የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

Garowe online
- አሜሪካ ለትግራይ እየደረሰ ያለውን ዕርዳታ መቅበሏን መረጃዎችን እየወጡ መሆናቸውን የሚዘግብ ነው።።
- ሚሊዮኖች ለወራት በጣም አስፈላጊ የሆኑ የአደጋ ጊዜ አቅርቦቶችን የሚያስፈልጋቸው ትግራይን ጨምሮ በኢትዮጵያውያን ዕርዳታ ከስካሁኑ በተሻለ መልኩ እንደደረሳቸው ያሳየ ነው።
- የእርዳታ ኤጀንሲዎች የኢትዮዽያ መንግስት ወደ ትግራይ እንዳይደርሱ የመረጃ ክልከላ እና እያደረገ ነው ሲሉ ሲወቅሱት እንደነበረ ጠቅሷል።
- ለተጨማሪ ሊንኩን ይጫኑ
ሊንክ https://www.garoweonline.com/en/world/africa/ethiopia-us-welcomes-progress-in-aid-reaching-tigray
Daily News Egypt
- የኢትዮጵያ በአባይ ግድብ ላይ ያልተረጋጋ መሬት ላይ የሚንጠባጠብ ውሃ ነው የሚል የግድቡ ሥራ በማንኛውም ሰዓት ሊስተጓጎል የሚችል እንደሆነ ለማሳየት የሞከረ ጽሁፍ ነው።
- ግድቡ በአባይ ወንዝ ላይ በሱዳን እና በግብፅ የታችኛው ተፋሰስ ላይ የሚኖረውን ፍሰት የሚጎዳ እንደሆነ በማንሳት በወንዙ ላይ የውሃ መብትን በተመለከተ ትልቅ መከራከርያዎች አሁንም እንደቀጠሉ በማብራራት ግብጽ አሁንም የግድቡን ሙሌት ለማስተጓጎል ዓላማው እንዳላት የሚያሳይ መረጃ ነው።
- በርካታ ሳይንቲስቶች እና መሐንዲሶችም ግድቡ በቴክቶኒክ ክልል ውስጥ በተራራማ መሬት ላይ ስለሚገኝ ስለ ግድቡ መዋቅራዊ ታማኝነት ስጋታቸውን ለመግለፅ ማሳየት ሞክረዋል ።
- የሳተላይት ምስሎች እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ የግድቡን የውሃ ማጠራቀሚያ እየሞላች ነው የሚልም መረጃ አካቷል። ይህም ኢትዮጵያ የሁለቱን የተፋሰሱን ሀገራት ፍላጎት ችላ እንዳለች ለማስረዳት የሞከረ መሆኑ ነው።
- ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ በአባይ ግድብ ላይ ያላቸውን ደህንነቱ የተጠበቀ አሰራር እና የቀጣናውን ሠላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ፖለቲካዊ መግባባት ላይ ለመድረስ ከኢትዮጵያ ጋር እየተደራደሩ መሆናቸውን አስቀምጧል።
- ለተጨማሪ ሊንኩን ይጫኑ
ሊንክ https://dailynewsegypt.com/2022/06/08/ethiopias-gerd-damming-water-in-unstable-terrane/
The East African
- የኢትዮጵያ መንግስት በአፍሪካ ህብረት ጥረት እየተካሄደ ላለው የሽምግልና ሂደት ቁርጠኛ እንደሆነች መግለጿን የሚተነትን ነው።
- የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ወ/ሮ ቢልለኔ ስዩም የኢትዮጵያ መንግስት ግጭቱን ለማስቆም መንግስት ቁርጠኝነቷን በተግባር እያሳየች መሆኗን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መግለፁን በማስታወስ ኢትዮጵያ ከህወሓት ጋርም የመደራደር ፍላጎት እያሳየ እንደመጣ ለማሳየት
- ኢትዮጵያ ወደ ትግራይ የሚደረገውን ዕርዳታ ለመፍቀድ የአንድ ወገን ስምምነት እንዳወጀችም በመጻፍ ከህወሓት ይልቅ መንግስት አሁን እንደ እዲስ መከሰቱ የሚያሰጋውን ጦርነት ማድረግ ፍላጎት እንደሌለውም ለመግለጽ ሞክሯል።
- ለተጨማሪ ሊንኩን ይጫኑ
All Africa
- አሜሪካ መንግስት የአፋር እና የህወሓት ባለስልጣኖች የሰብአዊ አቅርቦት እንዲጨምር አስፈላጊ አገልግሎቶችን ወደነበረበት እንዲመለስ ጥሪ አቅርበዋል በሚል የጀመረችውን ፕሮፓጋንዳን በማካተት መንግስት የትቋረጡትን አገልግሎቶችን መልሶ የማስጀመር ሥራ እንዲጀምር የማስገደድ ሥራ ውስጥ እንዲገባ ለማስቻል በውጭ ሀይሎች ጫና እያደረጉ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
- የአሜሪካ መንግስት በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ለተቸገሩ ማህበረሰቦች ሰብዓዊ ርዳታ ይበልጥ መደበኛ በሆነ መንገድ እንዲደርስ በማድረግ የተገኘውን መሻሻል በደስታ የሚቀበል እንደሆነም በመግለጽ ጉዳዩ ላይ አሜሪካ የማበረታታትና ወደ ድርድር እንዲያመሩ ሳይሆን እርዳታው ወደ ትግራይ ለህወሓትም ሀይል በሚተርፍ መልኩ ወደ ክልሉ እንዲገባ ለማድረግ ከፈተኛ እንቅስቃሴ እያደረገች እንደሆነም የሚያመላክት ነው።።
- አሜሪካ በተጨማሪም “የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች፣ አለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ሌሎችም የአሜሪካ መንግስት አጋሮች እና የሰብአዊ ድርጅቶች በመላው ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጥረት” እንደሚያደንቁም ለማመላከት ጥሯል።
- ለተጨማሪ ሊንኩን ይጫኑ
ሊንክ– https://allafrica.com/stories/202206090149.html