የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
መስከረም 25፣ | 2015 ዓ.ም – Oct 5 | 2022
Reuters
- የአፍሪካ ህብረት የፌደራል መንግስት እና የህወሓት ሀይሎች ወደ ሰላም ድርድር እንዲመጡ መጋበዙን የሚተነትን ዘገባ ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ሃይሎችን ወደ ሰላም እንዲመጡ መጋበዙን ።
- ጦርነቱ ለሁለት አመታት የቆየውን ግጭት ለማስቆም በደቡብ አፍሪካ የሰላም ድርድር እንዲያደርጉ ጋብዟል ሲል ሮይተርስ በላከው ደብዳቤ ማስታወቁን ።
- በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ለህወሓት ሀይል ለሆኑት ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የጻፉት ደብዳቤ ትክክለኛነቱን ።
- ደብዳቤው እንደተፃፈላቸው የተነገሩት ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ሦስት የዲፕሎማቲክ ምንጮች ማረጋገጣቀቸውን ።
- ደብዳቤ እንደሚያሳየው ለኢትዮጵያ መንግስት እና ለህወሓት መላኩን እንደሚያመለክት ነው ።
- ምንጮቹ እንደሚያመለክተት ሁለቱም ወገኖች ግን እስካሁን የትኛውም ወገን መሳተፉን አላረጋገጠም ማለታቸውን ።
- የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ሀይል ጦርነቱ ከተነሳ ጀምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎችን መገደላቸውን
- መንግስት እና ህወሓት ጦርነት ለማስቆም በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ማስታወቃቸውን ።
- ነገር ግን አሁንም ለአምስት ወራት በዘለቀው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ምንም አይነት መደበኛ ውይይት አልተካሄደም እና አሁንም በትግራይ ከባድ ውጊያ መቀጠሉን ።
ሊንክ https://www.reuters.com/world/africa/african-union-invites-ethiopias-warring-parties-peace-
news24
- በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት ለማስቆም ኤስኤ እና ዩኤስ እንዴት በጋራ መስራት እንዳለባቸው የሚል ጹሁፍ ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በዚህ ወር ወደ ኤስኤ መምጣታቸውን ።
- ኤስኤ በኢትዮጵያ ሞዛምቢክ እና ዚምባብዌ ላሉ ቀውሶች መፍትሄ በማፈላለግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ መጠበቁን ።
- ሀመር ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ጋር በኢትዮጵያ እንደሚገናኙ ።
- በትግራይ ክልል በአፍሪካ ህብረት የሚመራው የሰላም ውጥን ደቡብ አፍሪካ የካሜኦ ሚና ብቻ ሊኖራት እንደሚችል ።
- በአሜሪካ ደቡብ አፍሪካ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች የስራ ቡድን በዋሽንግተን ዲሲ ስብሰባ ላይ መገናኘታቸውን
- አሜሪካና ደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያ ያለው ጦርነት ላይ ምክክር ማድረጋቸውን ።
ሊንክ https://www.news24.com/news24/africa/news/how-sa-and-us-are-working-together-to
Africa news
- የፌደራል መንግስት ከህወሓት ሀይሎችጋር የሰላም ድርድር ለማድረግ መስማማቱን የሚዘግብ ዘገባ ነው
የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ መንግስት በህወሓት ሀይል ጋር ከሚገኙ ታጣቂዎች ጋር ቀንና ቦታ ሳይገልጽ ከአፍሪካ ህብረት የቀረበለትን የሰላም ድርድር መቀበሉን ማስታወቁን ።
- የአፍሪካ ህብረት ለመንግስት እና ለህወሓት ሀይል የሰላም ድርድር ግብዣ መላኩን ።
- የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን ግብዣ መቀበሉን እናግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ድርድር እንደሚያስፈልግ በሚለው መርህ መሰረት መሆኑን ነው። የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ በትዊተር ገፃቸው ላይ መናገራቸውን ።
- የኢትዮጵያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በላከው መግለጫ የአፍሪካ ህብረት በግብዣው ቀን እና የውይይቱ ቦታ ቢገለጽም ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።
- ከኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ የሚገኘው የህወሓት አማፂ ባለስልጣናት ስለግብዣው ጉዳይ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተጠይቀው ወዲያውኑ ምላሽ አለመስጠታቸውን ።
- ዝርዝሩን በተገቢው ከፓርቲዎቹ ጋር በመመካከር እናሳውቃለን ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ቃል አቀባይ ኤባ ካሎንዶ መናገራቸውን ።
- የህወሓት ሀይል መሪው ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በህወሓት እና በኢትዮጵያ መካከል ሊደረግ በታቀደው ውይይት ላይ ቢገኝ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጦርነት ለማስቆም የተደረገው ከፍተኛ ጥረት ሊሆን እንደሚችል ነው።
ሊንክ https://www.africanews.com/2022/10/05/ethiopia-agrees-to-peace-talks-with-tigrayan-rebels/