ኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታዎች በተመለከተ በዓለማቀፍ ሚድያዎች የወጡ የተመረጡ ዘገባዎች

መስከረም 27 /2017 ዓ.ም Oct 7 2024
Tvbrics
ኢትዮጵያ በ BRICS አባልነት የንግድና ኢኮኖሚ ግንኙነቷን አጠናክራ ልትቀጥል እንደሆነ ስለመግለቱስ የሚያብራራ ነው።
ዋና ዋና ነጥቦች
- ኢትዮጵያ በቅርብ የ BRICS አባልነቷ የንግድና ኢኮኖሚ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደምትሰራ
- ከሩሲያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል ልዩ የጋራ ትኩረት እንደሚሰጡ
- የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና የንግድ ልውውጥን ለመጨመር ትልቅ ዕቅዶች
- ኢትዮጵያ ለአዲሱ ልማት ባንክ የበኩሏን አስተዋጽኦ ለማበርከት እና የBRICSን አጠቃላይ አጀንዳ ለመደገፍ ያደረገችው ቁርጠኝነት
- በካዛን ፣ ሩሲያ ለሚደረገው የBRICS ስብሰባ በጉጉት እንደሚጠብቅ
Bloomberg
የኢትዮጵያ ፓርላማ አቶ ታዬ አጽቀ ሥላሴን የሀገሪቱ አዲስ ፕሬዝዳንት አድርጎ እንደመረጠ መናገሩን የሚያነሳ ነው።
ዋና ዋና ነጥቦች
- የኢትዮጵያ ፓርላማ ሣህለወርቅ ዘውዴን በመተካት አቶ ታዬ አፅቀ ሥላሴን በፕሬዝዳንትነት መምረጡ
- የቀድሞው ፕሬዝደንት በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በፃፉት ልኡክ ጽሁፍ ላይ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፣ ይህም ያልተጠበቀ ድምጽ እንዲሰጥ መደረጉ
- ከሹመቱ በኋላም የቀድሞው ፕሬዝዳንት የሀገሪቱን ህገ መንግስት ለአቶ ታዬ አስረክበው ለፓርላማ አባላት ንግግር ሳያደርጉ ፓርላማውን መልቃቀቸው