Ethiopian Truth Media

The Enemy Of Truth Is Blind Acceptance.

በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውጭ ሚዲያዎች ዘገባ

ጥቅምት 21 2017 ዓ.ም October 31 2024

  በደቡብ ኢትዮጵያ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት መጨመሩን በማንሳት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና በቀበሌ ሚሊሻዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን በተመለከተ የሚያብራራ ነው።

ዋና ዋና ነጥቦች

  • በኮንሶ ዞን ሰገን ከተማ ማንነቱ ባልታወቀ ታጣቂ በትንሹ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሁለት መቁሰላቸውን በማንሳት በአማሮ/ቆሬ ዞን በጎርኮ ወረዳ የኢትዮጵያ አዲስ አመት ከገባ መስከረም 11 ቀን ጀምሮ በትንሹ 15 ንፁሀን ዜጎች መገደላቸው
  • በምዕራብ ወለጋ ዞን በበጊ ወረዳ ኦላ/ኦነግ-ሼኔ ታጣቂዎች ጥቅምት 16 ቀን ከመንግስት ጋር በተሰለፉና በተለምዶ የቀበሌ ታጣቂዎች እየተባለ በሚጠራው የአካባቢ የጸጥታ ሃይሎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር የትጥቅ ግጭት ማስከተሉን በማቅረብ ጥቃቱ የደረሰው በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ባለው አስተዳደራዊ መልሶ ማዋቀር ሂደት ውስጥ የኤቤሌ ሚሊሻዎች ከበጊ ወደ አምቢሎ ዲላ ቀበሌ ሲሰፍሩ እንደሆነና  በግጭቱ ቢያንስ ሁለት ሰዎች መሞታቸውና በርካቶች መቁሰላቸው

ሊንክ  https://epo.acleddata.com/2024/10/30/ethiopia-weekly-update-29-october-2024/

ዋና ዋና ነጥቦች

  • የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና የጄሲአይ የኢትዮጵያ መረጃ አጠቃቀም አጋርነት (DUP) የኢትዮጵያ ሴቶችን በዲጂታል ጤና እና ጤና መረጃ ስርዓት ላይ ያላቸውን ተሳትፎና ክህሎት ለማሳደግ የሥርዓተ-ፆታ ግንዛቤ እና ሀብት (AGAR) መጀመራቸው
  • AGAR በዲጂታል ጤና እና የጤና መረጃ ስርዓት የሴቶችን ተሳትፎ እና ክህሎት ለማሳደግ ያለመ እንደሆነና ውስጡ የስድስት ወር ስልጠና፣ አማካሪ እና የክህሎት ግንባታ መርሃ ግብር እንደሚያካትት
  • በMOH እና DUP ዲጂታል የጤና ባለሙያዎች የተዘጋጀው የአጋር ሥርዓተ ትምህርት የመረጃ አጠቃቀምን ባህል ለመለወጥ እና የሥርዓተ-ፆታ ግምትን ከኤችአይኤስ ጋር ለማዋሃድ ያለመ እንደሆነና DUP የ AGARን የሥልጠና ሞጁሎች እና የአተገባበር መመሪያን ለማፅደቅ አውደ ጥናት ማካሄዱን በማንሳት  ለመጀመሪያው ቡድን ለመቅጠር መታቀዱን

ሊንክ  https://www.jsi.com/championing-women-digital-health-ethiopia/

 ኢትዮጲያ ከሶማሌላንድ ጋር የወደብ ስምምነት ማድረጓን ተከትሎ ከሶማሊያ ጋር ውጥረት ውስጥ መግባቷን በማንሳት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሶማሌ ክልል ከተገንጣይ ክልል ጋር በተደረገው ስምምነት ላይ በጦርነት ለመሳተፍ ምንም ፍላጎት እንደሌለው  መግለጹን በማንሳት አቅርበዋል። 

ዋና ዋና ነጥቦች

  • በጥር ወር የተፈረመው ስምምነቱ ኢትዮጵያ የሶማሌላንድ የባህር ዳርቻን ለ50 አመታት በሊዝ ስታከራይ መቆየትዋን በማንሳት ኢትዮጲያ ከሶማሌላንድ ጋር የወደብ ስምምነት መፈራረምዋን በማንሳት እ.ኤ.አ. ከ1991 ጀምሮ የሶማሌላንድን ነፃነት ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆኗ ስምምነቱ በሶማሊያ ቁጣን መቀስቀሱን  
  • ዶ/ር አብይ ስምምነቱን የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ የባህር መዳረሻ ፍላጎት መሰረት ያደረገ “የልማት ስምምነት” ሲል መግለጹን ነገር ግን  ሶማሊያ የኢትዮጵያን ስምምነት “ህገወጥ” እና ሉዓላዊነቷን የጣሰ ነው ስትል መውቀስዋን
  • ሶማሊያም ከግብፅ ጋር የጠበቀ ወታደራዊ ግንኙነት በመፍጠር በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ግጭት እንዳይፈጠር ስጋት መፈጠሩን በማንሳት ነገር ግን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሶማሌላንድ ጋር በተደረገው ስምምነት ላይ ጦርነት ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎት እንደሌለው

ሊንክ https://www.barrons.com/news/ethiopia-not-interested-in-war-over-somalia-dispute-pm-cc1136af

About Post Author

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *