የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ነሐሴ 6 ፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 12 |202
Africa News
የግብጽና የሱዳን ተቃውሞ ቀጥሎ ያለ ቢሆንም ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ ሀይል ማመንጨት እንደጀመረች ነው የጻፈው።
የተነሱ ነጥቦች
- ሁለቱ የጽፋሰሱ ሀገራት የህዳሴን ግድብ ውሀው ላይ ያላቸውን ድርሻ እንደሚያጎልባቸው እንደሚያስቡ
- ገብጽ ለተመድ የጽጥታ ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ደብዳቤ መጻፏ
- አሁንም ሁለቱ ሀገራት በግድቡ ዙርያ አንድ ስምምነት ላይ እንዲደረሥ እንደሚፈልጉ
- ይህ ውጥራት ባለበት ባሁኑ ወቅት በአካባቢው / በቀጠናው የአልሽባብ ጥቃት መቀስቀሱ
- ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ ለመጀምርያ ጊዜ ሀይል ማማንጨት እንደጀመረች
Al Jazeera
- ኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ለሦስተኛ ጊዜ የውኃ ሙሌት እንዳጠናቀቀች የሚተነትን ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- ኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ በአባይ ግድብ ላይ የሚገኘውን ግዙፍ ግድብ የውሃ ሙሌት ማጠናቀቋ
- ኢትዮጵያ የግድቡን ሦስተኛ ሙሌት ማጠናቀቋ ከግብፅ እና ሱዳን ጋር ተጨማሪ ውጥረትን ሊፈጥር እንድሚችል
- የከዚያው ጋር ተያይዞም የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሁለተኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማምረት መጀመሯ
- የኢትዮጵያ መንግስት ኢትዮጵያ ግድቡን ለመገንባት ሙሉ መብቷን በተፈጥሮ ያላት እንደሆነ አቋም መያዙ
ሊንክ – https://www.aljazeera.com/news/2022/8/12/ethiopia-says-completes-third-filling-of-mega-dam-reservoir
Al Arabiya
- የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሐተ ሀይሎች “ቀጥታ ግንኙነት” በማድረግ እየተነጋገሩ እንደሆነ የአፍሪካ ህብረት ሃሙስ እለት ባወጣው መግለጫ ማሳወቁን ነው የጻፈው።
የተነሱ ነጥቦች
- መንግስት ከህወሐት ጋር ቀጥተኛ ንግግር እንደጀመረ
- ሁለቱም ወገኖች የ21 ወራት ጦርነትን ለማስቆም ድርድር ሊደረግ እንደሚችል ሲጠቁሙ እንደነበረ ።
- ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ድርድሩን እንዲመራ ግፊት ማድረጓ
- በሰላማዊ ትግል ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደረጉት የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ሁለቱ ወገኖች እንዲደራደሩ መፈለጋቸው እንደሚፈልጉ
- የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ግጭቱን ለማስቆም ዲፕሎማሲያዊ ግፊት ማድረጋቸው