የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ጥቅምት 9 -2016 | Oct 20, 2023 |
Bloomberg
የመረጃው እንድምታ
ጅቡቲ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያ የኢትዮጵያን የቀይ ባህር ወደብ ቀጥታ የማግኘት ጥያቄ ውድቅ እንዳደረጉ ጠቅሶ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግን የባህር ተደራሽነት ወደብ ለሌላቸው ሀገራቸው እንደ ስትራቴጂካዊ አላማ እንደሚመለከቱት የሚያብራራ ነው።
SHINE
የመረጃው እንድምታ
በቻይና የሻንጋይ ፓርቲ ፀሐፊ ቼን ጂንግ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሊ ያደረጉትን ስብሰባ የተመለከተ ነው። ቼን የጠቅላይ ሚኒስትሩን የሻንጋይ ጉብኝት በደስታ የተቀበሉ ሲሆን ከተማዋ በሁለቱ ሀገራት መካከል ተግባራዊ ትብብርን ለማሳደግ ፍቃደኛ መሆኗን በማንሳት ኢትዮ-ቻይና ግንኙነት አስፈላጊነት ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የንግድ ትብብርን ለማሳደግ ያለውን እንድምታ የሚያሳይ እንደሆነ የሚተነትን ነው።
ሊንክ – https://www.shine.cn/news/metro/2310208012/
The East African
የመረጃው እንድምታ
የተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) በኢትዮጵያ ለተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የ219 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ እጥረት አጋጥሞታል የሚል ነው።