የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ጳጉሜ 5፣ | 2014 ዓ.ም – SEP 10 | 2022
Africa news
- የህወሓት ሀይሎች ሁኔታዊ እርቅ ማቅረባቸውን የሚመለከት ዘገባ ።
የተነሱ ነጥቦች
- በህወሓት ሀይሎች እና በመንግስት ደጋፊ ሃይሎች መካከል ውጊያው እየተጠናከረ በመምጣቱን ።
- በትግራይ ሰብአዊ እርዳታ በመቋረጡ የህወሓት ሀይሎች ቅድመ ሁኔታ ስምምነት ማድረጋቸውን የህወሓት ቃል አቀባይ አርብ መናገራቸውን
- የነበረው እርቅ ለአምስት ወራት የነበረው ቆይታ አሁን ላይ ጦርነት እርቅ ማብቃቱ ።
- የህወሓት መሪ ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በላኩት ደብዳቤ ትግሉ በተለያዩ ግንባሮች እየተባባሰ በመምጣቱ ጦርነቱ በቅድመ ሁኔታ እንዲቆም መጠየቃቸውን ።
- በአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የተገኘ እና የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የተረጋገጠው በዚህ ደብዳቤ ላይ የእርቅ ሰላሙ በተለይ ያልተደናቀፈ ሰብአዊ አቅርቦት እና በትግራይ ክልል አስፈላጊ አገልግሎቶችን መመለስ ላይ የተመሰረተ ነው ማለታቸውን ።
- በትግራይ ክልል ከሌላው የሀገሪቱ ክፍል ተቆርጦ የኤሌክትሪክ የቴሌኮሙኒኬሽን መረቦች የባንክ አገልግሎት እና ነዳጅ መነፈጋቸውን ።
ሊንክ https://www.africanews.com/2022/09/09/ethiopia-tigray-rebels-offer-conditional-truce/
Stratfor
- በመንግስት እና በህወሓት መካከል ዳግም ጦርነት መቀስቀሱን እና ጦርነቱ ቀጣይ ምን ይዞ ይመጣል የሚል ትንታኔ ።
የተነሱ ነጥቦች
- በመንግስት እና በህወሓት ሀይሎች መካከል ያገረሸው ጦርነት
- ጦርነቱ ቢያንስ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የሚቀጥል መሆኑን
- ጦርነቱ የተኩስ አቁም ድርደሩ የሚያወሳስበው እና በጦርነት በምትታመሰው ሀገሪቱ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ማባባሱን ።
- በመንግስት መከላከያ ሰራዊት እና በህወሀት መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ መቀዛቀዙን
- የመንግስት ወታደሮች እና የህወሓት ሀይሎች ከአምስት ወራት በፊት የተስማሙበት ሰብአዊ እርቅ መፍረሱን ።
- ሁለቱም ሀይሎች ለሁለት አመት የሚጠጋ ጦርነት ማካሄዳቸውን ቢታወቅም አሁን ላይ የህወሓት ሀይል ግን የሰው ሃይል የመሳሪያ የስለላ እና የሀብት እጥረቶችን እንደገጠማቸው ።
- ይህ ሁሉ ጦርነት የሚያሳየው የኢትዮጵያ መንግስት በህወሓት ሀይል ላይ የመንግስት ቁጥጥር ለማድረግ እና ህወሓት ራሱን የቻለ ክልል እና መንግስት መጠየቁን ነው ።
ሊንክ https://worldview.stratfor.com/article/whats-next-ethiopias-civil-war-amid-renewed-fighting-