የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
1 min read
መጋቢት 7፣ | 2015 ዓ.ም – march 16 | 2023
CNN
- አንቶኒ ብሊንከን ጉብኝት ወቅት በኢትዮጵያ ለደረሱ ግፍ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂነትን እንዲሰፍር ሀሳብ እንዳነሱ የሚገልጽ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሰሜን ኢትዮጵያ ለዓመታት በዘለቀው ግጭት በሁሉም ወገኖች ለተፈጸሙት ግፍና በደል ተጠያቂነትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ማነጋገራቸው
- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሊንከን በሀገሪቱ የመጀመሪያ የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማት በጎበኙበት መወያየታቸዉ
- አንድ ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን ኒዠርን ከጎበኙ እና የአንቶኒ ብሊንከን ጉብኝት ቡሃለ ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ እንደምትፈልግ
- ብሊንከን እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እሮብ በመጋቢት 6 ፣ 2015 ዓ.ም ባደረጉት ውይይት “የተሻሻለውን የሰብአዊ አቅርቦት እና የመሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ ሌሎች የስምምነት ግዴታዎችን በመተግበር ላይ ስላለው ጉልህ መሻሻል ማንሳታቸዉን” ሚገልጹ ሀሳቦች ከዋና ዋና ነጥቦቹ መካከል ናቸው።
ሊንክ – https://www.cnn.com/2023/03/15/politics/blinken-ethiopia-visit/index.html
Reuters
- የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ኢትዮጵያን በትግራይ የሰፈነውን አንጻራዊ ሰላም ቢያደንቁም ነገር ግን ሀገሪቷን ወደ አሜሪካ የንግድ መርሃ ግብር አላስመለሱም የሚል ነዉ።
የተነሱ ነጥቦች
- የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ረቡዕ ኢትዮጵያ የትግራይን ግጭት ለማስቆም የሰላም ስምምነትን በመተግበር ስላሳየችው መሻሻል ማድነቃቸው
- በሰሜናዊው ክልል ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት የሻከረውን ግንኙነት ለመጠገን፣ ሰላምን ለማጠናከር፣ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ወደነበረበት ለመመለስ እና ሰብአዊ ፍላጎቶችን እጥረት ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ላይ ኢትዮጵያን የጎበኙት ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝተው እንደተወያዩ
- በሰሜኑ ክልል ጦሪነት ምክንያት አሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን የኢኮኖሚ እና የጸጥታ ዕርዳታ በመገደብ ለሀገሪቱ የጨርቃጨርቅ ዘርፍ ፋይዳ የነበረው ከቀረጥ ነፃ የንግድ መርሃ ግብር (AGOA) የተባለው ተቋርጦ እንደነበር
- “በእርግጥም ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ እንደትመለስ እንመኛለን “ ያሉት ብሊንከን ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከሌሎች የመንግስት አካላት ጋር ካደረጉት ውይይት በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ እንደሰጡ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከውይይቱ በኋላ በአገሮቻችን መካከል የቆየውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተናል የሚል መልዕክት በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩ
ሊንክ – https://www.reuters.com/world/africa/blinken-meet-ethiopian-government-leaders-repair-ties-2023-03-15/