Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

መስከረም  15| Sep 26, 2023

Anadolu Ajansı

  • በአማራ ክልል 50 ታጣቂዎች በፀጥታ ሃይሎች እና ሚሊሻዎች መካከል በተነሳ ግጭት  መገደላቸውን የሚገልጽ ነው ።

  የተነሱ ነጥቦች

  • በሰሜን ኢትዮጵያ በሚገኘው የአማራ ክልል የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እና የአማራ ታጣቂዎች በፈጠሩት ግጭት በትንሹ 50 ታጣቂዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ጦር ማስታወቁን
  • በዋነኛነት በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ የተካሄደው ግጭት ከሀገሪቱ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ በስተሰሜን 700 ኪሎ ሜትር 435 ማይል ርቀት ላይ በሚገኘው በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል ስለሚገኘው የክልሉ መረጋጋት ስጋትን መቀስቀሱን
  • የኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት በፌስቡክ ባወጣው መግለጫ ባብዛኛው የተፈፀመውን ከባድ ግጭት የፋኖ ሚሊሻዎች ጥቃት በተሳካ ሁኔታ በመመታቱ ከ50 በላይ ታጣቂዎች መሞታቸውን  ማረጋገጣቸውን
  • በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው እና የአማራ ብሄር ተወላጆችን ያቀፈው የፋኖ ሚሊሻ ቡድን ለፖለቲካዊ እና የትጥቅ እንቅስቃሴው ትኩረት  ማግኘቱን
  • የአማራ ታጣቂዎች ትናንት በማህበራዊ ድረ-ገጾቻቸው በሰጡት መግለጫ በደርዘን የሚቆጠሩ ወታደሮች መማረካቸውን  ማስታወቃቸውን
  • የፌደራል መንግስት ከኢትዮጵያ 11 ክልሎች የተውጣጡ የጸጥታ ሃይሎችን ወደ ፌዴራል ሃይል ለማዋሃድ ያለመ የውህደት ትእዛዝ ባወጣበት ወቅት በክልሉ ግጭቶች መፈጠሩን
  • የአካባቢው ማህበረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደርን ፍራቻ በመግለጽ እና በክልላቸው ውስጥ የጸጥታ ጉዳዮችን በሚቆጣጠሩ የውጭ አካላት ላይ እምነት ማጣትን በመግለጽ እርምጃውን  መቃወማቸውን የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።

ሊንክ    https://www.aa.com.tr/en/africa/50-militants-killed-as-security-forces-militia-clash-in-ethiopia-s-restive-amhara-region/3000496

   Arab News

  • በኢትዮጵያ አማራ ክልል አዲስ ጦርነት  መቀስቀሱን የሚያሳይ ነው ።

 የተነሱ ነጥቦች

  • መንግስት የአካባቢ በአማራ ክልል ብጥብጥ መቀስቀሱንለሃይሎችን ትጥቅ ለማስፈታት ባቀደው መሰረት ሚሊሻዎች ከወታደራዊ ሃይሎች ጋር ሲጋጩ አዲስ ጦርነት  መቀስቀሱን
  • ፋኖ የተሰኘው ሚሊሻ ታጣቂዎች ከወታደራዊ ክፍሎች ጋር  መዋጋታቸውን ነዋሪዎች መግለጻቸውን  
  • በጎንደር ከተማ አሁን ላይ ሰላም ሰፍኖ ቢሆንም የመንግስት ወታደሮቹ ከተማዋን  እንደተቆጠቀጠሩ እና አሁንም አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ነዋሪዎች መግለጻቸውን
  • ለተፈጠረው አለመረጋጋት መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎትን በመዝጋት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማውጣቱን
  • ጦርነቱ በትግራይ አጎራባች ክልል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ በህዳር ወር በተኩስ አቁም የተጠናቀቀውን ቢሆነም አሁን ላይ በአማራ ክልል የተነሳው ግጭት የእርስ በርስ ጦርነት ስጋትን   ፈጥሯል።
  • ብጥብጡ የተቀሰቀሰው የክልሉን ሃይሎች ትጥቅ ለማስፈታት በተጀመረው እቅድ ሲሆን መንግስት የኢትዮጵያ ህገ-መንግስታዊ ስርዓትን አደጋ ላይ ይጥላል ማለቱን
  • የአማራ ብሔር ተወላጆች በቡድናቸው ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት በመጥቀስ የመከላከያ ሃይሉን ጋር እንደሚፋለሙ መናገራቸውን
  • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባሳለፍነው ወር በደረሰው ሁከት ከ180 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የገለፀ ሲሆን የአለም አካሉ የዐማራው ብሔር ተወላጆች መታሰር እንዳሳሰበው መግለጹን
  • የኢትዮጵያ መንግስት የተሰየመው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኮሚሽን እንዳስታወቀው የአካባቢው ባለስልጣናት ለግድያ ኢላማ እየተደረጉ እንደሆነ እና  በአማራ ክልል ብቻ እንደሆነ የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ። 

