የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
![](https://ethiopiantruth.com/wp-content/uploads/2022/08/2H.png)
ነሐሴ 3 ፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 9 |202
VOA
- ኢትዮጵያ አዲስ ጦር ወደ ጎረቤት ሶማሊያ አሰማራች ይላል።
የተነሱ ነጥቦች
- የጦሩ ተልዕኮ በሶማሊያ የመሸገውን አልሸባብን ለማጥፋት እንደሆነ
- የኢትዮጵያ ወታደሮች በዶሎዋ የድንበር ከተማ እና አካባቢዋ የጦር ሰፈር መመስረታቸውን ።
- ቁጥራቸው ወደ 2,000 የሚጠጉ ወታደሮቹ የአልሸባብ ታጣቂዎችን ለመውጋት እንደተሰምማሩና በድንበር አካባቢ ብዙ ተዋጊዎችን ማሰባሰብ እንደጀመሩ
- የጸጥታው እጦት እየጨመረ በመምጣቱ የአልሸባብ ታጣቂዎች ድንበር አካባቢ ዘልቀው በመግባታቸው ምክንያት
ሊንክ – https://www.voanews.com/a/ethiopia-deploys-new-troops-into-neighboring-somalia-/6693095.html
Asharq AL-awsat
- ኢትዮጵያ 7 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የአባይ ውሃ እያጠራቀመች እንደሆነ የሚተነትን ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- ኢትዮጵያ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር ውሃ መሰብሰብ ከጀመረች ወዲህ 7 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ማከማቸቷ
- የግብፅ የውሃ ሀብት ኤክስፐርት እና የጂኦሎጂ ፕሮፌሰር አባስ ሻራኪ ኢትዮጵያ በዚህ አመት ሶስተኛውን ሙሌት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ብዛት ያለው ውሀ ማከማቸቷ
- ኢትዮጵያ ለሦስተኛው ተከታታይ ዓመት ሙሊቱን በማካሄድ ላይ እንደሆነች
- ግብፅ በግድቡ ላይ የኢትዮጵያን እንቅስቃሴ እንደምትቃወምና ያም የዓለማቀፍ ሀግን የጣሰ እንደሆነ
ሊንክ – https://english.aawsat.com/home/article/3805661/ethiopia-storing-7-billion-cubic-meters-nile-waters
Bloomberg
ሳሙኤል ገብሬ በተባለ ግለሠብ የተሠጠ ሀሳብ በመውሰድ በኢትዮጵያ የጽጥታ ችግር የተጠረጥሩትን ፍለጋ በሺዎች የሚቆጠሩ መታሠራቸውን ነው የጻፈው።
የተነሱ ነጥቦች
- በሽብር ድርጊት የተጠረጠሩትን ለማኘት በማጣራት ሂደቱ ከ4000 በላይ የሚሆኑ ዜጎች መታሠራቸው
- ዋነኛ ምክንያቱ የኢነግ ሸኔ፣ የአልሸባብና ሌሎች የሀገር ውስጥ አሸባሪ ቡድንን አመራር ፣ አባላትና ደጋፊዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንደሆነ