የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ሐምሌ 23፣ | 2014 ዓ.ም – July 30 |2022
Reuters
- በኢትዮጵያ ወታደሮች እና አሸባሪው አልሸባብ መካከል በተፈጠረ ግጭት የበርካታ የቡድኑ አባላት መገደላቸው መነገሩን ነው የሚተነትነው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- የሱማሌ ክልል ልዩ ሀይል የሸአሪውን አባላት ቁጥራችው 150 የሚሆኑትን መግደላቸው
- የአልሸባብ አሸባሪ ቡድኑ የተመታበትንና የተበታተኑትን አባላቱን መልሶ በማሰባብሰብ መልሶ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ጥሶ ለመግባት እንደሞከረ
- አልሸባብ በኢትዮጵያ ውስጥ የጦር ሰፈር ለመመስረት ሲጥር የቆየ እንደሆነና ከቅርብ አመታት ወዲህም በኢትዮጵያ በሚነገረው በአፋን ኦሮሞ መልእክት አስተላልፎ እንድነበር።
Aljazeera
- ሩሲያ እንደ ምዕራቡ ዓለም ለአፍሪካ እውነተኛ ወዳጅ አይደለችም ይላል።
- የሩስያ ወራራን መደገፍ የምዕራባውያንን ቅኝ ግዛት ወይም ተጨማሪ የአፍሪካን ነፃነት ለመዋጋት የሚውል መንገድ አይደለም በሚል ሀሳብ አንድ ታፊ ማካ የተባለ በጆሃንስበርግ ላይ የተመሰረተ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተንታኝ የጻፈው ነው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርይ ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ያደረገው የ 5 ቀናት ጉብኝት ሀገራቸ ከአፍሪካ ጋር ያላት ጠንካራ ትሥሥር ለማስቀጠል ያለመ እንደሆነ
- በየሀገራቱ ለጉብኘት ሲጓዙ ምንም እውነትን የያዙ መልዕክቶች ሳይሆን ተገቢ ያልሆኑ የሩስያን የፖለቲካ እሳቤዎች እየተናገሩ እያስተላለፉ እንደነበር
- ለአፍሪካ በሚቀርቡ በጥራጥሬ እህሎች ላይ የገጠመ ችግር በምዕራባውያን ማዕቀቦችና ጫናዎች ምክንያት እንደሆነ ሁሉም ይረዳል በማለት በካይሮ የተናገሩት በሩሲያ ዩክሬን የወረራ ጦርነት የተከሠተ እንደሆነ ለማዘናጋት እንደሆነ
- በየሀገራቱ የተናገሩትና የጻፏቸው ሀሳቦች ሁሉ ምዕራውባውያንን የሚኮንኑና ውሸት እንደሆኑ የሚሉት ዋና ዋና የዘገባው ነጥቦች ናቸው።
Voa
- አሜሪካ አልሸባብ በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ድንገተኛ አይደለም’ ሲል እንዳስጠነቀቀች ነው የጻፈው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- የሸብር ቡድኑ በሚቀጥሉ ወራት በኢትዮጵያ ላይ ተመሣሣይ ጥቃቶች ለማድረስ መዘጋጀቱ የአሜሪካ ጦር መሪዎች መግለጻቸው
- ቡድኑ ሠሞኑ ከመመታቱ በፊት እስከ 150 ኪሎ ሜትሮች ዘልቆ ገብቶ ሊሆን እንደሚችል
- የአሜሪካ ጦር የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል እስጢፋኖስ ታውንሴንድ፣ መቀመጫውን ዋሽንግተን ያደረገው የመከላከያ ጸሃፊ ቡድን ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ “ኢትዮጵያውያን ይህን ወረራ በአብዛኛው በቁጥጥር ስር ያዋሉ እና ያሸነፉ ይመስላል ማለታቸው
- ቡድኑ ከዚህ በፊትም በዝያ አቅጣጭ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲያቅድ የነበረ እንደሆነም
- ቡድኑ ባሁኑ ወቅት ከ 7000 እስከ 12000 የሚደርሱ ብዛት ያላቸው የጦር አባላት እንዳሉት የሚሉት ከዋና ነጥቦች መካከል ናቸው።
ሊንክ – https://www.voanews.com/a/us-warns-al-shabab-attack-on-ethiopia-not-a-fluke/6677868.html
Ahram Online
- በኢትዮጵያ የሠላም ጥረት የሚደግፍ የአሜሪካ ልዩ መልክተኛ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ የሚገልጽ ነው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- አዲሱ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ በመንግስት እና በህወሓት መካከል የተጀመረውን የሰላም ጥረት ለማገዝ አርብ እለት ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ
- ልዩ መልክተኛው ማይክ ሀመር በኢትዮጵያ መነግስት ባለሥልጣናት እንደሚያናግሩ
- ከምንም በላይ የሠላም ጥረቱ በጦርነቱ ለተጎዱ ዜጎች የምግብ እጥረትና ሌሎች ችግሮቻቸው ለመድረስ የሚረዳ በመሆኑ የሠላም ጥረቱ ሊጠናከር እንደሚረዳ