ሊንክ    https://www.arabnews.com/node/2380441/world

  ZAWYA

  • ግብፅ ሱዳን እና ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ በአዲስ አበባ ድርድር እንደጀመሩ የሚገልጽ ነው ።  

የተነሱ ነጥቦች

  • ስብሰባው በግድቡ አሞላልና ማስኬጃ ደንቦች ላይ የተደረሰውን ስምምነት ለመጨረስ የተደረሰው የአራት ወራት የጊዜ ገደብ አካል እንደነበር
  • ግብፅ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የጀመሩትን ድርድር ለመቀጠል የግብፅ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና ተደራዳሪ ቡድኖች በዋና ከተማ አዲስ አበባ  መገናኘታቸውን
  • ስብሰባው በግድቡ አሞላል እና ስራ ላይ የተደረሰውን ስምምነት ለመጨረስ የተደረሰው የአራት ወራት የጊዜ ገደብ አካል መሆኑን
  • ውይይቱ የተካሄደው ኢትዮጵያ በግብፅ እና በሱዳን ተቃውሞ ቢቀርብም አራተኛውን እና የመጨረሻውን የውሃ ሙሌት ደረጃ ማጠናቀቁን ከሁለት ሳምንት በፊት ማስታወቋን ተከትሎ መሆኑን እና ኢትዮጵያ ያከማቸችውን የውሃ መጠን ወይም የአንድ ወገን እርምጃዋን አንድምታደርግ አለመግለጾን  
  • የግብፅ የውሃ ሃብትና መስኖ ሚኒስትር ሃኒ ስዋይላም ግብፅ በቁም ነገር እና በመልካም አላማ ለድርድሩ ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀው የውሃ ደህንነቷን እና ጥቅሟን የሚያስጠብቅ ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ ስምምነት ላይ ለመድረስ በማለም ለድርድሩ ልማት እና ትብብር ለማረጋገጥ  እንደምታቅድ
  • ስዋይላም ኢትዮጵያ ግድቡን ያለስምምነት እንደሞላች እና በ2015 የተፈረመውን የመርሆች መግለጫ መጣስ እንደሆነ እና አሁን ያለውን የድርድር ሂደት እንደሚያናጋው አስጊ ነው ማለታቸውን
  • በግድቡ አሞላል እና ስራ ላይ አስገዳጅ የህግ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችሉ ቴክኒካል እና ህጋዊ መፍትሄዎችን ማፈላለግ አስፈላጊ መሆኑን  ማሳሰባቸውን የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።

ሊንክ      https://www.zawya.com/en/economy/north-africa/egypt-sudan-and-ethiopia-resume-talks-on-gerd-in-addis-ababa-tyf158zf

 Egypt Independent

  • ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ ከግብፅ ጋር ስላተደረገው ድርድር መግለጫ እንዳወጣች የሚያሳይ ነው ።

 የተነሱ ነጥቦች

  • የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ የተካሄደውን ሁለተኛው የሶስትዮሽ ድርድር አስመልክቶ  መግለጫ መስጠቱን
  • በኢትዮጵያ በሱዳን እና በግብፅ መካከል የተካሄደውን ሁለተኛውን የሶስትዮሽ ድርድር ስታስተናግድ የቆየች ሲሆን ይህ ዙር ውይይት የተጀመረው እድገት በማስመዝገብ እና በታዩ ጉዳዮች ላይ ልዩነቶችን በማጥበብ ብሩህ ተስፋ ነበረው ሲል መግለጫው ማካተቱን
  • በመቀጠልም በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና በክቡር ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ የተጣለባቸውን አደራ እንደማሳካት በማመን እና በፓርቲዎቹ መካከል ያለውን አዎንታዊ መንፈስ ለመጠበቅ በሁለተኛው ዙር ድርድር ላይ ኢትዮጵያ በቅን ልቦና እንደተወያየች በማለት መናገሩን
  • ሶስቱ ሀገራት ሊገናኙ የሚችሉ ጉዳዮችን በመለየት መሻሻል እንደቻሉ በግብፅ ካይሮ የሶስትዮሽ ድርድር እንዲቀጥልም  መስማማታቸውን
  • መግለጫው ግብፅ እንደሚያሳየው የተፈረመውን የመርሆች መግለጫ ስምምነትን የሚያፈርስ አቋም ላይ ትገኛለች ማለታቸውን
  • ግብፅ ከቅኝ ግዛት ዘመን ጀምሮ – በብቸኝነት ብዝበዛ ላይ የተመሰረተ እና የቅኝ ግዛት የውሃ ኮታ በመጠየቅ በድርድሩ ላይ ተጨባጭ እድገት እንዳይኖረው ያደረገችውን ​​አግላይ ውል ለማስቀጠል አጥብቃ መቀጠሏ አሳዛኝ ነው  ማለታቸውን የሚገልጽ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው ።

ሊንክ    https://www.egyptindependent.com/ethiopia-issues-statement-on-gerd-negotiations-with-egypt/

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *