የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ነሐሴ 23 ፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 29 |2022
The Gurdian
- በትግራይ የሰሞኑን ጦርነት የቀሰቀሠው ምክንያት በሚል ለመተንተን የሞከረ ጽሁፍ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- በሁለቱም ወገን በጦርነት እርስ በእርስ ያለመተማመንና የመወቃቀስ ሁኔታዎች የመጀመርያ ምክንያት እንደሆነ
- ለወራት የቆየው የነበረው የተኩሥ አቁም ሁኔታ የሠላም ተስፋ እንዲታይ አድርጎ እንደነበርና ይህ ጦርነት ያን ተስፋ ያጨለመ እንደሆነ
- በጦርነቱ የተጓተተውን የሠላም ድርድር ችግሮችን የሚፈታ እንዳልሆነ
- ምንም ያህል ግጭቱ ቢቀጥል ለሠላም መስፈን መፍትሔ የማይሆን እንደሆነ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው
ሊንክ – https://www.theguardian.com/world/2022/aug/27/ethiopia-airstrike-hits-playground-in-tigray-
Egypt independent
- የመንግስት ሃይሎች እና የህወሀት ሀይሎች ሲጋጩ በኢትዮጵያ ለተኩስ አቁም የነበረው ቁርጥኝነት መሸርሸሩን የሚተነትን ነው።
የተነሱነጥቦች
- ለወራት በነበረው የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንደፈረሠ የሚያመላክት ግጭት በአዲስ መልክ መቀስቀሱ
- በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለቱም ወገኖች ለጥቃቱ ሌላኛውን ወገን በግጭት ቀስቃሸንነት ተጠያቂ ማድረጋቸው ።
- የህወሀት ሀይል ረቡዕ በፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ መንግስት ጥቃቱን ጀመርኩ ያለው ጥቃቱን ፈጽሟል ካለ በኋላ የህወሓት ሀይሎችን እንደከሰሰ እና የቶክስ አቁሙን እንዳቋረጠ
- የመንግስት ሃይሎች በደቡብ ትግራይ “ማጥቃት” እንደከፈቱ ያም በአማራ ልዩ ሃይል እና ሌሎች የኢትዮጵያ ሀይሎች እንደሚታገዝ መናገሩ።
- ከጦርንነቱ ዳግም መቀስቀስ በፊት በመንግስትም ሆን ህወሀት በግልጽ የሚታይ የሰላም ድርድር ፍላጎት አሳይተው እንደነበር ።
- ነገር ግን ሁለቱ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ተቃራኒ መግለጫዎችን ማውጣታቸውን ተከትሎ አሁን ላይ ያለው ግጭት ላይ መሆናቸው የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው
ሊንክ https://www.egyptindependent.com/ethiopias-fragile-ceasefire-ends-as-government-forces-and-
North Africa Post
- ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች የተፈጸመውን አሰቃቂ ጥቃት በማለት የመቀሌውን የህጻናት መዋያ ተመታ በተባለው ላይ የማውገዝ ሀሳቡን አቀረበ ይላል።
የተነሱነጥቦች
- የህወሓት ሀይሎች የአየር ድብደባ እርምጃው ንጽሁንን ኢላማ ያደረግ እንደሆነ በመግለጽ መግለጹ
- በድብደባው ዒላማ አካባቢ የነበሩ የእርዳታ ሠራተኞችም የጸረ እየር ተኩስ ድምጽ እንደሠሙ መረጃ መስጠታቸው
- መንግስት ግን ንጹሀንን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንዳልወሰደ መግልጹ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ- https://northafricapost.com/60266-escalating-tigray-war-unicef-condemns-deadly-attack-by-