Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ጥቅምት 8 -2016 | Oct 19, 2023

INTELLI NEWS

የመረጃው እንድምታ    

ሶማሊያ የቀይ ባህርን ወደብ የማግኘት እድልን በተመለከተ ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የድርድር ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን በመግለጽ ይህ የኢትዮጵያ የቀይ ባህር መዳረሻ ፍላጎት በቀጠናው መረጋጋት ላይ ስጋት መፍጠሩን የሚያብራራ ነው።

ሊንክ   –  https://intellinews.com/somalia-rejects-ethiopia-s-call-for-negotiations-on-red-sea-access-297441

 Relief Web

የመረጃው እንድምታ    

በኢትዮጵያ እየታዩ ባሉት የሀይማኖት ተቋማት አለመግባባት ዙርያ በሀገሪቱ ግጭት አፈታት እና መከላከል የሀይማኖቶች ሚና ላይ ያተኮረ መረጃ ነው። ሪፖርቱ የሰዎች እምነት/ ሀይማኖት  በድርጊታቸው ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር በማንሳት የተለያዩ አመለካከቶችን እና አስተያየቶችን በመቅረጽ ላይ ያተኩራል። ሃይማኖት ከታሪካዊ ትረካዎች፣ የብሄር ማንነቶች እና ሌሎች ማህበራዊ መመዘኛዎች ሙሉ በሙሉ ሊነጠሉ የማይችሉ ልምምዶች እና እምነቶች ስብስብ እንደሆኑ የሚያሳይ ነው።

ሊንክ   https://reliefweb.int/report/ethiopia/religious-polarisation-ethiopia-urban-conflicts-and-resources-peace

Ventures Africa

የመረጃው እንድምታ    

ኢትዮጵያ ለግል ኢንቨስትመንት ቅድሚያ ለመስጠት እና ሂደቶችን ለውጭ ኢንቨስትመንት ለማቀላጠፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማድረግ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማረጋገጥ እና የመንግስት እና የግሉ ሴክተሮች በኢኮኖሚው ውስጥ ያላቸውን ሚና ለማስተካከል ብትሰራም የኢትዮጵያ መንግሥት የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ተመንን ለማስጠበቅ ተግዳሮቶች እንዳጋጠሙት የሚያብራራ ነው።

ሊንክ   https://www.bnnbloomberg.ca/ethiopia-says-lack-of-port-access-can-fuel-future-conflict-1.1985611

  PRENSA LATINA

የመረጃው እንድምታ    

የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከእስራኤል አምባሳደር አሊ አድማሱ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት መምከራቸውን የሚገልጽ ነው።

ሊንክ   –  https://www.plenglish.com/news/2023/10/18/conflict-resolution-focuses-ethiopia-israel-meeting/

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *