የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
1 min read
ነሐሴ 19 ፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 25 |2022
Aljazeera
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰሜን ኢትዮጵያ በድጋሚ በተካሄደው ጦርነት የተኩስ አቁም ጥሪ እንዳቀረበ ነው የሚገልጸው።
የተነሱነጥቦች
- የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በትግራይ ክልል ዳግም ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ መደንገጣቸውን ጠቅሶ የተኩስ አቁም ጥሪ እንዳቀረቡ።
- ጦርነቱ በፊት በሚዋጉት አካላት መካከል የተቀሰቀሰው ለወራት የቆየውን የተክስ አቁም ያፈረሠ እንደሆነ
- ከጦርነቱ መቀስቀስ በኋላ የኢትዮጵያ አየር ሀይል የጦር መሣርያ የጫነን የጦር አውሮፕላን በኢትዮጵያ አየር ክልል ውስጥ በመግባቱና መቶ እንደጣሉን
- በጦርነቱ ቀስቃሽነት ሁለቱም ወገኖች እርስ በእርስ እየተካሠሱ እንደሆነ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://www.aljazeera.com/news/2022/8/24/au-calls-for-peaceful-solution-amid-renewed-f
Bloomberg
- ኢትዮጵያ ከሱዳን ድንበርን የተሻገረን የጦር መሳሪያ የጫነ አውሮፕላን እንደመታች አሳወቀች ይላል።
የተነሱነጥቦች
- የኢትዮጵያና የሱዳን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሻክሮ እንደነበርና አሁን የበለጠ የሚሻክር እደሆነ
- የአውሮፕላኑ መመታትም በትግራይ ከጦርነቱ መቀስቅሰ ጋርም እንደሚያያዝ
- የሱዳን መከላከያ ቃላቀባይ የአውሮፕላኑ መመታት ከሱዳን ጋር የማይገናኝ እንደሆነ መግለጹ
- የጦርነቱ መቀስቀስ አሁን ዳግም የእርዳታ ማድረሥ ስራዎችንና ለዜጎች የማደልንም እንቅስቃሴ የሚገታ እንደሆነ የሚሉት ዋና ዋና ነጥብች ናቸው።
ሊንክ – https://www.bloomberg.com/news/articles/2022-08-24/ethiopia-says-arms-laden-plane-from-
The Telegraph
- በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ‘ትልቅ’ ጦርነት ቀሰቀሰ የሚል መልዕክት የያዘ ነው።
የተነሱነጥቦች
- የመረጃው አቀራረብ የፌድራል መንግስት በትግራይ ላይ ከባድ ጦርነት እንደጀመረ ተድርጎ መቅረቡ
- ይህ ግጭት ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የሠላም ድርድርን የሚያስቀር እንደሆነ
- መንግስት ማንኛውም አካል የወታደራዊ እንቅስቃሴዎች መረጃን እንዳይዘግብ መከልከሉን ጠቅሶ መንግስት ጦርንቱን ለመጀመር ያን እንዳድረገ ተደርጎ መቅረቡ የሚሉት ዋና ዋና ነጥብች ናቸው።
ሊንክ – https://www.macon.com/news/business/article264834829.html
Mercury News
- ይግራይን ከኢትዮጵያ ውጭ እንዳለ ሌላ አካል አድርጎ የሚያቀርብ መረጃ የኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ‘ትልቅ’ ጥቃት ሰነዘረች በሚል ርዕስ የወጣ ነው።
የተነሱነጥቦች
- መንግስት ከፍተኛ የማጥቃት እርምጃ እንደወሰደ ተደርጎ መነገሩ
- ይህም መንግስት ከአፍሪካ ትልቁን የመከላከያ ሠራዊት ከገነባ በኋላ ማጥቃት ጀመረ በሚል ውንጀላ መቅረቡ
- የህወሓት ቡድን ድርድር እንደማይፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲናገሩ መቆየታቸው ጦርነቱን እንደሚጀምሩ አመላካች እንደሆነ
- መንግስት ለድርድር ዝግጁ መሆኑን እንደገለጸ ሁሉ የህወሓት ቡድንም በትግራይ መሠረታዊ አገልግሎቶች አስቀድመው የሚጀመሩ ከሆነ እንደሚደራርደር መግለጹ በሚል ጽሁፉ መንግስት ድርድሩን እንዳልፈለገ የሚያነግር መልዕክት ማካተቱ
ሊንክ – https://www.mercurynews.com/2022/08/24/ethiopia-launches-large-scale-offensive-in-tigray-