Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

1 min read

ሚያዚያ 29|  May 7, 2023

Independent

 • ኢትዮጵያ 61 ሀገራት ዜጎችን ከሱዳን እንዲወጡ ረድታለች ይላል።

የተነሱ ነጥቦች

 • “የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቻቸውን ከሱዳን በግዛቱ ለማስወጣት በዓለም ዙሪያ ካሉ 61 ሀገራት ጋር አስፈላጊውን ድጋፍ እና ትብብር አድርጓል” ሲሉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም መግለጻቸው
 • መንግስት ለ75 የበረራ አገልግሎት ፍቃድ መስጠቱን ጠቅሰው አገራቱ ዜጎቻቸውን ከጎረቤት ሱዳን በኢትዮጵያ አየር ህዋ እንዲያወጡ እንዳስቻላቸው መጠቀሱ
 • እርምጃው ከአለም አቀፍ የሰብአዊ አገልግሎት መርሆዎች ጋር የተጣጣመ እና የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ለማጠማከር ያለመ እንደሆነ መገለጹ
 • እስካሁን 3,517 ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 7,700 ሰዎች ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ቃል አቀባዩ እንዳሳወቁ
 • ኢትዮጵያ በሱዳን ያለውን ግጭት በሱዳን ህዝብ መፍታት እና በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር በሰላማዊ ድርድር መፍታት እንዳለበት ኢትዮጵያ እንደምታምን መገለጹ

ሊንክ   –  https://www.independent.co.ug/ethiopia-helps-61-countries-evacuate-citizens-from-sudan/

  PRENSA LATINA

 • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃላፊ በኢትዮጵያ ሰላም ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት ድጋፍ ጠየቁ
 •  የተነሱ ነጥቦች
 • አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላምን ለማጠናከር እና የማገገሚያ ጥረቶችን ለማፋጠን ያለውን  ቁርጠኝነት በማረጋገጥ ሀገራዊ ጥረቶችን መደገፍ ያለውን ጠቀሜታ አስገንዝበዋል።
 • ጉቴሬዝ ኢትዮጵያ የሰሜንን ግጭት ፈትታ እድገት እያስመዘገበች መሆኗ የተሰማቸውን ደስታ እንደገልጹ እንዲሁም በቀጠናው ማዕከላዊ ሚና ስላላት የኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ለአካባቢው ሁሉ አዎንታዊ አንድምታ እንዳለው አጽንኦት መስጠታቸው
 • በመንግስታቱ ድርጅት እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር መንግስት ከግጭት በኋላ የሚያደርጋቸውን እርምጃዎች ለመደገፍ ሁለቱ ወገኖች መስማማታቸውን እንደገለጹ

ሊንክ   –  https://www.plenglish.com/news/2023/05/07/un-chief-claims-support-for-initiatives-to-keep

The Organization of World Peace / OWP

 • “ የኢትዮ-ትግራይ የሰላም ስምምነት “  በሚል ርዕስ የወጣ ነው።

 የተነሱ ነጥቦች

 • ከህዳር 2020 ጀምሮ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ለሁለት አመታት የዘለቀው ጦርነት እስከ 600,000 የሚደርሱ ንፁሀን ዜጎችን ሳይገድል እንዳልቀረ
 • በዩናይትድ ስቴትስ (አሜሪካ) እና ከአፍሪካ ኅብረት (AU) በተደረገው የሽምግልና ጥረቶች ምስጋና በኅዳር 2022 ከጥቂት የተኩስ አቁም ስምምነት በኋላ ወደ ሰላም እንደተመለሱ እና የሁለቱም ወገኖች ስምምነቶቹን በውጤታማነት ተግባራዊ ለማድረግ እና ልዩነቶቻቸውን ለመፍታት ቁርጠኝነት እስካላቸው ድረስ የሰላም ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም የማስገኘት አቅም እንዳለው
 • ግጭቱ የተባባሰው የኢፌዴሪ መንግስት እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መካከል በተፈጠረ ፖለቲካዊ አለመግባባት እንደነበር
 • ግጭቱ ከተጀመረ አምስት ቀናት በህዳር 9 የህወሓት መሪ ድብረጽዮን ገብረሚካኤል ጦርነቱን ለማስቆም የርአፍሪካ ህብረት ጣልቃ በመግባት የሰላም ድርድር ጠይቆ እንደነበር
 • አቢይ ህወሀትን ከ2018 ጀምሮ ሚሊሻዎችን በማደራጀት ለጦርነት መዘጋጀቱን ከሰው እንደነበር እና መንግስት ላይ በማመፅ በትግራይ ህገወጥ ምርጫን በማካሄዱ በማንሳት እንደከሰሱ
 • እነዚህ መክንያቶች ዋና የጦርነቱ መቀስቀስ መነሻ እንደሆኑ
 • በጦርንቱ ብልጭ እንደተወሰደበት በማወቁ ህወሓት የሰላም ድርድር እንደሚፈልግ መግለጹ
 • በዚያም ድርድሩከመጀመሩ በፊት ቅድመ ሁኔታዎቻቸው እንዲሟሉላቸው ይፈልጋሉ በተለይ በትግራይ አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት እንደተመለሱ
 • የኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄው ከተኩስ አቁም ድርድር የተለየ ጉዳይ ነው በማለት ጥያቄውን ውድቅ አንዳደረገ እና ወደ ስራ ለመግባት የበለጠ የተረጋጋ ሁኔታን እንደሚጠይቅ ገልጹ እንደነበር
 • ተፋላሚዎቹ በሽምግልና ላይ መስማማት ባለመቻላቸው የአፍሪካ ህብረት በፕሮቶርያ ድርድሩን እና ግጭቱን በማካሄድ እንደቋጩት

ሊንክ  https://theowp.org/reports/stakes-of-the-ethiopia-tigray-peace-agreement/

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *