የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች
የካቲት 7፣ | 2015 ዓ.ም – Feb. 15 | 2023
Crisis24
- በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በመላ አገሪቱ ሊካሄድ የነበረውን የተቃውሞ ቢራዘምም መንግስት የጸጥታ ጥበቃ ማጠናከሩን የሚገልጽ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- በቤተክርስቲያኒቱ ጉዳይ ላይ መንግስት ፈጽሟል በተባለውለው ጣልቃ የመግባት ጉዳይ እና በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መከፋፈል የተነሳ ውጥረት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ ባለስልጣናት ውይይት ካደረጉ በኋላ ሠልፉ ለሌላ ጊዜ የተራዘመ ቢሆንም፣ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አዲስ የተቃውሞ ጥሪን በድጋሚ ሊያደርግ ይችላል መባሉ።
- በተለይ አዲስ አበባን ጨምሮ በትልልቅ ከተሞች ድንገተኛ መሰባሰቦች ሊደረጉ ባይችሉም ተቃዋሚዎች በሃይማኖታዊ ቦታዎች፣ በከተማ ማዕከሎች እና በሕዝብ አደባባዮች ሊሰበሰቡ እንደሚችሉ መነገሩ
- ማንኛውም ተቃውሞ ቢከሰት እና ተቃዋሚዎች የፖሊስን ትዕዛዝ ካልተቀበሉ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ግጭት ሊፈጠር እንደሚችል
- መነሻው ከጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ሦስት ሊቀ ጳጳሳት እና 25 ሊቃነ ጳጳሳት ተሿሚዎች መገንጠልን ተከትሎ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ‹‹በሕገ ወጥ ቅብዐት›› ውስጥ እጃቸው አለበት በሚል ክስ ስለተመሠረተባቸው በአለመግባባቶች መካከል በኦርቶዶክስ ሀይማኖት መሪዎች እና በመንግሥት መካከል አለመግባባቱ ተፈጥሮ አሁንም እንደቀጠለ
- ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት እስከመሄድ የደረሰ እንደሆነ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
The East African
- በኢትዮጵያ ያለው የሩሲያ ኤምባሲ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ሰተዋል የተባለውን ሀሳብ ሀሰተኛ እንዳልሆነ አጣጥሏል ይላል።
- የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዙሪያ በተነሳው ውዝግብ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል በሚለው በትዊተር የተሠራጨው ሀሰት እንደሆነ
- ፕሬዝዳንቱ “በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች ላይ እየደረሰ ያለው ነገር አዝኛለሁ ከአመታት በፊት ተመሳሳይ ፈተና አጋጥሞናል እናም በእግዚአብሔር እርዳታ አስቸጋሪውን ጊዜ አሳልፈናል። ኢትዮጵያ ችግሮቿን በሕዝቦቿና በእግዚአብሔር ረዳትነት እንደምትወጣ እምነታችን ነው።” ሲል በአማርኛ የተጻፈው ትዊተር ተናግሯልየተባለው ሀሰት እንደነበር።
- ሀሰተኛ ዜናውም PesaCheck በተባለው የእውነተኛ መረጃ አፈላላጊ ድረገጽ እንደተጣራ ነው የተጻፈው።