Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

1 min read

ጥር 19 ፣ | 2015 ዓ.ም – Jan 27 | 2023

Al Jazeera

 • ከ2021 መፈንቅለ  መንግስት ሙከራ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሱዳን መጎብኘታቸውን የሚገልጽ ጽሁፍ ነው

የተነሱ ነጥቦች

 • የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሱዳንን  መጎብኘታቸውን  ።
 • መንግስት እና ከሱዳን መንግስት ወታደራዊ መሪ አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተገናኝተው  መወያያታቸውን  ።
 • የሁለቱም የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ግንኙነት ከቅርብ አመታት ወዲህ በውጥረት የተሞላ መሆኑን  
 • በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካካል የነበረው ውጥረት በድንበር ውዝግብ እና በትግራይ ክልል ለሁለት አመታት የዘለቀው ግጭት ስደተኞችን  መጨመሩን ነው ።
 • የሱዳን ገዥው ሉዓላዊ ምክር ቤት ሐሙስ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው አል-ቡርሃን እና አብይ በካርቱም የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር እና ማጎልበት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መወያየታቸውን ።
 • ግብፅ እንደ ስጋት ብላ የምትመለከተው አወዛጋቢው የኢትዮጵያ ሜጋ-ግድብ ላይ ሁለቱ ሰዎች ተግባብተውና ስምምነት ላይ ናቸው ማለቱን ።
 • ቡርሀን የመሩት ሉዓላዊ ምክር ቤት ሱዳንና ኢትዮጵያ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሁሉም ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መሆናቸውን ቡርሃን አጽንኦት መስጠታቸውን ።

ሊንክ    https://www.aljazeera.com/news/2023/1/26/ethiopias-pm-abiy-ahmed-in-sudan-on-first-visit-

Sudan Tribune

 • ሱዳናውያን ከውጭ ጣልቃ ገብነት ውጪ ችግሮችን  እራሳቸው እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጥሪ ማቅረባቸውን የሚገልጽ ዘገባ ነው ።

የተነሱ ነጥቦች

 • የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በካርቱም የአንድ ቀን የስራ ጉብኝት በማድረግ የሱዳን የፖለቲካ ሃይሎች ከውጭ ጣልቃ ገብነት ውጪ ችግሮቻቸውን  እንዲፈቱ  መምከራቸውን  ።
 • በሱዳን ዋና ከተማ ያደረጉት ጉብኝት በሁለቱ ጎረቤቶች መካከል በድንበር ግጭት ከተከሰተ በኋላ ለኢትዮጵያ መሪ የመጀመሪያው ጊዜ መሆኑን ነው።
 • እንደገና በመመለሴ እና በሱዳን ጥበበኛ እና ንቁ ሰዎች መካከል በመሆኔ ደስተኛ ነኝ። ለጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ለተደረገልን አቀባበል አድናቆቴን አቀርባለሁ ”ሲል ዶ/ር አብይ ካርቱም ከደረሱ በኋላ በትዊተር ገፃቸው ላይ ተናግረዋል።
 • ኢትዮጵያ አሁን ባለው ራሷን በሚመራ የፖለቲካ ሂደት ከሱዳን ጋር አጋርነቷን  እንደቀጠለች ።
 • በካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ አል-ቡርሃን እና አህመድ በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ምክክር  ማድረጋቸውን ።
 • በጉብኝቱ ማጠናቀቂያ ላይ የወጣው የጋራ መግለጫ ውይይቶቹ ግዙፉን ግድብ እና የድንበር ውዝግብን ያካተተ ነው  ማለታቸውን ።
 • መግለጫው የአንድ ቀን ጉብኝት አላማ የሱዳን መንግስት እና ህዝቦች በሱዳን ውስጥ መግባባት ላይ በመድረስ ለስለስ ያለ የሽግግር ጊዜ ለመመስረት አጋርነታቸውን እና ድጋፍን ለማሳየት መሆኑን አፅንዖት መስጠታቸውን  ።
 • በጉብኝቱ ማብቂያ ላይ የወጣው መግለጫ ሱዳናውያን ውስጣዊ ችግሮቻቸውን መፍታት ይችላሉ ሲል አፅንዖት መስጠቱን ።
 • በኢትዮጵያ በኩል ሱዳናውያን የሽግግር ሲቪል መንግስት እና ሌሎች ተቋማትን ለመመስረት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተስፋ በማድረግ በሽግግሩ መጨረሻ ላይ ለምርጫ መንገድ ይጠርጋሉ በማለት  መግለጫው  መግለጹን ።

