Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

ሰኔ 10 | 2014 ዓ.ምJune 17 |202

Voice of America / VOA

  • በኢትዮጵያ የኦ ኤን ኤን (ONN) ጋዜጠኛ ደሱ ዱላ ከኦሮሚያ ኒውስ ኔትወርክ ወይም ኦ ኤን ኤን በፀረ-ሀገር/ ጸረ ሠላም ተግባር  መከሰሱንና ቅጣቱም እስከ ሞት ቅጣር የሚደርስ ከባድ ሊሆን እንደሚችል መገለጹን ነው የዘገበው።
  • የኢትዮጵያ የሚዲያ ተቆጣጣሪ በሚያዝያ ወር የውሸት ዜና እና የጥላቻ ንግግር እያሰራጩ ነው ባሉ 25 ሚዲያዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ  መወሰዱን ዘግቦ በኢትዮጵያ የሚዲያዎች ነጻነት መከበር ላይ ችግር እንዳለ የሚገልጽ ዘገባ ነው።
  • ነገር ግን የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ተቺዎችን ወይም ተቃዋሚዎችን ዝም ለማሰኘት ህጋዊ መንገዶችን እየተጠቀመ ነው ሲል መናገሩንም በመጥቀስ የዘገባውን ዓላማ ለማጠናከር የሞከረ ነው።
  • መረጃውንም ወ/ሮ ፀዳለ ለማ እንደተናገሩት በሚል “በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የመገናኛ ብዙሃን ክፍሎች ላይ ትልቅ በደል እንዳለ ነው’’ የሚል ሀሳብ በማካተት ሚዲያዎች ላይ መንግስት ከፍተኛ ጫና እያደረገ እንዳለ አድርገው  የተጠቀሙት መሆኑ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ

ሊንክ –  https://www.voanews.com/a/media-arrests-reverberate-across-ethiopian-newsrooms-/6620706.html

The east African

  • የሱዳን ባለስልጣናት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለ ህጋዊ ስምምነት ሌላ ዙር መሙላት በአባይ ላይ ያለውን የፀጥታ ሁኔታን ይጎዳል የሚል ስጋት እንዳላት መግለጿን  ነው የጻፈው።
  •  ሱዳን በዓባይ ላይ የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ኃይል ማምረት እንደተቃወመች ዘገባው ተናግሯል ።
  • የሶስተኛው ሙሌት ቀን እየተቃረበ ሲመጣ ሱዳን የሶስቱ ሀገራት – ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ  የዓባይን ውሃ እንዴት በጋራ መጠቀም እንደሚቻል የረዥም ጊዜ ስምምነትን የሚያፈልጋቸው ጊዜ አሁን ነው እያለች እንድሆነና፣ ስምምነቱ አላመኖሩ የህዳሴ ግድብን ብቻ ሳይሆን ሌሎች በወንዙ ላይ የተገነቡ ግድቦችንም ድህንነት ይጎዳል የሚል እሳቤ ማስቀመጧንም በግልጽ ጽፏል።
  • ሱዳንና ግብጽ በተደጋጋሚ  ስለግድቡ ስምምነት በአስገዳጅነት ቢያነሱም ግን መንግስት ስምምነቱ ባይኖርም የአባይን ግድብ ካቀደው እና ካሰበው ጊዜ ወሀውን ከመሙላት ወደኋላ እንደማይል በግልጽ በማሳየቱ በተወሰነ መልኩም ቢሆንድንጋጤ የፈጠረናቸው እንደሆነም ነው የጽፈው።
  • ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ

ሊንክ  https://www.theeastafrican.co.ke/tea/rest-of-africa/why-sudan-is-wary-of-third-filling-of-ethiopia-nile-dam-3850474

News 24    

  • መንግስት እና ህወሐት በኬንያ የሰላም ድርድር ለማድረግ መስማማታቸውን ነው የዘገብው።
  •  መንግስት ከህወሐት ጋር የሰላም ድርድር የሚካሄድበትን ሁኔታ የሚያጣራ ኮሚቴ እንዳለ መክሰኞ እለት በነበረው የፓርላማ ስብሰባ ላይ መናገራቸውን  በቪዲዮ ዘገባ ለመግለፀ ሞክሯል ።
  • የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፌደራል ሃይሎች ጋር ለ19 ወራት በፈጀ  ግጭት ውስጥ ከቆዩት ከህወሐት ጋር የሰላም ድርድር ሊኖር እንደሚችል ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ መናገራቸውን ጽፎ ይህ የሚያመላክተው መንግስት ከህወሓት ጋር የመደራደር ፍላጎት ማሳየቱን ያመላከተ ሀሳብ ነው ያስቀመጠው።
  • ነገር ግን በአፍሪካ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጎ ኦባሳንጆ እና በኢትዮጵያ ጠ/ሚ አብይ አህመድ መካከል ስላለው መልካም ተግባቦት የህወሓትን ሀይል እንዳስፈራቸውና ይህም በድርድሩ ሠውየው ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፍላጎት ይወኛሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው የሚገልጽ ነው።

ሊንክ   https://www.news24.com/news24/africa/news/tigray-and-ethiopia-agree-on-kenya-convening-peace-talks-20220616

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *