Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

                                                                                                                                                                                   ግንቦት  7|  May 14, 2023

The Nation

  • ኢትዮጵያ እና ፓክ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ትብብር ስምምነት መፈራረማቸውን የሚገልጽ ዘገባ ነው

የተነሱ ነጥቦች

  • የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና የፓኪስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ የሁለቱን ሀገራት ተቋማዊ ትስስር በማጠናከር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት  መፈራረማቸውን ።
  • የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ፎዚያ አሚን እና የፓኪስታን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሳይንስ አማካሪ አቶ ዘይኑል አብዲን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በፓኪስታን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር በተገኙበት  መፈራረማቸውን ።
  • የመግባቢያ ሰነዱ የኢኮ ስርዓትን በመፍጠር ውሎ አድሮ የሁለቱንም ሀገራት ምርታማነት የሚያሳድግ በተለያዩ የሳይንስ ቴክኖሎጂ ጤና ጨርቃጨርቅ ፋርማሲዩቲካል እና ሌሎችም የእውቀት ሽግግር እንዲኖር  እንደሚያስችል ።
  • በስምምነቱ ወቅት ወይዘሮ ፎዚያ አሚን እንዳሉት የመግባቢያ ሰነዱ በሁለቱ ሀገራት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክፍሎች እና የምርምር ተቋማት መካከል ትብብር ለመፍጠር መሰረት የጣለ እንደ ሆነ ነው።
  • ሚኒስትር ዴኤታው እንዳሉት ሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ የጋራ ማስፈጸሚያ እቅድ በማዘጋጀት የሁለቱም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የጋራ አፈፃፀም እቅድ ማውጣቱን  መናገራቸውን ።
  • የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሳይንስ አማካሪ አቶ ዘይኑል አብዲን ስምምነቱን በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ የትብብር መስክ መሆኑን  መግለፃቸውን ።
  • የተፈረመውን ሰነድ ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥታቸው ያለውን ቁርጠኝነት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በእውቀት መጋራት ለምሳሌ በፋርማሲዩቲካል፣ ጨርቃጨርቅ እና ኬሚካል ኢንዱስትሪዎች ኢትዮጵያን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን  ማረጋገጣቸውን ።

ሊንክ      https://www.nation.com.pk/15-May-2023/ethiopia-pak-sign-accord-for-science-tech-cooperation

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *