሆነና ብዙ አድናቆትን ያተረፈ እንደሆነ
- በጥቂት ሳምንታት ብዙ ጎብኚዎች ያስተናገደ እንደሆነ
- ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ሙዚየሙ ከጥቅምት 4 ቀን ጀምሮ በይፋ ከተከፈተ በኋላ ከ700,000 በላይ የሳይንስ ጎብኚዎች ከኢትዮጵያ እና ከሱዳን እንደጎበኙት
- ሙዝየሙ የኢትዮጵያን እድገትና ልማት የሚደግፉ ሳይንሳዊ ፈጠራዎች የሚታሰቡበት እና የሚወለዱበት መድረክ ሆኖ ያገለግላል ተብሎ እንደሚጠበቅ
- የሳይንስ ሙዚየሙ በቻይና የተደገፈ የአዲስ አበባ ወንዝ ዳር አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ምዕራፍ ሁለት ዋና አካል እንደሆነ
ሊንክ – https://english.news.cn/20221121/5f2a44a607b447799881c93cf218509b/c.html