የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ነሐሴ 21 ፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 27 |2022
The Gurdian
- በትግራይ የልጆች መጫወቻ ስፍራ ላይ በደረሰ የአየር ድብደባ በትንሹ ሰባት ሰዎች መሞታቸውን ነው የሚዘግበው።
የተነሱ ነጥቦች
- ሰባት ሠዎች ሞተዋል በማለት ከነዚያ መካከልም ሦስቱ ህጽናት እንደሆኑ
- መንግስት በበኩሉ በእየር ድብደባ እርምጃው ንጹሐንን ዒላማ ያድረገ እንዳልሆነ
- ባለፉት የውጊያ ወራትም መንግስት በአየር ጥቃት የ56 ሠዎች ሕይወት እንዲያልፍ ማድረጉንና ከነዝያም ህጻናት እንደሚገኙበት የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://www.theguardian.com/world/2022/aug/27/ethiopia-airstrike-hits-playground-in-tigray-
Alarabiya
- ህወሓት እንዳለው ተመድ “ በትግራይ የህጻናት መዋያ ላይ የተደረገ የኢትዮጵያ አየር ድብደባ እርምጃ” በማለት እርምጃውን ማውገዙን ነው የጻፈው።
የተነሱነጥቦች
- እርምጃዉን የተመድ የህጻናት ኤጀንሲ UNICEF እንዳወገዘው
- መንግስት ንጹሀንን እርምጃ እንደማያደርግና የቡድኑን “ ንጹሀን ሞቱ “ ውንጀላ ተቀባይነት እንደሌለው መግለጹ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://english.alarabiya.net/News/world/2022/08/27/UN-denounces-airstrike-in-Ethiopia-that-
DW
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ መንግስት የተፈጸመውን የአየር እርምጃ በመዋዕለ ህጻናት ላይ እንደሆነ ማመኑን መግለጹን የሚተነትን ነው።
የተነሱነጥቦች
- የእርምጃው ሠለባ ሆነዋል በተባለው ከሁልት ህጻናት ጋር የአራት ግለሠቦች ሞትን የተመድ አካል የሆነው UNICEF በጥብቅ ማውገዙን ነው የሚያሳየው።
- ከዚህ በፊትም የመጀምርያው የጦርነት ፍንዳታማ መንግስት ወታደሩን ወደ ትግራይ በመላክ ትግራይን እንዲያጠቁ በማዘዙ እንደሆነ
- አሁንም መንግስት ጦርነቱን እንደ አዲስ በአየር ድብደባ በመታገዝ እንዲስፋፋ አድርጓል የሚል ክሥ እየቀረበ ያለውን በጥሬ በጽሁፉ መቅረቡ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://www.dw.com/en/un-slams-airstrike-in-ethiopia-that-hit-kindergarten/a-62949431