የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
ሐምሌ 20፣ | 2014 ዓ.ም – July 27 |2022
VOA
- አልሸባብ ለምን በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቃት ፈጸመ የሚል ዘገባ ነው ።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- ባለፈው ሳምንት ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ደንበር ጠሰው የገቡት የአልሸባብ ታጣቂዎች ኃይሉ ተደምስሷል ቢሉም አሁንም በሀገሪቱ ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ነው ሲሉ ባለስልጣናት እና የደህንነት ባለሙያዎች እየተናግሩ መሆኑን
- ባለሥልጣናቱ ሰኞ ዕለት የጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያ ሶማሌ ግዛት ፌርፊር በተባለው የድንበር ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ላስኩሩን መንደር ውስጥ ከአልሸባብ ተዋጊዎች ጋር መጋጨታቸው።
- የክልሉ ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ኦመር ወደ አካባቢው ከተላኩ የፌደራል ወታደራዊ ሃይሎች ጋር ሲገናኙ መታየታቸውን መናገራቸው ።
- ባለፈው ረቡዕ ከኢትዮጵያ ሶማሌ እና ኦሮምያ ክልሎች የመጡ በርካታ የአልሸባብ ተዋጊዎች ጨምሮ 500 ያህል የአልሸባብ ተዋጊዎች ኢትዮጵያ መግባታቸውን በርካታ የደህንነት እና የቀድሞ የአልሸባብ ታጣቂዎች ለቪኦኤ ሶማሌ “መርማሪ ዶሴ” ፕሮግራም ዘግቦ እንደነበር
- አሁን በስዊድን የሚኖረው የአል-ሸባብ የቀድሞ መሪ ኦማር መሀመድ አቡ አያን ወረራው በፕሮፓጋንዳ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ማለታቸው የሚሉት ዋና ዋና የዘገባው ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ https://www.voanews.com/a/why-did-al-shabab-attack-inside-ethiopia/6674783.html
Sudan tribune
- ኢትዮጵያ ሰላምን ለማስፈን ጥረት የሚያደርጉ የተመድ ልዑካንን አግዳለች በሚ የአሸባሪው ህወሓት አመራሮች እየከሠሱ እንደሆነ የሚዘግብ ነው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- የአሸባሪው ህወሓት አመራሮች የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜናዊው የሀገሪቱ ክፍል የነበረውን ጦርነትና ጉዳቶቹን ለማስቆም አህጉራዊ እና አለምአቀፋዊ ጥረቶችን ሆን ብሎ ማደናቀፍ ነው ሲሉ መክሰሳቸው
- የቡድኑ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ለሱዳን ትሪቡን መግለጫ መስጠታቸውንና በዝያም መንግስት ሰላምን ለማሳለጥ የሚሞክሩትን አለም አቀፍ ዲፕሎማቶች ጉዞ እየከለከለ ነው ማለታቸው
- የአሜሪካን አምባሳደሮችን ጨምሮ ከተመድና ሌሎች ሀገራት የተወጣጡ ልዑካን አምባሳደሮች ወደ ትግራይ ለመጓዝ ፈልገው በኢትዮያ መንግስት መታገዳቸው
- የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በዋሽንግተን ሁለቱን ወገኖችን ወደ ድርድር ለማድረስ በምታደርገው ጥረት አህጉራዊ ጉብኝት በመጀመሩ በመጪዎቹ ቀናት ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ሊንክhttps://sudantribune.com/article261894/