የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ሕዳር 7፣ | 2015 ዓ.ም – Nov 16 | 2022
Reuters
- ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በኋላ የመጀመርያው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ኮንቮይ ወደ ኢትዮጵያ ትግራይ እንደገባ የተጻፈ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- ዛሬ እሮብ ጥቅምት 07 15 የተመድ የእርዳታ ኮንቮይ ወደ ኢትዮጵያ ትግራይ መግባቱ
- ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በኋላ ዝግይቶ ዛሬ ገና መግባቱ
- እርዳታው ከጦርነቱ መጀመር በኋላ መጠቀም በተተወው የአማራ ክልል የጎንደር ኮሪደር መንገድን በመጠቀም መግባት እንደጀመረ
- ከነሐሴ ወር ጀምሮ የትግራይ ክልል ምንም ዓይነት ዓለማቀፍ እርዳታ እንዳልደረሰው
- የአማራና የትግራይ ክልልም የድንበር ውዝግብም በህግ አግባብ እንደሚፈታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ መናገራቸው
- በተጨማሪም የአሜሪካ መንግስት የስምምነቱን ተግባራዊነት በማይፈጽሙት ላይ ማዕብ ለመጣል እንደተዘጋጀች ነው የተጻፈው።
- ለሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም ተጠያቂ የሚሆኑትን አካላት እንዲጠየቁ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነች።
- ይህ ደግሞ ከኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ መውጣት እንዲተገበር በቀጥታ ጫና ለማድረግ ያለመ እንደሆነ የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ 1 – https://www.reuters.com/world/africa/first-un-aid-convoy-since-ceasefire-e
ሊንክ 2 – https://www.reuters.com/world/africa/us-will-not-hesitate-use-sanctions-ensur
Aljazeera
- የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አብይ የትግራይን ስምምነቱን በታማኝነት ተግባራዊ ለማድረግ ቈጠኛ እንደሆኑ ነው የተጻፈው።
የተነሱ ነጥቦች
- በስምምነቱ አፈጻጸም መሠረት ሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንደሚገባና የህወሓት ታታቂዎች ትጥቅ ይፈታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ
- ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ ተጨማሪ ስምምነትም ጭምር መፈራረማቸው
- በስምምነቱ መሠረት ሁለቱማ አካላት ያልተገደበ የእርዳታ መግብታ ላይ መስማማታቸው
- የትጥቅ መፍታቱ ጉዳይም ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ውጭ ሌሎች ታጣቂ ሀይሎች ከክልሉ ለቀው ከወጡ በኋላ እንደሆነ እንደተስማሙ የሚገልጹት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://www.reuters.com/world/africa/us-will-not-hesitate-use-sanctions-ensure-ethiop
DW
- የኢትዮጵያው የትግራይ ክልል እርዳታ መቀበል እንደጀመረ የተጻፈ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በኋላ የመጀመርያ እርዳታ ጫኝ ተሸክርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባታቸው
- ሁለት የጭነት መኪናዎች የህክምና ቁሳቁሶችን፣ የአደጋ ጊዜ መድሃኒቶችን እና የቀዶ ህክምና መሳሪያዎችን የታጨቁበት ማክሰኞ ከሰአት በኋላ በትግራይ ዋና ሆስፒታል መግባታቸውን የአለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ እንዳሳወቀ።
- ተጨማሪ የነፍስ አድን የእርዳታ አቅርቦቶች ታሽገው በጭነት መኪና እና በአውሮፕላን ወደ ጦርነት ወደ ክልል በተቻለ ፍጥነት ለመንቀሳቀስ ዝግጁ መሆናቸውን አይሲአርሲ መግለጹ
- ሌሎች አለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶችም የፀጥታ እና የጽዳት ሂደቱን ለማጠናቀቅ እየጠበቁ መሆናቸው
ሊንክ – https://www.dw.com/en/ethiopia-tigray-starts-to-receive-desperately-needed-