የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
1 min read
ሐምሌ 13፣ | 2014 ዓ.ም – July 20 |2022
Ahram Online
- ግብጽ በአባይ ግድብ ላይ አለም አቀፍ ህግ መተግበር እንዳለበት ለዓለማቀፍ ማህበረሠብ ጥሪ እያደረገች እንደሆነ ነው የጻፈው
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- ኢትዮጵያ ግብፅ እና ሱዳን ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት እንዲኖራቸው ጥሪያቸውን በድጋሚ ችላ በማለት ለሦስተኛ ጊዜ የአባይ ግድብን የውሀ ሙሌት እያካሄደች እንደሆነ፣
- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሞላል እና አተገባበር ላይ ሳይዘገይ ስምምነት ላይ እንዲደርስ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል ሲሲ እና የአሜሪካው አቻቸው ጆ ባይደን መጠየቃቸው፣
- አሜሪካ የግብጽን የስምምነት ላይ እንድረስ ፍላጎትና ጥያቄ ደጋፍ ለማድረግ ያህልና በሦስቱ የተፋሰሱ ሀገራት መካከል ስምምነት ላይ እንዲደረሰ ድጋፍ እንደምታደርግና ጠሪም ማድረጓን፣
- የጀርመን መንግስትን በስምምነቱ ዙርያ አለምግባባቱ ላይ ተቶክሮ ያን በመፍታት በሀገራቱ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት መፍታት እንደሚችል መግለጹን፣
- ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ወንዞችን የሚቆጣጠሩትን ስምምነቶች በመጣስ ባለፈው ሳምንት ለሦስተኛ ጊዜ የአባይ ግድብን የውኃ ማጠራቀሚያ እንደጀመረች።
ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጭኑ
Egypt Independent
- አባይ ግድብ ውስጥ ከአንድ ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ መከማቸቱን አንድ አባስ ሻራኪ የሚባል የውሃ ባለሙያ ።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሶስተኛው ክምችት ከተጀመረ ከሰባት ቀናት በኋላ በግድቡ ውስጥ ከአንድ ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ መከማቸቱን ሳተላይቶች ማሳየታቸውን ግብፃዊው የውሃ ኤክስፐርት አባስ ሻራኪ መናገሩ፣
- ስለ ግድቡ የሳተላይት መረጃ እንዳገኙ በመግለጽ የውሀ ይዘት መጠኑን ከፍ በማድረግ ግድቡ ሶስተኛ ሙሌቱን እያካሄደ እንድሆነና የወሀ ይዘቱን እየጨምረ እንድሆነ፣
- ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር በግድቡ ሙሌት ክትትል ላይ በጋራ እለመስራት ለኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርባ እንደነበርና ኢትዮጵያም የግድቡ ችግሮች በሙሉ እንደተፈቱ አድርጋ እንደምታይ።
ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጭኑ
Wionews
- በኢትዮጵያ በሰላም ስምምነቱ ላይ ውዥንብር እንዳለ መንግስትም ሆነ ህወሀት ድርድሩ ተግባራዊ እንዲሆን እንዴት እንደሚፈልጉ እርስ በርሱ የሚጋጩ ፍላጎቶች እንዳሏቸው የሚተነትን የቪዲዮ ዘገባ ነው።
በዘገባው የተነሱ ነጥቦች
- በመንግስት በኩል ያለውም 7 አባላትን የያዘ ለድርድሩ የቋቋመ ኮሚቴም በጉዳዩ ላይ የመጀመርያ ስብሰባ እንዳካሄደ፣
- የአፍሪካ ህብረትም ድርድሩ እውን እንዲሆን በምሥራቅ አፍሪካው ልዩ መልዕክተኛው ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በኩል ጥረት እያደረገ መሆኑን፣
- የህወሓት ቡድንም የአፍሪካ ህብረትን ባደራዳሪነት እንዲቀርብ እንደማይፈልግና ኬንያ በቦታው እንደትሆን እንደሚፈልግ መግለጹ፣
- መንግስት ለህወሓት ከሸባሪነት እንዲሠረዝም እድል መስጠት እንድሚፈልግም መግለጹን የሚሉት ዋና ዋና የተነሱ ነጥቦች ናቸው።
ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጭኑ
ሊንክ – https://www.wionews.com/videos/world-of-africa-will-ethiopias-tigray-conflict-end-peacefully-498965