የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
መስከረም 15፣ | 2015 ዓ.ም – SEP 25 | 2022
Voa
- በትግራይ ክልል ባለው ጦርነት ለህፃናት ሊሰጥ የነበረውን ክትባቶችን እንደተስተጎጎሉ የሚተነትን ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- በትግራይ ክልል እንደ ኩፍኝ ቴታነስ እና ደረቅ ሳል ያሉ ገዳይ በሽታዎች እየተበራከቱ መሆናቸውን ።
- የእርስ በእርስ ጦርነት መባባሱን የክትባት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ማድረጉን ።
- ከዚህ በፊት ሲሰጥ የነበረው የህጻናት ክትባት አስር በመቶ መውረዱን ከትግራይ ጤና ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳይ ።
- የክትባቱን መጠን ለመጨመር ለዓመታት ያደረገውን ጥረት በጦርነቱ ምክንያት ውድቅ እንዳደረገው ።
- ለአለም አቀፍ የክትባት ቡድን ጋቪ በፃፈው ደብዳቤ በጦርነቱ ምክንያት ህፃናት ጤናማ እና ደስተኛ እንዲሆኑ የነበራቸው ተስፋ እንደጨለመ መፃፉን ።
- በደብዳቤው ላይ በኢትዮጵያ መንግስት ታጣቂዎች በትግራይ ላይ ያደረሱት ጥቃት የአቅርቦት እጥረት መኖሩ የክትባት መጠኑን እንዲቀንስ አድርጓል ብሏል።
- የትግራይ ኤጀንሲም የመብራት መቆራረጥ የክትባት አቅርቦት ሰንሰለት መቋረጡን መናገራቸውን ።
- ኤጀንሲው አክሎም በገጠር የሚኖሩ ሰዎች ወደ ጤና ጣቢያዎች ለመድረስ አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ።
- ጦርነቱ እንደገና ከተጀመረ ወዲህ የሰብአዊ መብት ተደራሽነት ተቋርጧል ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች መናገራቸውን ።
ሊንክ https://learningenglish.voanews.com/a/deadly-diseases-rise-as-war-limits-vaccinations-in-
Sudan tribune
- የግብፅ መንግስት አል ሲሲ ስለ አባይ ግድብ ጉዳይ መወያየታቸውን የሚተነትን ዘገባ ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- የግብፅ ፕሬዝዳንት እና የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ በሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጠናዊ ጉዳዩች ላይ በግብፅ መወያየታቸውን ።
- አብደልፈታህ አል-ቡርሃን ከኒውዮርክ ወደ ካርቱም ሲመለሱ ግብፅ ገብተው ከ አብዱልፈታህ አልሲሲጋር መነጋገራቸውን ።
- የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ደህንነት እና ወታደራዊ ትብብር እንዲሁም በንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ መወያየታቸውን ።
- የግብፅ ፕሬዝዳንት ከውይይቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ የሁለቱን ወንድማማች አገሮች በፀጥታ፣ በወታደራዊ፣ በኢኮኖሚ እና በንግድ ደረጃ ያለውን ጥቅም ለማስከበር አስተዋፅዖ በሚያደርግ መልኩ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚፈልጉ አልሲሲ መግለፃቸውን ።
- የግብፅ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ በበኩላቸው ስብሰባው የህዳሴውን ግድብ ጨምሮ በጋራ ጥቅም ላይ በሚውሉ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የተከሰቱትን የቅርብ ጊዜ ለውጦች መገምገሙን ።
- በተጨማሪም በዚህ ረገድ በሚቀጥሉት ጊዜያት የተጠናከረ ምክክር እና የጋራ ትብብር ለመቀጠል ተስማምተዋል ሲል በአጽኖት ማስቀመጡን ።
ሊንክ https://sudantribune.com/article264506/
The east African
- የኤርትራ አዲስ ብጥብጥ የተበሳጨው የህወሓት ሀይል የሚል ትንተና ነው
የተነሱ ነጥቦች
- የመንግስት እና የህወሓት ግጭት አስታራቂዎች ለማስታረቅ የማይችሉበትን ሁኔታ መሆናቸውን እንዳስከፋቸው መግለፃቸውን ።
- በመንግስት እና በህወሓተ መካከል ያለውን በሰላማዊ መንገድ ምንም አይነት መፍትሄ እንደሌላው የሚያሳይ ነው ።
- የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በሚዲያ ገለጻ ላይ እንደተናገሩት ሁለቱም ፓርቲዎች በምን ያህል ፍጥነት ትጥቃቸውን እንደሚያስቀምጡ እርግጠኛ እንዳልሆኑ ነው ።
- ኢትዮጵያ በትግራይ ያለውን ጦርነት እንድታቆም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ከአፍሪካ ህብረት ጋር እየሰራ መሆኑን ሚስተር ሀመር መናገራቸውን ።
- የኤርትራ መንግስት አሁን ላይ በትግራይ አካባቢዎችን እየወረሩ መሆኑን እና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ሙሉ በሙሉ እያወገዘች እንዳለ
- በተጨማሪ የኤርትራ መንግስት ባለፈው አምት ላይ የትግራይን ክልል ለቆ እንዲወጣ ግፊት እንደተደረገበት ።
ሊንክ https://www.theeastafrican.co.ke/tea/rest-of-africa/mediators-in-addis-tigray-conflict-by-n