Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

መስከረም 27፣ | 2015 ዓ.ም – Oct 7 | 2022

Reuters

  • የኢትዮጵያ የሰላም ድርድር በሎጂስቲክስ ምክንያት መዘግየቱን ዲፕሎማቶች እንደተናገሩ ይገልጻል

የተነሱ ነጥቦች

  • ለመደራደር ሁለቱም አካላት የተስማሙ እንደሆኑ
  • ድርድሩ መራዘሙን የተናገሩት አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ ያለተፈለገው ዲፕሎማት እንደሆኑ
  • የድርድሩን መራዘም በተመለከተ ሌላ ምክንያት እንዳለ ካለ ሲጠየቅ ግን ሁሉም አካላት ምላሽ እንዳልሰጡ በመግለጽ ለሎጂስቲች እንደሆነ የተራዘምው አጠራጣሪ መሆኑን ጽፏል።

ሊንክ   https://www.reuters.com/world/africa/ethiopia-peace-talks-delayed-logistical-reasons-dip/

Yahoo News

  • በኢትዮጵያ ግጭት የሰላም ድርድር መጓተቱን ዲፕሎማቶች መግለጻቸውን የሚያስረዳ ነው።

የተነሱነጥቦች

  • በአፍሪካ ህብረት የተደገፈው የሠላም ድርድር የኢትዮጵያን የትግራይ ግጭት ለመፍታት በታቀደው መሰረት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ለመካሄድ የታቀደ ቢሆንም እንደማይካሄድ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ለአሶሼትድ ፕሬስ አርብ ዕለት ተናግረዋል።
  • የኢትዮጵያ መንግስትም በአፍሪካ ህብረት በኩል የቀረበለትን የድርድሩን ሀሳብ መቀበሉ
  • የሽብር ቡድኑ ህወሓት አመራርም ተደራዳሪዎችን ለመላክ መዘጋጀታቸውን ቢገልጹም የውይይቱን አወቃቀር በተመለከተ ግልጽ መረጃ እንዲሰጣቸው እንደጠየቁና ከዚህ ቀደም የዓለማ አካላት በታዛቢነት እንዲሳተፉም እንደጠየቁ ሁሉ አሁንም አጥብቀው እንደጠየቁ እንዲሁም ወደ ድርድሩ ቦታ ሲሄዱ  ለጉዟቸው የደህንነት ማረጋገጫ እንዲሠጣቸው ጭምር እንደጠየቁ
  •  በጉዳዩ ላይ በይፋ ለመገር ስላልተፈቀደላቸው ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት የዲፕሎማቲክ ምንጮቹ የሎጂስቲክስ ጉዳዮች ለመዘግየቱ በከፊል ተጠያቂ እንደሆኑ መግለጻቸው።
  • የድርድሩ ፎርማትም ሆነ የተቆረጠ አዲ ቀንም እንደሌለ
  • ኤርትራን ጨምሮ በኢትዮጵያ ጎረቤት ያሉ አካላትም በጦርነቱ እንደተሳተፉ የተገለጽ እንደሚገኝ

ሊንክ – https://www.yahoo.com/news/peace-talks-ethiopian-conflict-delayed-113249532.html

Aljazeera

  • የኬንያው ፕሬዝዳንት ሩቶ ለሁለትዮሽ ጉዳዮች ኢትዮጵያን እንደጎበኙ ያብራራል።

  የተነሱ ነጥቦች

  •  ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ የመጀመርያቸው የሆነውን  ጉብኝት እንዳደረጉ
  • ኢትዮጵያ እና ኬንያ የረጅም ጊዜ ወዳጅነት እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ትብብር ያላቸው ሀገራት መሆናቸው።
  • ፕሬዝዳንት ሩቶ በመንግስትና ህወሓት መካክል መካከል የሚካሄደውን የሰላም ድርድር በመምራት ረገድ አስተዳደራቸው ንቁ ሚና እንደሚጫወት አስቀድመው አረጋግጠው እንደነበር።

ሊንክ https://www.africanews.com/2022/10/07/kenyas-president-ruto-visits-ethiopia-for-meeting/

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *