Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች 

ሰኔ 18 | 2014 ዓ.ም – June 25 |202

Egypt Independent

  • ኢትዮጵያ በ አባይ ግድብ ውዝግብ ላይ የአውሮፓ ህብረት መግለጫን “አድሏዊ” በማለት  እንደገለጸች የዘገበ ነው ።
  • ኢትዮጵያ ታላቁን የህዳሴ ግድብ አስመልክቶ የአውሮፓ ህብረት በቅርቡ ያወጣውን መግለጫ “የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ ብቻ ነው” በማለት መግለጫውን ውድቅ ማድረጓን ባለፈው ሃሙስ ማስታወቋንም በማንሳት መግለጫውን የኢትዮጵያ መንግስት እንደማይቀበለው ያሳየ ዘገባ ነው ያጻፈው።
  • የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ የአውሮፓ ህብረት መግለጫ “በአገሮች መካከል ያለውን የጋራ ጥቅም ያላገናዘበ የግብፅን ጥቅም ብቻ የሚያስጠብቅ ነው” ማልታቸውንም በመጥቀስ ህብረቱ ለግብጽ ያደላ አቋም መያዙ ተገቢ እንዳልሆነና መግለጫው ያዳላ እና በሁሉም መመዘኛዎች ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ያንን የኢትዮጵያ መንግስት በይፋ ማውገዙንም ነው የገለጸው።
  • የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የሶስቱ ሀገራት የህዳሴ ግድብ ድርድር ደጋፊ እና ታዛቢ እንደነበርና በመግለጫውም ግብፅ በሶስትዮሽ ድርድሩ ላይ ያላትን አቋም የሚደግፍ በመሆኑ እንደታዛቢነት ለመቅረብ ተገቢ ያልሆነና ተቀባይነት እንደሌለው በኢትዮጵያ በኩል አቋም መያዙን ነው የገለጸው።
  • ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ

ሊንክ  https://egyptindependent.com/ethiopia-categorically-rejects-eu-statement-on-gerd-crisis-describing-as-biased/

News Ghana

  • ይህኛውም ኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት በአባይ ግድብ ላይ ያለውን አቋም “አድሎአዊ” በማለት ውድቅ  ማድረጓን  ማሳወቋን ነው የጻፈው።
  • የአውሮፓ ህብረት እና ግብፅ በቅርቡ በሰጡት የጋራ መግለጫን  የግብፅን የውሃ ደህንነት ለመጠበቅ እና በአካባቢው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በአባይ ግድብ  መሙላት እና ስራዎች ላይ አስገዳጅ ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚያስፈልግ  ማሳሰቡን ገልጾ  ይህም ተገቢ ያልሆነ አድሏዊ ሀሳብን የያዘ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት እንደማይቀበለው የገለጸበትን ሀሳብ ነው ያስቀመጠው
  • ጉዳዩ ከላይ እንደተቀመጠው  የሚያሳየው የአውሮፓ ህብረት በአባይ ጉዳይ ላይ የሰጠው መግለጫ ለአንድ ወገን እንዳለ የሚያሳይ በመሆኑ የኢትዮጵያን መንግስት ያስቆጠጣ እንደሆነ በሚገባ ያሳየ ዘገባ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ

ሊንክ   https://newsghana.com.gh/ethiopia-rejects-eus-stance-on-nile-dam-as-biased/

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *