የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ነሐሴ 10 ፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 16 |2022
VOA
የኢትዮጵያ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ ክልል የመሬት ክፍፍል ውንጀላዎችን መመርመር የሚፈልግ መሆኑን የሚገልጽ ነው።
የተነሱ ነጥቦች- በትግራይ የአማራ ክልል የሆኑት ባለስልጣናት የአማራ ብሄር ተወላጆችን ብቻ የመሬት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሆኡ እንደሆነና በዝያም ቅሬታዎች እየተሠሙ እንደሆነ
Sudan Tribune
ኢትዮጵያ የአየር ክልሏን ከማንኛውም የውጭ ጥቃት እከላከላለው በማለት ማስጠንቀቋን ነው የጻፈው።
የተነሱ ነጥቦች
- ኢትዮጵያ የአየር ኃይሉ ከማንኛውም ዓይነት ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል አቅም እንዳለው መግለፁ
- የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለሶስተኛው ዙር ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቋ
- የአባይ ግድብ ሙሌትን ተከትሎ ለተፋሰሱ ሀገራት ሌላ ተጨማሪ ውጥረትን የሚፈጥር እርምጃ እንደሆነ መነገሩ
- ግብፅም በአሁኑ የዛናብና ጎርፍ ወቅት ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ የውሃ ሙሌት እንደምትሞላ የሚገልጽ መልእክት ከኢትዮጵያ በኩል በጁላይ 26 ደርሶኛል ማለቷ
- ባለፈው ወር ግብፅ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተቃውሞዋን ማስመዝገቧንና ኢትዮጵያ ግድቧን በአንድ ወገን ያለ ስምምነት መሙላቷን መቃወሟ የሚሉት የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://sudantribune.com/article262822/
The new Arab
- በአባይ ግድብ ጉዳይ ግብፅ እና ኢትዮጵያን ለማስደሠት ጆ ባይደን አጣብቂኝ ውስጥ ገቡ ይላል።
የተነሱ ነጥቦች
- ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲሞላ እስከ 74 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የውሃ ሙሌት አንድሚኖረው እና በኢትዮጵያ ትልቁ እንደሆነ
- ከግድቡ በታች በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የምትገኘው እና በታሪክ ከውሃዋ የበለጠ ተጠቃሚ የሆነችው ግብፅ ግንባታዋን አጥብቃ እንደተቃወመች
- ግብፅ የአባይን ውሃ የኤኮኖሚዋ እና የግዛትነቷ መመላለሻ መስመር ወደፊት እየቀነሰ እንዳይሄድ መድስጋቷ የሚሉት ከተነሱ ነጥቦች መካከል ናቸው።
ሊንክ https://english.alaraby.co.uk/opinion/between-dam-and-two-autocrats-bidens-gerd-dilemma