የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
መስከረም 9፣ | 2015 ዓ.ም – SEP 19 | 2022
Aljazeera
- የኢትዮጵያን የሰላም ሂደት ያቆመው ምንድን ነው የሚል ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- በፌዴራል መንግስት እና በህወሓት ታጣቂዎች መካከል ጦርነት መቀስቀሱን ።
- ጦርነቱ ለአምስት ወራት የቆየውን የተኩስ አቁም ስምምነት ካቆመ በኋላ እስከ አዲሱ አመት ምንም አይነት ለውጥ አለመታየቱን ።
- ባለፈው በመቀሌ ከተማ የአየር ጥቃት እንደደረሰና በጥቃቱ አስር ሰዎች መሞታቸውን ።
- በጥቃቱ አሁንም ብዙ ሰዎች እየሞቱ እና እየቆሰሉ እንደሆነ የሚያሳይ ለ መሆኑን ።
- የህወሓት ሀይሎች እና የኢትዮጵያ መንግስት ለተፈጠረው ግጭት እርስበርስ ተጠያቂ መደራረጋቸውን ።
- ጦርነቱ በከባድ ውጊያ ውስጥ እንደሆነና አሁን ላይ የሰላም ተስፋዎችን አደጋ ላይ መጣሉን ።
- በመቀሌ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ሀኪም ዶክተር ፋሲካ አምደስስላሴ ለአልጀዚራ እንደተናገሩት የሞቱት ሰዎች እና የቆሰሉት ቁጥራቸው እይጨመረ መሆኑን ።
ሊንክ https://www.aljazeera.com/news/2022/9/18/what-stagnated-the-ethiopia-peace-process
Alaraby
- ኤርትራ በጦርነቱ ኢትዮጵያን ለመርዳት ወታደሮቿን ወደ ኢትዮጵያ እየላከች እንደሆነ አክቲቪስቶች እና የአለም አቀፍ ማህበረሠብ መሪዎች እየገለጹ እንደሆነ የተጻፈ ነው።
የተነሱ ነጠቦች
- ኤርትራ ታጣቂ ኃይሏን እያሰባሰበችና ወደ ኢትዮጵያ እየላከች እንደሆነ።
- ኤርትራ ጦር ወደ ጎሮቤት ትግራይ ጦርነት ለተጎዱ ሰዎች ለመርዳት ነው ሲሉ አክቲቪስቶችና አለማቀፍ ባለስልጣናት መግለፃቸውን ።
- የኤርትራ የመብት ተሟጋች ሜሮን እስጢፋኖስ ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደተናገረችው ወደ ትግራይ ክልል የተላኩ ኤርትራዊያን ድምፃቸው እየተሰማ እንዳልሆነ ።
- የኤርትራ የስደተኞች መብት ተነሳሽነት ዳይሬክተር ሜሮን እንደገለፀችው ክልላችን ለትውልድ በቂ ደም እንዳይኖረው ሁሉ ይህ አሳዛኝ ጦርነት እንደሆነ መናገሯን ።
- በኤርትራ የሚገኙ የአይን እማኞች እንደተናገሩት ተማሪዎችን እና የመንግስት ሰራተኞችን ጨምሮ ሰዎች በመላ አገሪቱ እየተለቀሙ ወደ ሰራዊቱ እንደሚገቡ ።
- ኤርትራ ከአለም ገለልተኛ ከሆኑ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኤርትራ እድሜያቸው ከ18 እስከ 40 ዓመት ለሆኑ ዜጎቿ ወታደራዊ አገልግሎትለ እንደምትሰጥ ።
ሊንክ https://english.alaraby.co.uk/news/tigray-eritrea-appears-be-sending-soldiers-ethiopia