የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ነሐሴ 5 ፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 11 |2022
Al-Monitor
- ግብፅ እና ኢትዮጵያ በተደረጉ ስብሰባዎች የአባይን ግድብ ውዝግብ ላይ አቋማቸውን ማለሣለሳቸውን ነው የጻፈው ።
የተነሱ ነጥቦች
- የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በቅርቡ ባደረጉት የአፍሪካ ጉብኝታቸው በአራት የናይል ተፋሰስ ሀገራትን በማካተት የአባይን ውሃ ውዝግብ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ያለውን ቀውስ መመልከታቸውን ።
- መግለጫው የአባይ ግድብ ቀውስን አለመመልከቱን እና የሩሲያ የኢንዱስትሪ ዞን ላይ ያተኮረ መሆኑ
- የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የግብፅ እና በኋላም ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት ከአባይ ግድብ የውሃ ማጠራቀሚያ ሶስተኛው የመሙላት ሂደት ጋር መገናኘቱን ።
Sada El balad
- ግብፅ የ አባይን ግድብ የ3ኛ ሙሌቷን አደጋዎች እንዳሉት ለUNSC ደብዳቤ እንደላከች ይዘግባል።
የተነሱ ነጥቦች
- ግብፅ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት (UNSC) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለሦስተኛ ጊዜ የሚካሄደው ሥራ በሚደርሳት ውሀ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንደሚያደርስ ማሳወቋ
- የቅርብ ጊዜ የሳተላይት ምስሎች ከአባይ ግድብ የኮንክሪት ፊት ላይ ስንጥቅ የሆነ ነገር መታየቱ
- ኢትዮጵያ የሚጠበቅባትን የአካባቢ እና ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ጥናቶችን የማካሄድ ግዴታዋን አለመወጣቷን በግብፅ የውሀ ሃብትና መስኖ ሚኒስትር መሀመድ አብደል አቲ መግለጻቸው
- ኢትዮጵያ ለግብፅ ሁለተኛውን ሙሌት ስታደርግ ምንም አይነት ዝርዝር ነገር አለመስጠቷን እና ትክክል አለመሆኑን ዓለም አቀፍ ህግን የሚጥስ መሆኑን መጠቁሙን ።
ሊንክ – https://see.news/egypt-sends-letter-highliligting-dangers-of-gerd-3rd/
Ahram Online
- ኢትዮጵያ ከአባይ ግድብ 2ኛ ተርባይን የሃይል ማመንጨት መጀመሩን እንዳስታወቀች ነው የጻፈው።
የተነሱ ነጥቦች
- ኢትዮጵያ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛውን ተርባይ በመጠቀም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫት መጀምሯ
- ተርባይኑ ዛሬ ላይ ሥራ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በነበረው ሥነሥርዓት ላይ ማስታወቃቸው