Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

መስከረም  22| oct 3, 2023

  Crisis24

  • በአማራ ክልል የፀጥታው ሁኔታ ቢያንስ እስከ ጥቅምት መጨረሻ ድረስ ያልተረጋጋ ሆኖ ሊቆይ እንደሚችል የሚገልጽ ነው ።

     የተነሱ ነጥቦች

  • በአማራ ክልል፣ ኢትዮጵያ ቢያንስ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በቀጠለው ወታደራዊ ዘመቻ የጸጥታው ሁኔታ ያልተረጋጋ ሆኖ ሊቆይ መቻሉን  
  • በኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት ወታደሮች እና ፋኖ ቡድን መካከል በቀጠለው ግጭት  በአማራ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ ተለዋዋጭ ሆኖ እንደሚቆይ
  • በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች መኖራቸውን እና በፋኖ ቡድን ላይ ጥቃት መድረሱን
  • በመንግስት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሁን ላይ ጦርነት ማስነሳቱን እና መንግስት በክልሉ ላይ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ግጭቶች መቀስቀሳቸውን
  • የፌደራሉ መንግስት በአማራ ክልል በተለይም በባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ሞጣ እና ኮምቦልቻ በመሳሰሉት ትላልቅ ከተሞች የታጠቁ ተሽከርካሪዎችን ማሰማራትን መጨመሩን እና ከፍተኛ የሰራዊት ይዞታ መያዙ አለመቅረቱን
  • መንግስት በውጊያው አቅሙ በመዳከም ምክንያት ኤንትረኔት እና መብራትን ጨምሮ በክልሉ ያሉትን መሰረታዊ አግልግሎቶች  በማቆረጥ ላይ እንደሆነ እና መንግስት በአማራ ክልል ላይ አዲስ የጉዞ ገደቦችን በማድረግ እገዳ እንደሚጥል
  • መንግስት ከፋኖ ቡድን ጋር ግጭት ውስጥ የመግባቱ ምክንያት በአማራ ክልልን ወክለው የፓርላማ አባል የሆኑ ክርስትያን ታደለ ጥያቄ በመጠየቃቸው እንደሆነ የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።

ሊንክ   https://crisis24.garda.com/alerts/2023/10/ethiopia-security-situation-likely-to-remain-volatile-in-amhara-region-through-at-least-late-october-update-3

  Just Security

  • በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሊራዘም እንደሚገባ የሚያሳይ ነው ።    

 የተነሱ ነጥቦች

  • የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ካውንስል (HRC) በቅርቡ የወደፊት እጣ ፈንታን  እንደሚወስን ።
  • የተጠረጠሩ የጦር ወንጀሎችን እና ሌሎች የሰብአዊ መብቶችን የሚመረምር ገለልተኛ ኮሚሽን በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል እና በሌሎች አካባቢዎች የሚፈጸሙ ጥሰቶች የሶስት ባለሙያዎች ፓነል እንዳለው ።
  • ኢትዮጵያ (ICHREE) የስልጣን ዘመኗን ለማደስ ከፍተኛ ጦርነት እንደገጠማት እና ዩናይትድ ስቴትስ የራሳቸው ጂኦፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ያሏቸው ሌሎች የምዕራባውያን መንግስታት የኢትዮጵያን መሪዎች ማስደሰት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትሕ ረቂቅን  እንደሚያከራክሩ
  • ኢትዮጵያ ለዘለቄታው ሰላም የምትጓዝበት መንገድ ትክክለኛ ፖለቲካዊ እና ህጋዊ ተጠያቂነትን እንደሚጠየቅ
  • የዩኤስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሰብአዊነት እና በዘር ማጥፋት ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት ላይ ውሳኔ መስጠቱን  
  • ICHREE በቅርቡ ባወጣው ዘገባ በትግራይ ያለው ግጭት  አሁንም እንዳላበቃ እና የኤርትራ ወታደሮች እና የአማራ ታጣቂዎች ቀጣይነት ያለው የመብት ጥሰት እየፈጸሙ እንደሆነ የሚል መደምደሚያ ላይ  መድረሱን 
  • በትግራይ የተፈፀመውን ግፍና ሌሎች ግጭቶችን በተመለከተ አጠቃላይ ምርመራ በኢትዮጵያ HRC በዚህ ወር የኮሚሽኑን ማራዘም አለመቀጠል ለመወሰን መዘጋጀቱን እና የተቋቋመበትን ዋና የሰብአዊ መብት መርሆዎች የማክበር ግዴታ እንዳለበት የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።

ሊንክ   https://www.justsecurity.org/89012/un-human-rights-council-should-extend-investigation-commission-on-ethiopia/

    BBC

  • በሱዳን ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በከባድ መሳሪያ ጥቃት መፈጸሙን ምንጮች መግለጻቸውን የሚያሳይ ነው

 የተነሱ ነጥቦች

  • በሱዳን ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ ማለዳ ላይ በከባድ መሳሪያ ጥቃት መፈጸሙን ታማኝ ምንጮች ለቢቢሲ  መናገራቸውን  
  • በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በከባድ መሳሪያ ጥቃት በመድረሱን እና በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም ንብረት መውደሙን ለማረጋገጥ ወደ አካባቢው ሰዎች  መላካቸውን
  • በጄኔራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ የሚመራው የሱዳን ፈጣን ምላሽ ሃይል (RSF) በትዊተር ገፁ እንዳሰፈረው የሱዳን ወታደሮች ካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት እንዳደረሱ
  • እኛ የሱዳኑ ፈጣን ምላሽ ሃይል መሰል ድርጊቶችን እናወግዛለን እና የአል-ቡርሃን ሃይሎች በአለም አቀፍ ድርጅቶች እና ዲፕሎማቶች ላይ ማነጣጠሩን ቀጥለዋል ማለታቸውን እና የሱዳን መንግስት በዲፕሎማቲክ ተቋማት ላይ ተፈጽሟል ስለተባለው ጥቃት የሰጠው መግለጫ  አለመኖሩን
  • የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ላይ መግለጫ ባይሰጥም በካርቱም የቀሩትን ሰራተኞቻቸውን ለማስወጣት እየሰራ እንደሆነ የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።

ሊንክ      https://www.bbc.com/afaanoromoo/articles/clkj9ek8x73o

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *