Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

1 min read

ጥር 18 ፣ | 2015 ዓ.ም – Jan 26 | 2023

The Washington Post

 • የሰላም ውል በመንግስት እና በህወሓት መካከል የተደረገው የነበረውን ጦርነት እንዲቆም መደረጉ ተጨማሪ ግፍ ፍራቻን ለማስወገድ  እንደሆነ የሚገልጽ ዘገባ ነው።

የተነሱ ነጥቦች

 • በኢትዮጵያ ለሶስት ወራት የዘለቀው የሰላም ስምምነት ሰብአዊ እርዳታን እንዲያንሰራራ እና ወደ ትግራይ ክልል የስልክ ግንኙነት እና የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲመለስ ማድረጉን ።
 • ነገር ግን ለጦር ማዕበል ተጠያቂው ከጎረቤት ኤርትራ የሚመጡ ወታደሮች በመቀጠላቸው ብዙ ቤተሰቦች አሁንም ስጋት ውስጥ  መሆናቸውን ።
 • ለሁለት ዓመታት በመንግስት እና በህወሓት መካከል በነበረው ጦርነት የተፈጸሙ አሰቃቂ ድርጊቶችን  እንደነበሩ ።
 • የኢትዮጵያ መንግስት ጦርን ሲደግፉ የነበሩት ኤርትራዊያን ከቦታው መውጣታቸውን በስፋት ቢዘግብም በሶስት የትግራይ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች በቃለ ምልልሳቸው የኤርትራ ወታደሮችን እስከ ማክሰኞ ድረስ ማየታቸውን  መግለፃቸውን ።
 • ሌሎች ደግሞ በገጠር ያሉ የቤተሰባቸው አባላት እዚያ ያሉ ወታደሮችም እንዳልሄዱ እንደነገራቸው  መናገራቸውን ።
 • በፍርሃት ስንኖር ሰላም አንሆንም ያሉት አንድ የከተማዋ ነዋሪ አጸፋውን በመፍራት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ እንደሆነ ።
 • በሳምንቱ መገባደጃ ላይ የኤርትራ ወታደሮችን የጫኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ መኪኖች የሚመስሉ አስመሳይ ኮንቮይዎች ወደ ሰሜን ትግራይን አቋርጠው በመጓዝ ወታደሮቹ በመጨረሻ እየወጡ ነው የሚል ተስፋ በአንዳንድ ነዋሪዎች ላይ መፍጠሩን ።
 • ለዘ ዋሽንግተን ፖስት በቀረበው ቪዲዮ መሰረት ወታደሮች ጥሩንባ እያሰሙ የኤርትራን ባንዲራ ሲያውለበልቡ በጭነት መኪናዎቹ ጎን ላይ መሳለቂያ መልእክቶች  መጻፋቸውን ።

  ሊንክ    https://www.washingtonpost.com/world/2023/01/25/ethiopia-tigray-eritrea-peace-deal/

The Washington Post

 • በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ በጎሳ ግጭት ምክንያት ሰዎች መሞታቸውን የዓይን እማኞች  መናገራቸውን የሚገልጽ ዘገባ ነው ።

የተነሱ ነጥቦች

 • በኦሮሞ እና በአማራ ብሄር ተወላጆች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት በርካታ ንፁሀን ዜጎች እና ተዋጊዎች መሞታቸውን የዓይን እማኞች መናገራቸውን  ።
 • ጦርነቱ ቅዳሜ በአማራ ክልል በጁሃ ከተማ  መቀስቀሱን በማስከተል የአጸፋውን ምላሽ በመፍራት ስማቸው እንዳይገለጽ ያልፈለጉ እንደሌሎች እማኞች ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደተናገሩት ከሸኔ ተዋጊዎች  የአማራ ልዩ ሃይል በሚጠቀሙበት ካምፕ ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከ20 በላይ የሚሆኑትንወታደሮች መግደላቸውን  ።
 • ጦርነቱ ወደ ሌሎች ከተሞችም  እየተዛመተ መሆኑን እማኙች መናገራቸውን በቀብር ላይ የተሳተፈ ሌላ ምስክር  መናገሩን  በተጨማሪም በጁሃ በርካታ አስከሬኖች መሰብሰቡን  ።
 • በአማራ ክልል በአጣዬ ከተማ በኦላ እና በአማራ ልዩ ሃይል መካከል ግጭት መቀስቀሱን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች እየሸሹ መሆናቸውን እማኝ  መግለጻቸውን ።
 • የሸዋ ሮቢት ሆስፒታል ሀኪም እንደገለጻው ከሰኞ ጀምሮ የበርካታ ሰዎች አስከሬን እንዲሁም አንዳንድ ተጎጂዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ ለኤፒኤ መናገራቸውን ።
 • የአማራ ክልል መንግስት ትናንት ረቡዕ ግጭቱን ያረጋገጠ ሲሆን የፌደራል መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የአማራ ክልል ሃይሎች ሁኔታውን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰሩ መሆናቸውን  ማስታወቁን ።
 • የፌደራል ፖሊስ ቃል አቀባይ ለጥሪዎች ምላሽ አለመስጠቱን የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ለገሰ ቱሉ ስልኩን  መዝጋታቸውን ።
 • አንዳንድ የአማራ እና የኦሮሞ ተወላጆች ሁለቱ የኢትዮጵያ ትላልቅ ብሄረሰቦች በአዲስ እና በአሮጌ ቅሬታዎች ላይ ከፍተኛ ፉክክር ውስጥ መሆናቸውን ።
 • በኦሮሚያ ክልል አጎራባች አካባቢዎች በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት ሲደርስ የአማራ ሚሊሻዎች እንዲሰማሩ መደረጉን ።
 • ኦሮሞዎችም በአማራ ተወላጆች ለሞት የሚዳርግ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው ሲሉም  መግለጻቸውን ነው ።
 • የኦሮሞ ሌጋሲ አመራርና ተሟጋች ማህበር በዚህ ሳምንት ባወጣው መግለጫ በአለም አቀፍ ህግ መሰረት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ዜጎቹን የመጠበቅ ግዴታ አለበት ማለቱን ።

ሊንክ    https://www.washingtonpost.com/world/witnesses-say-latest-ethnic-clashes-in-ethiopia-kill-dozens/2023/01/26/27458e12-9d43-11ed-93e0-38551e88239c_story.html

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *