የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ጥር 26 ፣ | 2015 ዓ.ም – Feb. 3 | 2023
UN News
- ኢትዮጵያ፡ የሰሜን ዕርዳታ ተደራሽነት እየተሻሻለ ቢሆንም አንዳንድ አካባቢዎች ግን ለመድረስ አስቸጋሪ እንደሆነ የሚግለጽ ነው።
የተነሱ ነጥቦች
- የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ በሰሜን በኩል ያለው የዕርዳታ ተደራሽነት መሻሻል እየቀጠለ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ሰጭዎች ሪፐርት ማውጣታቸው
- ነገር ግን በጦርነት በክልሉ ያሉ አንዳንድ ቦታዎች ለመድረስ አስቸጋሪ የሆኑ መኖራቸው
- ያልተደረሰባቸው ቦታዎች እንዳሉ ሆነው ግን አሁን ላይ የእርዳታው ተደራሽነት ከትግራይ አልፎ ወደ አማራና አፋር ክልሎችም መስፋፋት መቻሉ መገለጹ
- ከተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኦቻ ባወጣው የቅርብ ጊዜ የሁኔታዎች ሪፖርት መሰረት ከጥር 12 እስከ 18 ባለው ጊዜ ውስጥ 400,000 የሚጠጉ ሰዎች በትግራይ የምግብ እርዳታ እንዳገኙ
- በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች ትልቅ ስጋት እየሆኑ እንደመጡ
ተቋሙና አጋሮቹ በጋራ ባቀዱት መሠረት ለ 17 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ፣ የውሃ፣ የጤና እና የግብርና ድጋፍ እና ሌሎች ዕርዳታዎችን ለማድረስ አላማ እንዳላቸውም የኢገልጹ ዋና ዋና ነጥቦች ተነስተዋል።
ሊንክ – https://news.un.org/en/story/2023/02/1133112
Northafricapost
- ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል 15 የሚዲያ ተቋማትን አገደች የሚል መልዕክት ያለው ነው።
- የተነሱ ነጥቦች
- የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት በምስራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ የሚሰሩ 15 የውጭ ሚዲያዎችን ማገዱን መረጃዎች እየወጡ እንደሆነ
- የሚዲያ ባለስልጣን እገዳውን ያዘዘው በምርመራ ላይ ያሉ ሚዲያዎች ያለፈቃድ እየሰሩ ነው በሚል እንደሆነ
- ከታገዱት ሚዲያዎች ውስጥም ቢቢሲ ሶማሊኛና የሱማሌው ዩኒቨርሳል ቲቪ እንደሚገኙበት
- ምርመራዉና እርምጃው የተወሰደው በቅርቡ በገለልተኛ ጋዜጠኞች እና በክልሉ ባለስልጣናት መካከል ያለውን መጥፎ ግንኙነት ተከትሎ እንደሆነ
- የኢትዮጵያ የክልል ጋዜጠኞች ማህበር እገዳው የተወሰደው በመገናኛ ብዙሃን በሙስና እና በመሳሰሉት ዘገባዎች ላይ በመሥራታቸው መንግስት የበቀል እርምጃ እንደወሰደ ጠቅሰው እንደሚከሱ የሚገልጹ ዋና ዋና ነጥቦቹ ናቸው።
New Vision
- ኢትዮጵያ በ2023 ከሰሃራ በታች ያሉ 5 ምርጥ ኢኮኖሚዎች ካያላቸው ሀገራት አንዷ በመሆኗ እድገታቸው ለወደፊት ከሚጠበቁ ሀገራት መካክል እንደሆነች ይገልጻል።
የተነሱነጥቦች
- ኢትዮጵያ በ2023 ከሰሃራ በታች ያሉ 5 ምርጥ ኢኮኖሚዎች ካያላቸው ሀገራት ደረጃ 4ኛ ላይ እንደምትገኝ IMF መግለጹ
- በቅርቡ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ ላይ ጫናን ያደረገ ጦርነት ላይ ብትሆንም በፊት የምትቀድመዋን ኬንያን በመቅደም 4ኛ ደረጃ ላይ እንደሆነች
- ጦርነቱ ባይኖር ከዚህ የተሻለ ከፈተኛ ለውጥ እንደምታሳይ እንደሚገመት ተቋሙ እንደገለጸ
- በዚህ አመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት መጠን 126.2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ እና በ13.5 በመቶ እንደሚያድግ እንደተነበየ አይ ኤም ኤፍ መግለጹ
- ይህ አሃዝ በጣም አስደናቂ እንደሆነና በሚቀጥሉት አመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በፍጥነት የሚያደግ እንደሆነ የሚገልጹ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።
ሊንክ – https://www.africanews.com/2023/02/02/top-5-economies-in-sub-saharan-africa-to-watch-out-for