Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

1 min read

ሐምሌ 24፣ | 2014 ዓ.ም – July 31 |2022

VOA

  • የአሜሪካ ልዩ ልዑክ በኢትዮጵያ የሰላም ንግግሮች እና ዕርዳታ መሻሻል ላይ  ቱክረት እንዲደረግ እንዳሳስቡ ነው የተሚዘግበው።

በዘገባው የተነሱ ዘገባወች

  • የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሃመር ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ያልተገደበ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲገባና ለዝያም ሁኔታዎችን መንግስት እንዲያመቻች ለማደረግ መሆኑ
  • በተጨማሪም የፖለቲካ ምክክሮች እንዲኖሩና ሁለቱ ወገኖችም የድርድር ጉዳይ ላይ ከፍተBኛ ጥረት እንዲያደርጉ ለማስቻል እንደመጡ
  • በጉዳዩ ለይ ለድርድሩ መንግስት ቁርጠኛ ቢሆንም የህወሓት አሸባሪ ሀይል ከድርድሩ አሰቀድሞ ቅድመ ሁኔታዎችን ለማስቀመጥ የሞከረ እንደሆነና ከቅደም ሁኔታዎቹም መካክል በትግራይ ክልል የመሠረታዊ አገልግሎቶች እንዲመለስላቸው እንደጠየቁ
  • የመሠረታዊ አገልግሎቶችም ሆነ የምግብና የነዳጅ እጥረትን በተመለከተ ህወሓት እንዳለው መንግስት ትግራይን በከበባ ውስጥ በማስገባቱ እንደሆነ መገለጹ የሚሉት ዋና ዋና የዘገባው አንኳር ሀሳቦች ናቸው።

ሊንክ  – https://www.voanews.com/a/us-envoy-urges-progress-on-ethiopia-peace-talks-aid-/6680877.html

Garowe Online

  • የአልሸባብ  አሽባሪ ቡድን ከድንበር አካባቢ እንዳልሄደ በመሆኑ በትኩረት ልንከታተለው ይገባል በማለት የሶማልያ መንግስት መግለጹን ነው የሚዘግበው።

በዘገባው የተነሱ ዘገባወች

  • የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን የኢትዮጵያን ምድር ለመጀመርያ ጊዜ ገብቶ ለማወክ የበቃው በድንበር አካባቢ ጠንካራ የስምሪት እቅድ ይዚ ስለነበር እንደሆነና በዚሁም በርካታ የኢትዮጵያን የጽጥታ ሀይሎች እንደገደለ
  • የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይል እርምጃ እንደወሰደበትና ባሁኑ ጊዜ ቡድኑ ካካባቢው የራቀ ያስመስል እንጂ እንዳልተዳከመም ጭምር በመግለጽ ካካባቢው እንዳልሄደ የሚያሳዩ ምልክቶች እንዳሉ የተለያዩ ተንታኞች እንደሚገልጹ የሚሉ ዋና ዋና የዘገባው ነጥቦች ናቸው።

ሊንክ- https://www.garoweonline.com/en/editorial/somalia-al-shabaab-never-left-so-we-must-keep-our-heads-focused

Egypt Independent

  • ግብጽ የህዳሴ ግድብ መሞላትን በተመለከተ ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ተቃውሞ አቀረበች ይላል።

በዘገባው የተነሱ ዘገባወች

  • የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ግብፅ ባቀረበችውን ተቃውሞ የኢትዮጵያን ውሀ ሙሌት ሙሉ በሙሉ ውድቅ ለማድረግ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ደብዳቤ መላካቸው
  • ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በዚሁ ወር ኢትዮጵያ ግድቡን ውሀ እየሞላች እንደሆነ መረጃ መስጠቷን ጠቅሰው ያን እንደማይቀበሉ መግለጻቸው
  • ኢትዮጵያ የዓለማቀፍ የውሀ ሀብት አስተዳደር ህግን ጥሳልች ለሱም ተጠያቂ ናት በማለት ገብጽ እየከሠሠች እንደሆነች

ሊንክ  –  https://www.egyptindependent.com/egypt-addresses-un-security-council-over-ethiopias-continued-filling-of-gerd/

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *