የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ጳጉሜ 4፣ | 2014 ዓ.ም – SEP 9 | 2022
VOA
- የኦሮሚያ እና የአማራ ብጥብጥ የኢትዮጵያን ጦርነት እንዳያሰፋፋ ስጋት ሆነ የሚል ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ስንበቴ ከተማ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችና በአማራ ክልል የጸጥታ አካላታ ጋር ውግያ መክፈታቸው
- በቅርቡ በሸዋ ሮቢትም ተመሣሣይ የጸጥታ ችግሮች ሲፈጠሩ እንደነበር
- በግጭቱ ከባድ መሣርያዎችም በትኩሱ ልውውጥ እንደተጠቀሙ ጭምር ያነሳል።
- በተለያዩ ቦታዎች በሚፈጠሩ የኦሮሞና አማራ ብሔር ተወላጆች ግጭት ሁሉ ቦታዎች የኢነግ ሸኔ የሸብር ቡንድ እጅ እንዳለበት መገለጹ
ሊንክ https://www.voanews.com/a/analysts-oromia-violence-threatens-to-widen-ethiopia-s-war-
France24
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጦርነቱ እየተባባሰ በመምጣቱ ለኢትዮጵያ ትግራይ የሚሰጠው እርዳታ ቆሟል በማለት የህወሓትን የግጭት ቀስቃሽነትን ተግባርን ወደ ጎን የተወ ጽሁፍ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- ጦርንቱ በሁሉቱም ወገን መጀመሩንና ይህም እርዳታን ለትግራይ ክልል ለማስገባት አስቸጋሪ እንዳደረገው
- የመጨረሻው የርዳታ ኮንቮይ ከ17 ቀናት በፊት በጓጓኡን መቋረጡ
- ጦርነቱ በድንበር አካባቢ ተባብሶ እንዳለና በኤርትራ በኩልም የኤርትራ ጦር የአዲግራትን ከተማ በከባድ መሣርያ ማጥቃት መጀመሩን ዲፕሎማቲክ መረጃዎች አሉ መባሉ
- ግጭቱን መልሶ ለማስቆም የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀማር እንደሚመጡ እንደተነገረና የአውሮፓ ህብረት መልዕክተኛ አኒት ዌበርም ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ እንደሚጠበቁ
ሊንክ – www.france24.com/en/live-news/20220908-aid-halted-to-ethiopia-s-tigray-un-says-as-f
AL MONITOR
- ግብፅ ኢትዮጵያ ከኡጋንዳ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደናቀፍ ቆርጣለች ይላል።
የተነሱ ነጥቦች
- ካይሮ በኡጋንዳና በኢትዮጵያ ጥምረት ላይ በተለይም በአባይ ግድብ ጉዳይ ላይ ጫና ለማድረስ ሁጋንዳ የምግብ ዋስትናን እንድታገኝ ልትረዳት እንደሆነ
- ግብፅም ሆነች ሱዳን በ2010 የተፈረመውን ስምምነት ውድቅ በማድረግ ግብፅ ወደ ናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ መመለሳቸው።
- ግብፅ በምግብ ዋስትና ላይ በመተባበር ከኡጋንዳ ጋር በመቀራረብ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥምረት ለማፍረስ እየሰራች መሆኗ
- ግብፅ የኡጋንዳና የኢትዮጵያን ጥምረት ለመፍረስ ለዓመታት እንደሠራች።
- ግብፅ ሽብርተኝነትን እና ሌሎች ወንጀሎችን ለመዋጋት ከኡጋንዳ ጋር የወታደራዊ የመረጃ ትብብር ስምምነትን በ2021 እንዳጠናቀቀች።
ሊንክ – https://www.al-monitor.com/originals/2022/08/egypt-determined-disrupt-ethiopias-ties-uganda