የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ነሐሴ 2 ፣ | 2014 ዓ.ም – Aug 8 |202
Sudan Tribune
በኢትዮጵያ ከ800 በላይ የአልሸባብ ተዋጊዎች መገደላቸውን መረጃ ያጋራ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- ከተገደሉት መካከል ሶስት የአልሸባብ ከፍተኛ አመራሮች ይገኙበታል ፉአድ መሀመድ ኻላፍን እንደሚገኙበት
- ከተገደሉት በተጨማሪ አንድ መቶ የሚጠጉ የቡድኑ አባላትም መያዛቸው መገለጹ
- የሽብር ቡድኑ ይህን የወረራ ሙከራ ያደረገው በኢትዮጵያ ላይ የመጀመርያው እንደሆነ
- ቡድኑ ሊወረው የሞከረው የአቶ ከተማ አሁን በኢትዮጳያ መከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር መሆኑ
- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ጋር በተቀናጀ መልኩ እርምጃ የወሰደ የሽብር ቡድኑ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት ከፈጸመ በኋላ እንደሆነ የሚሉት ዋና ዋና ንጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://sudantribune.com/article262470/
All Africa
ኢትዮጵያ ሱዳን፣ እና በግብፅ በህዳሴው ግድብ ላይ ያደረጉት ውይይት ስኬታማ እንዳሆነ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ማመኑን የሚነግር ትንተና ነው ።
የተነሱ ነጥቦች
- በኢትዮጵያ ሱዳን፣ እና ግብፅ መካከል በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሶስቱ ሀገራት መካከል የተካሄደው ድርድር በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እንደተገለጸ
- የሀዳሴ ግድብ ቀጠናዊ ውህደትን እና ትብብርን ለማሳደግ ትልቅ እድል መሆኑን ገልፆ ሶስቱንም ሀገራት የአፍሪካ ህብረት የመሪውን ድርድር የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መንግስት በደስታ እንደተቀበለ
- በግድቡ አሰራር እና አገባብ ላይ ከኢትዮጵያ ህጋዊ የሆነ ስምምነት እንዲደረግላቸውና የተወሰነ መጠን ያለውን ውሃ እንደሚያገኙ ዋስትና እንዲሰጣቸው ሱዳን እና ግብፅ እንደሚፈልጉ
- የሱዳን መንግስት የራሳቸውን የሀይድሮ ኤሌክትሪክ አባይ ግድቦች ተግባር ለማረጋገጥ እና ወደፊት የጎርፍ መጥለቅለቅን ለማስቆም የግድቡ ስራ ላይ ወቅታዊ መረጃ እንዲሰጣቸው ኢትዮጵያ መጠየቃቸው
ሊንክ https://allafrica.com/stories/202208080207.html