 ሊንክ  https://sudantribune.com/article269975/

Voice of Nigeria

 • ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሞ እና አማራ ብሄረሰብ መካከል የዘር ግጭት እንደገጠመ የሚገልፅ ዘገባ ነው ።

የተነሱ ነጥቦች

 • በኦሮሞ እና በአማራ ብሄር ተወላጆች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት በርካታ ንፁሀን ዜጎች እና ተዋጊዎች መሞታቸውን የዓይን እማኞች መናገራቸውን  ።
 • ጦርነቱ ቅዳሜ በአማራ ክልል በጁሃ ከተማ  መቀስቀሱን በማስከተል የአጸፋውን ምላሽ በመፍራት ስማቸው እንዳይገለጽ ያልፈለጉ እንደሌሎች እማኞች ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደተናገሩት ከሸኔ ተዋጊዎች  የአማራ ልዩ ሃይል በሚጠቀሙበት ካምፕ ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከ20 በላይ የሚሆኑትንወታደሮች መግደላቸውን  ።
 • ጦርነቱ ወደ ሌሎች ከተሞችም  እየተዛመተ መሆኑን እማኙች መናገራቸውን በቀብር ላይ የተሳተፈ ሌላ ምስክር  መናገሩን  በተጨማሪም በጁሃ በርካታ አስከሬኖች መሰብሰቡን  ።
 • በአማራ ክልል በአጣዬ ከተማ በኦላ እና በአማራ ልዩ ሃይል መካከል ግጭት መቀስቀሱን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች እየሸሹ መሆናቸውን እማኝ  መግለጻቸውን ።
 • የሸዋ ሮቢት ሆስፒታል ሀኪም እንደገለጻው ከሰኞ ጀምሮ የበርካታ ሰዎች አስከሬን እንዲሁም አንዳንድ ተጎጂዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ ለኤፒኤ መናገራቸውን ።
 • የአማራ ክልል መንግስት ትናንት ረቡዕ ግጭቱን ያረጋገጠ ሲሆን የፌደራል መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የአማራ ክልል ሃይሎች ሁኔታውን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰሩ መሆናቸውን  ማስታወቁን ።
 • የፌደራል ፖሊስ ቃል አቀባይ ለጥሪዎች ምላሽ አለመስጠቱን የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ለገሰ ቱሉ ስልኩን  መዝጋታቸውን ።
 • አንዳንድ የአማራ እና የኦሮሞ ተወላጆች ሁለቱ የኢትዮጵያ ትላልቅ ብሄረሰቦች በአዲስ እና በአሮጌ ቅሬታዎች ላይ ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ መሆናቸውን ።
 • በኦሮሚያ ክልል አጎራባች አካባቢዎች በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት ሲደርስ የአማራ ሚሊሻዎች እንዲሰማሩ መደረጉን ።
 • የኦሮሞ ሌጋሲ አመራርና ተሟጋች ማህበር በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጫ በአለም አቀፍ ህግ መሰረት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ዜጎቹን የመጠበቅ ግዴታ አለበት ማለቱን ።

  ሊንክ       https://von.gov.ng/ethiopian-faces-ethnic-clashes-in-oromo-amhara/

 The Defence Post

 • ኢትዮጵያ በደርዘን የሚቆጠሩ ቻይናን ባለ ተሽከርካሪ መድፍ ገዛች ይላል።

የተነሱ ነጥቦች

 • ኢትዮጵያ ዘመናዊ SH15 የተሰኘ ባለተሸከርካሪ መድፎችን ከቻይና መግዛቷ
 • መድፎቹን በአቃሽ አርባ ቴክኒካል ማሠልጠኛ ትርዒት ላይ እንዳሳየች
 • መድፎቹ እስከ 50 ኪሎሜትር ርቅት ድረሥ ተተኳሾቻቸውን ማሰወንጨፍ እንደሚችሉ
 • ዘመናዊነታቸው በመድፎቹ ላይ የተሻሉ ቴክኖሎጂን ያካተቱ ኮምፒትረሮች የተገጠሙ እንደሆነ የሚሉት ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።

ሊንክ   https://www.thedefensepost.com/2023/01/26/ethiopia-chinese-wheeled-howitzers/

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *